Get Mystery Box with random crypto!

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ                 ክፍል ስምንት    | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

                ክፍል ስምንት

   ከርሱ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ በሆነው አላህ
ምዬ መናገር እችላለሁ፡፡ በዚህ ዓለም ውስጥ ከነቢያት በስተቀር እንደ አቡበክር ያለ ታላቅ ሰው እስከ አሁን ድረስ አልተፈጠረም።

    ብዙ ሙስሊም ወጣቶች ታላላቅ አድርገን የምንቆጥራቸው
ምን አይነት ሰዎችን ነው? እስኪ የአቡበክርን ታሪክ ለመመርመር ጥረት እናድርግ፡፡ ከተራራ የገዘፈ ታላቅነት ጎልቶ ይታየናል። የአስ-ሲዲቅን ሕይወት እንመርምር፡፡

           እስክጠግብ ድረስ እርሳቸው ጠጡ!

      አቡበክር አስ-ሲዲቅ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በዋሻው ተሸሽገው ቆዩ፡፡ ሁለቱንም ረሃብና ጥማት ያሰቃያቸው ጀመር፡፡ አንድ እረኛ ከዋሻው ወዲያ ማዶ ሲያልፍ ተመለከቱ፡፡ ጥቂት ወተት ካለው ይሰጣቸው ዘንድ ለመጠየቅ አቡበክር ወጣ አሉ፡፡ መጠነኛ ወተት ከእረኛው አገኙ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲጠጡ አደረጉ፡፡ አቡበክር ይህን ሁኔታ በተመስጦ ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ፦

  “ወተቱን እኔ እስክረካና እስክጠግብ ድረስ እርሳቸው ጠጡ፡፡” እንዴት ያለው ፍቅር ነው! የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እርካታ የርሳቸው እርካታ ሆነ፡፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጥገብ ለርሳቸውም ጥጋብ ሆነ፡፡ እንዲህ ያለ ፍቅር ታይቶም አይታወቅም! ከዚህ በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)ና ወዳጃቸው ጉዙዋቸውን ወደ መዲና አቀኑ፡፡ አቡበክር በአካባቢው ታዋቂ ነጋዴ ስለነበሩ በየመንገዱ ያገኙዋቸው ሰዎች ሰላምታ
ያቀርቡላቸዋል።

    ስለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ማንነትም ይጠይቋቸው ነበር። አንዱን ሰላም ሲሉት ይህ ሰው ማነው አቡበክር በማለት ይጠይቃቸዋል ይህ መንገድ የሚመራኝ ሰው ነው በማለት ይመልሳሉ። ጠያቂው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡበክር መንገድ የሚመሩት ሰው እንደሆነ እንዲገምት አድርገዋል። በእርግጥ አቡበክርን የሐቅ የእውነትና የጀነት መንገድ ይመሯቸው የነበሩት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው። ዑመር ቢን አል-ኸጣብ የአቡበክር መዓዛ እንደሚስክ ሽቶ ያውዳል ይሉ ነበር፡፡

                     እኔ ተራ ሰው ነኝ
           እርሶ ግን የዚህ ዲን ዓርማ ነዎት!

አቡበክር ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና አብረው በመጓዝ ላይ
እያሉ አንዴ ወደፊት አንዴ ደግሞ ወደኋላ ቆይተው ደግሞ ከግራና
ከቀኝ እየሆኑ ያጅቧቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ምን ሆነህ ነውአቡበክር” ይሏቸዋል። አቡበክርም “መጠበቅ እንዳለብኝ ሳስታውስ ከፊት እሆናለሁ። ከዛም የሚያሳድዱዎትን ሳስታውስ ከኋላ እሆናለሁ ከዚያም በግራዎ በኩል አንድ ነገር እንዳይጎዳዎ እልና በግራዎ እሆናልሁ፡፡" በቀኝ በኩልም ምንም ነገር እንዳያገኝዎ እሰጋና በስተቀኝ እሆናሉ፡፡ ‹‹አቡበክር ይህን ያህል ትወደኛለህ እንዴ?›› ይላሉ፡፡ ‹‹እጀግ በጣም ነው እንጂ ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹በእኔ ቦታ ሆነህ ለመሞት ትፈልጋለህ ማለት ነው?›› ብለው ይጠይቃሉ ‹‹አዎና እኔ ብሞት እኮ ተራ ሰው ነኝ፡፡ እርሶ ግን የማይገኙ የዚህ ዲን አርማ ነዎት፡፡››

            አምሳያ የሌለው ሥነ-ምግባር

   አቡበክር አስ-ሲዲቅ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ እያደረጉ መዲና
እስኪገቡ ድረስ አብረዋቸው ተጓዙ፡፡ ወደ መዲና ሲቃረቡ የመዲና ሰዎች (አንሷሮች) እየጠበቋቸው ነበር፡፡ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በመልክ ለይተው አያውቋቸውም። አቡበክር ለጥበቃ ከፊት ከፊት ይጓዙ ስለ ነበር አንሷሮች ሁሉ እርሳቸው መስለዋቸው ነበርና የተጫነበትን ግመል ይዘውላቸው ወደፊት ይመሩ ጀመር፡፡ ይሄን ጊዜ አቡበክር ሁኔታው ይገባቸውና ኩታቸውን ያወልቁና ጥላ ይሆናቸው ዘንድ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ይከልሉበታል፡፡ አንሳሮችም ወዲያው ነገሩ ይገባቸውና የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ግመል መሳብ ይጀምራሉ።

              የውመል ፉርቃን

       ጊዜው ሄዶ ሙስሊሞች መዲና ላይ መሠብሰብ ጀመሩ። ታላቁ የበድር ጦርነት ተከሰተ፡፡ የአስ-ሲዲቅ ልጅ ዐብዱረህማን በወቅቱ ገና አልሰለመም ነበር፡፡ በውጊያው ዕለት ሰይፉን ከአፎቱ መዘዘና "ማነውየሚገጥመኝ?›› ብሎ ፎከረ፡፡ አቡበክር(ረ.ዐ) ተነሱና ««የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እኔ እገጥመዋለሁ›› አሉ፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) "ተወው እኔ እበቃዋለሁ" ብለው ተነሱ፡፡ ዐብዱረህማን ቢን አቡበክር ከሰለሙ በኋላ ለአባታቸው እንዲህ አሏቸው “ያኔ ካንተ ጋር ላለመግጠም ብዬ እየተደበቅሁ ነበር፡፡
አቡበክርም(ረ.ዐ) ‹‹ወላሂ ያኔ ባገኝህ ኖሮ አልምርህም ነበር›› አሉት፡፡

    አቡበክር ሰውነታቸው ለስላሳና ክብደታቸው ቀላል ቢሆንም
የቀልባቸው ጥንካሬ ግን ድንቅ ነበር፡፡ የአላህ (ሱ.ወ) ውሳኔ እርሳቸውን የመሰሉ ሰዎች በዓርአያነት ይከተሏቸው ዘንድ ገርና ለስላሳ ሆነው ተፈጠሩ፡፡ ህይወታቸውና ገንዘባቸው የአላህ (ሱ.ወ) ዲን የበላይ ይሆንዘንድ የማያወላውሉ ሰዎች አስ-ሲዲቅን በዓርአያነት መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ እርሳቸውን ሞዴል ማድርግ አለባቸው፡፡

    የበድርን ውጊያ አቡበክር ጀብድ በተሞላበት ሁኔታ ነው ያሳለፉት፡፡ በወቅቱ ሶሃባዎች ከከህዲያኖች ይከላከልላቸው ዘንድ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዙፋን ሠርተውላቸው ነበር፡፡ ይህን ሠርተው ካበቁ በኋላ ከረሱል (ስ.ዐ.ወ) ጎን ሆኖ የሚከላከል ሰው ይመርጡ ጀመር፡፡ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ዓልይ ቢን አቡጣሊብ(ረ.ዐ) ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ ‹‹ይህንኑ ኃላፊነት ለመውጣት ሁላችንም አፈግፍገን ነበር፡፡ አቡበክር ሰይፋቸውን መዘው መጡና ‹‹የረሱልን ዙፋን እኔ እየጠበቅኩ እከላከላለሁ አሉ፡፡ እስከመጨረሻው የውጊያ ሰዓት ድረስም ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሳይለዩ በተከላካይነት ቆዩ፡፡››

   አቡበክር የነበራቸው ወኔ እጅግ ከፍተኛና እንግዳ ነበር፡፡ ለጀነት
በተለይ ደግሞ ለከፍተኛው የፊርደውስ ጀነት የነበራቸው ጉጉት
አስገራሚ ነው፡፡ ይህንን ክስተት እስኪ እናስተውል።

   አንድ ቀን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦቻቸውን (የዕምነት ጓዶቻቸውን)
ሰብስበው ስለጀነት ሰዎች ሁኔታ ይነግሯቸው ነበር፡፡ ‹‹ጀነት ውስጥ የተለያዩ የማዕረግ በሮች አሉ፡፡ እንደየሥራው በየበሩ የሚጠራ ሰው አለ፡፡ የሰላት ሰው በሰላት በር፤ የጾመ ሰው ረያን በሚባል በር፤ ሙጃሂድ ሆነ የሞተ ሰው የጂሀድ በር በሚባለው በኩል፤ የሶደቃ ሰው የነበረ በሶደቃ በር፣ በሚባለው በኩል እንደየሥራው እየተጠራ ይገባል›› ብለው ነገሯቸው፡፡

የጀነት ጉጉታቸው ወደር ያልነበረው አቡበክር እንዲህ በማለት ጠየቁ... ‹‹አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በሁሉም በር እየተጠሩ መግባት የሚቻልበት ሁኔታ አለን?›› ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) «እንዴታ አቡበክር አንተ ከእንዲህ ዓይነት ሰዎች እንድትሆን እመኛለሁ፡፡» አሏቸው።

                  ሁለገብ ማንነት

  በአንድ ወቅት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊሞችን የፈጅር ሶላት ካሰገዷቸው በኋላ ወደ እነርሱ ተቀጣጭተው ተቀመጡና እንደሚከተለው ጥያቂያዎችን አቅረቡ፡፡ «ከናንተ ውስጥ ማነው ለዛሬ ጾምን ነይቶ ያደረው፡፡ ሁሉም ዝም ሲሉ ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) «አንቱ የአላህ መልእክተኛ! እኔ ለመጾም ነይቼ አላደርኩም›› አቡበክር(ረ.ዐ) ቀበል አደረጉና «እኔ ጾምን ነይቼ ነው ያደርኩት» አሉ፡፡ ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ጥያቄዎችን እያከታተሉጠየቁ «ከእናንተ ውስጥ ታማሚን የጠየቀ ማነው?» «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኛ በቀጥታ የመጣነው ፈጅር ለመስገድ ነው በዚህ ሰዓት እንዴት የታመመን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡» በማለት ሰይድ ዑመር....
http://t.me//@arebgendamesjid