Get Mystery Box with random crypto!

#ተውበት (ወደ አላህ መመለስ) ተዉበት በሠራነዉ ስራ ተፀፅተን ወደአላህ መመለስ ከፈጣሪ ምህረትን | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

#ተውበት (ወደ አላህ መመለስ)
ተዉበት በሠራነዉ ስራ ተፀፅተን ወደአላህ መመለስ ከፈጣሪ ምህረትን መጠየቅ
ነው ይችን ዱኒያ ዛሬ ይሁን ነገ መቸ እንደምንለያት አናቅምና ሁሌም መች እና
እንደት እንደሚመጣብን ለማናዉቀዉ ሞት ማስታወስ ግድ ነው በየትኛዉ ሠከንድ
እንደሚመጣ የአላህ ቀጠሮ አናዉቅምና
ተውበት (ወደ አላህ መመለስ)

#ተውበት፡- በአላህ ትእዛዝ ላይ ከማመፅ ለህግጋቱ ወደ መታዘዝ. መመለስ ነው፡፡

#ተውበት፡- ተውበት አላህዘንድ በጣም የተወደደ ነው።
‹‹… ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟﺘَّﻮَّﺍﺑِﻴﻦَ ﻭَﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟْﻤُﺘَﻄَﻬِّﺮِﻱﻥَ
‹‹ ....አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል
በላቸው፡፡››
አል በቀራህ 222
ተውበት በእያንዳንዱ አማኝ ላይ ግዴታ ነው፡፡
አላህ እንድህ ይላል:-
ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺗَﻮْﺑَﺔً ﻧَّﺼُﻮﺣًﺎ ﻋَﺴَﻰٰ ﺭَﺑُّﻜُﻢْ ﺃَﻥ ﻳُﻜَﻔِّﺮَ ﻋَﻨﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ
ﻭَﻳُﺪْﺧِﻠَﻜُﻢْ ﺟَﻨَّﺎﺕٍ ﺗَﺠْﺮِﻱ ﻣِﻦ ﺗَﺤْﺘِﻬَﺎ ﺍﻟْﺄَﻧْﻬَﺎﺭُ ﻳَﻮْﻡَ ﻟَﺎ ﻳُﺨْﺰِﻱ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲَّ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻣَﻌَﻪُ ۖ
ﻧُﻮﺭُﻫُﻢْ ﻳَﺴْﻌَﻰٰ ﺑَﻴْﻦَ ﺃَﻳْﺪِﻳﻬِﻢْ ﻭَﺑِﺄَﻳْﻤَﺎﻧِﻪِﻡْ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﺃَﺗْﻤِﻢْ ﻟَﻨَﺎ ﻧُﻮﺭَﻧَﺎ ﻭَﺍﻏْﻔِﺮْ ﻟَﻨَﺎ ۖ ﺇِﻧَّﻚَ ﻋَﻠَﻰٰ
ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮٌ
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ንፁህ የኮነችን ፀፀት በመፀፀት ወደ አላህ
ተመለሱ…..››
አል ተህሪም 8
‹‹… ﻭَﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺃَﻳُّﻪَ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ
‹‹ ... ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ)
ተጸጸቱ፡፡››
ሱረት አል-ኑር 31
መድህን (ፈላህ) ማግኘት ማለት አንድ ሰው የፈለገውን ማግኘት የሚፈራውን
ነገር መዳን ነው፡፡
ፍፁምና እውነተኛ የሆነ ተውበት፡- ኃጢአቱ የፈለጉትን ያህል ቢከብድና ቢበዛም
እንኳን አላህ # ፍፁምና_እውነተኛ ከሆነ ተውበት ኃጢአቶችን ሁሉ ይቅር ብሎ
ምህረት ያደርጋል፡፡
۞ ﻗُﻞْ ﻳَﺎ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﺳْﺮَﻓُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰٰ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻟَﺎ ﺗَﻘْﻨَﻄُﻮﺍ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ۚ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﻐْﻔِﺮُ
ﺍﻟﺬُّﻧُﻮﺏَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﻐَﻔُﻮﺭُ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት
ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው
አዛኙ ነውና፡፡
አል-ዙመር - 53
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ