Get Mystery Box with random crypto!

》መዉሊድ 《 በታላቁ ሸይኽ ዱክቱር ሷሊህ አል ፈውዛን من كتاب الخطب المنبرية لمع | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

》መዉሊድ 《
በታላቁ ሸይኽ ዱክቱር ሷሊህ አል ፈውዛን من كتاب الخطب المنبرية لمعالي
الشيخ 1الدكتور صالح الفوزان/ج

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ሙውሊድ በብዙ አቅጣጫ ከንቱ እና ሀራም ነው።
①በዲን ላይ ፈጠራ ነው ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው ሙሊድን ማቆም የሚያዩ ሰወች ከሸሪአ ማስረጃን ሊያቆሙለት አይችሉም
②ሙሊድ ነሷራዎችን በኢሳ ልደት ላይ በማክበራቸው ላይ መመሳሰል ነው በነሷራዎች ከመመሳሰል ደግሞ በርግጥ ተከልክለናል
③በመውሊድ ዉስጥ በአብዘሃኛው ግዜ በተወገዙ  እና እርም በተደረጉ ነገሮች ላይ ይወድቃል እርም ከተደረጉ ነገሮች ትልቁ በአሏህ ማጋራት ነው ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለምን መጣራት በሳቸዉም እርዳታን መጠየቅ ሽርክ ያለባቸዉን ስንኞችን ነብዩን ማወደስ ላይ መግጠምን ይመስል ቡሩዳ የተሰኘው ስንኝ እና መሰሎቹ(መውሊድ ላይ ይከሰታል)
④በእስልምና ላይ ሁለት በዓል እንጂ የለም ¹ኢዱል_አድሃ እና የተባረከው ²ኢዱል_ፈጥር ሶስተኛ በዓልን የፈጠረ በርግጥም በእስልምና ከርሱ ያላደለን ፈጥሯል
አነስ ኢብኑ ማሊክ ከርሱ የተገኘውን አሏህ ይውደድለትና እንድህ አለ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም መደመዲና ገቡ ለመዲና ሰወችም በነሱ ዉሰጥ የሚጫወቱባቸዉ ሁለት ቀን ነበራቸው ነብዩም እነዚህ ቀኖች ምንድን ናቸው አሉ እነሱም በጃሂልያ ግዜ እንጫወትባቸው ነበር አሉ ነብዩም እንድህ አሉ አሏህ ከነዚህ ቀኖች የተሻለ የሆነን ቀን ለውጦላቹሀል ¹የእርዱ ቀን እና ²የፈጥሩ ቀን
አቡ ዳውድ አህመድ ነሳኢይ ዘግበውታል ሰነዱ በሙስሊም ነስፈርት ነው

እናንተ የአሏህ ባሪያዎች ሆይ አሏህን ፍሩ ቢድአንና ተፃርኖን ተጠንቀቁ ሱናን ሙጭኝ አድርጋቹህ ያዙ ተከተሉ አትፍጠሩ
أعوذ بالله من الشيطان الرجيم
وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
بارك الله لي ولكم في القرآن العظيم
)من كتاب الخطب المنبرية، لمعالي الشيخ الدكتور صالح الفوزان/ج1)·
☞ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈዉዛን [አሏህ ይጠብቃቸዉ] እንዲህ አሉ ፦
[ልክ ወደ መልካም ተጣሪዎች እንዳሉት ሁሉ ፡ ወደ መጥፎ ተጣሪዎችም አሉ

☞ሰዎች ደግሞ ከመልካም ተጣሪዎች ይልቅ ወደ መጥፎ ተጣሪዎች የቀረቡ ናቸዉ ፡ ምክንያቱም ነፍሶች ወደ ፊትና እና ወደ ሹብሀ የተዘነበሉ ናቸዉ አሏህ ያዘነለት ሲቀር ]

ምንጭ ☞ሸርህ ኪታብ አል-ፊተን ወል ሀዋዲስ [83]
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ