Get Mystery Box with random crypto!

አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡ ወጣትነትህን     ከማርጀትህ በፊት | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡

ወጣትነትህን     ከማርጀትህ በፊት
ጤንነትህን       ከመታመምህ በፊት
ሀብትህን         ከመደህየትህ በፊት
ትርፍ ጊዜህን    ከመጨናነቅህ በፊት
ህይወትህን         ከመሞትህ በፊት

የአሏህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ሲናገሩ " ሕዝቦች አምስት ነገሮችን በመውደድ ከአምስት ነገሮቺ ይዘናጋሉ"  ካሉ በኀላ ሲዘረዝሯቸው እንዲህ አሉ:

   ሕይወትን ያፈቅሩና - ሞትን ይረሳሉ:

ዱንያን ያፈቅሩና -አኼራን ይዘነጋሉ፡

  ህንፃ መገንባት ይወዱና - ቀብር  መኖሩን ይዘነጋሉ፡

  ገንዘብ ይወዱና - ከሒሳብ ( በቂያማ ግዜ መተሳሰቡን ) ይዘነጋሉ ፡

ፋጡራንን ያፈቅሩና - ፈጣሪን ይዘነጋሉ ፡፡
አሏህ ከዚህ ተግባር ይጠብቀን ኣሚን ፡፡

http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ