2022-08-25 13:33:16
#በወንጀል #ምክንያት የሚመጣን ቅጣት ሊያስቀሩ የሚችሉ ነገሮች
የአላህን ምህረት ማግኘት ትልቅ ዕድል ነው፣ወንጀላችንን ያለሱ ማንም
ሊምረንና ይቅር ሊለን አይችልምና!
ሙእሚን ወንጀሉ ያሳስበዋል
ሙናፊቅ ግን ከምንም አይቆጥረውም
ቁርኣንና ሐዲሥ የወንጀል መዘዙ ሰዎች/ሰሪዎቹ ላይ እንዳይደርስ
የሚያደርጉ 10- ነገሮች እንዳሉ አመላክተዋል እነሱም፥
➊ ተውበት (ተጸጽቶ ወደ አላህ መመለስ)
➋ኢስቲጝፋር ማድረግ
➌ መልካም ስራዎችን ማብዛት
➍ ስንሞት ሙእሚኖች የሚያደርጉልን ዱዓና ኢስቲጝፋር ለምሳሌ ሰላተል-ጀናዛ
ላይ
➎ ለሞተ ሰው የሚደረጉ መልካም ነገሮች ለምሳሌ ሰደቃ...
➏ የነቢዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ምልጃ
➐ ሙእሚንን ዱኒያ ላይ የሚገጥሙ የተለያዩ ችግርና መከራዎች
➑ የቀብር ጭንቀትና ፈተና/ድንጋጤ
➒ የቂያማ ቀን መከራና ስቃይ
➓ ከወንጀለኛው ወይም ከሰው ልጆች በኩል ምንም ሳይደረግ በአላህ
እዝነትና ይቅር ባይነት
በወንጀላችን ምክንያት ኣኺራ ላይ ይጠብቀን የነበረ ቅጣት ሊቀር ይችላል::
(ከሸይኹል-ኢስላም ንግግር የተወሰደ)
ወንጀልን መጀመሪያውኑ ከበሽታ በላይ እንጠንቀቅ ከተፈተንን ግን ተስፋ
አንቁረጥ የአላህ ረሕመቱ ሰፊ ነው!
ከላይ ከተጠቀሱ ነገሮች በአንዱ ምክንያት ምህረትን እንደምናገኝ ተስፋ
እናድርግ
ዛሬ ነገ ሳንልና ሞት ሳይቀድመን ተጸጽተን እንመለስ!
መስፈርቱን ያሟላ ተውበት የማይሰርዘው ወንጀል የለም!
አብሺሩ ያ ዒባደላህ
( ﻟَﺎ ﺗَﻘْﻨَﻄُﻮﺍ ﻣِﻦْ ﺭَﺣْﻤَﺔِ ﺍﻟﻠﻪ )
SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
589 views10:33