Get Mystery Box with random crypto!

#የኢብሊስ_አሟሟት ዱንያ ልትጠናቀቅ ጥቂት ሲቀራት እና ጡሩንባው ከመነፋቱ በፊት የሰው ልጆች | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

#የኢብሊስ_አሟሟት

ዱንያ ልትጠናቀቅ ጥቂት ሲቀራት እና ጡሩንባው
ከመነፋቱ በፊት የሰው ልጆች በየመገበያያዎቻቸው ላይ
በመገበያየት ላይ ሳሉ ድንገት ከፍተኛ ድምፅ ይፈጠርና
ከምድር ሰዎች ግማሹ በድንህጋጤ ሲሞት የተቀሩት
ደግሞ ልክ አውሬ እንዳየ እንስሳት ይደናበራሉ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉም ብዙ ሳይቆዩ ከወደ ሰማይ በኩል
ከፍተኛ የሆነ እና የመብረቅ ነጎድጓድ መሳይ ድምፅ
መጥቶ የተቀረውን ፍጥረት ከሙታን ተርታ ያሰልፋል።
ያን ግዜ ምድር ከህያዋን ፍጥረታት ባዶ ትሆናለች።
ጂኖች፣ ሰዎች እና ሰይጣናት በሙሉ ሙተው ምድር ላይ
ኢብሊስ ብቻውን ይቀራል።ይህች ቅፅበት በአላህ እና
ለኢብሊስ መካከል የነበረችዋ ቃል ኪዳን ምትፈፀምባት
ናት።
አላህም ለመለከል መውት እንዲህ ይለዋል፦"እኔ
በመጀመሪያዎቹም በመጨረሻዎቹም ፍጥረታቴ ቁጥር
ያህል ረዳቶችን መድቤልሃለሁ። የሰማይን እና የምድር
ነዋሪያንን ጉልበት ሁሉ ሚያክል ላንተ ሰጥቼሀለሁ።
ዛሬ የቁጣን እና የበቀልን ልብስ አልብሼሀለሁ። በበቀል
እና በቁጣ ተሞልተህ ወደ ረገምኩት ኢብሊስ ውረድ።
ሞትንም አቅምሰው። ከሞት ምሬትም ፍጥረታት፣ ጂኖች
እና ሰዎች ሁሉ የቀመሱትን እጥፍ ድርብ አድርገህ
አቅምሰው።
ዘባኒያዎችም የጀሀነምን ሰንሰለት ይዘው ይጠብቁሀል።
ከጀሀነም በሆኑ 70,000 አውሬዎችም ተጠቅመህ ግም
የሆነች ነፍሱን ገሽልጣት።ከዝያም ማሊክ/የጅሀነም
ጠባቂን በሯን እንዲከፍት ጥራው" ይላል።
ከዝያም መለከል መውት ለአላህ ትዕዛዝ በመተናነስ ወደ
ምድር ፍፁም አስፈሪ በሆነ ገፅታው ይወርዳል። በዚያ
ገፅታው ሰው፣ጂን እና መላዕክት ቢመለከቱት ትዕይንቱን
መቋቋም አቅቷቸው ይቀልጡ ነበር።
መለከል መውት ምድር ወርዶ ልክ ኢብሊስን
እንደተመለከተው በከፍተኛ ድምፅ ይጮህበት'ና ኢብሊስ
ራሱን ሲስት አንድ ግዜ ይጠልዘዋል።
ይህን ግዜ መለከል መውትም እየተከተለው፦"ቁም አንተ
እርጉም ዛሬ ባጠፋኸው ነፍስ ቁጥር ሁሉ አንተንም ሞትን
አቀምስሃለሁ። ስንት እድሜ ጨርሰሃል!!! ምን ያህል ክፍለ
ዘመናትንስ ነው ፍጥረትን በማጥመም የከረምከው!!!!?
በጀሀነም ሚቆራኙህ ስንት ቁራኛዎች እንዳሉህ ብታይ!
ዛሬማ ባንተ እና በአላህ መካከል የነበረችው ቃል ኪዳን
ምትፈፀምበት ቀን ናት። ዛሬ ወዴት ትሸሻለህ!!!?"
ይለዋል።
ከዝያም ኢብሊስ ወደ ምስራቅ ጫፍ ይሸሻል። ይሁን
እንጂ ፊቱ ላይ መለከል መውትን ያገኘዋል። ባህር ውስጥ
ይሰምጣል። አሁንም ከፊቱ መለከል መውትን ያገኛል፤
ባህርም ይተፋዋል።
ምንም ሳይታክት በተቻለው መጠን ለመሸሽ ምድርን
ይዞራል። ይሁን እንጂ ምንም ማምለጫም ሆነ መሸሸግያ
አይኖርም።ከዝያም ምድር ወገብ ላይ የአደም ቀብር
በሚገኝበት ስፍራ ይቆም'ና፦"አንተ አደም!!! ባንተ ሰበብ
ነው እርጉም ሆኜ የቀራሁት። ምን ነበር ባልተፈጠርክ!'
ይላል።
ከዝያም ኢብሊስ ለመለከል መውት፦"በምን አይነት ፅዋ
ነው ሞትን ምታቀምሰኝ?! ይለዋል።
መለከል መውትም፦"በ ለዟ፣ በሰቀር እና በእሳት ሰዎች
ፅዋ ነው አባዝቼ እማቀምስህ" ይለዋል።
ይህን የተመለከተው ኢብሊስም ጥቂት መሬት ላይ በፀፀት
ይንከባለልና ወደ ምስራቅ እና ወደ ምዕራብ ሲመላለስ
ዘባኒያ የተባሉት የጀሀነም ወታደሮች ድሮ ኢብሊ ከሰማይ
የወረደባት ቦታ ላይ ከጀሀነም አውሬዎች ጋር ሁነው
ይይዙታል።
በአውሬዎቹ እየተዘረገፈ እና እየተሰቃየ ላልተወሰነ ግዜ
በጣዕረ ሞት ላይ ይቆያል። ከዝያም ሀዋ እና አደም
ትዕይንቱን እንዲያዩ ይደረጉ'ና፦"ጠላታችሁን ተመልከቱ።
የሞትን ፅዋም እንዴት እንደሚቀምስ እዩ" ይባላሉ።
ሀዋ እና አደምም፦"ጌታችን ሆይ!!! ፀጋህን እኛ ላይ
ሞልተህልናል" ይላሉ።


ቻናላችን
#join
ያድርጉና ይቀላቀሉ
http://t.me//@arebgendamesjid
✹••••━━✿ ❁ ✿━━••••

የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ