Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ሰው ልጅ ክህደት የአላህ ፍጥረቶች ምን አሉ? ' ምድር በየቀኑ እንዲህ በማለት ጌታዋን ትጣ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

ስለ ሰው ልጅ ክህደት የአላህ ፍጥረቶች ምን አሉ?
"
ምድር በየቀኑ እንዲህ በማለት ጌታዋን ትጣራለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ልዋጠው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

ተራራም እንዲህ በማለት የጌታዋን ፍቃድ ትጠይቃለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ላጣብቀው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

ባህርም በተራዋ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን እንዳሠምጠው ፍቀድልኝ ፣እርሱ ያንተን እርዚቅ እየበላ አያመሰግንህም» ትላለች

ሰማይም «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን አንዳች መቅሰፍት ላውርድበት ፍቀድልኝ እርሱ የአንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም» በማለት ትጣራለች።

#አሏህም « ፍጥረቶቼ ሆይ,,,, የሰው ልጅን የፈጠራችሁት እናንተ ናቹህን»? ይላቸዋል

«#ጌታችን #ሆይ አይደለም» ይላሉ ጥራት የተገባው አሏህም እንዲህ ይላል፦ እናንተ ብትፈጥሯቸው ታዝኑላቸው ነበር።

የነሱን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ከነሱ ወደኔ ተፀፅቶ የተመለሰ «አንተ ተውበት አድራጊ ሆይ
እንኳን ደህና መጣህ ብየ ከርቀት እቀበለዋለሁኝ ።

ወንጀል ሰርቶ ከኔ ለሚሸሸው ደግሞ፦ ወደርሱ ቀርቤ ፦ ባርያዬ ወዴት ነው የምትሄደው ከእኔ ውጭ ሌላ ጌታ አገኘህን፤ ከኔ ውጭስ ሌላ አዛኝ የሆነ ጌታ አገኘህን የምትሸሸኝ »በማለት እጠራዋለሁኝ።

ጌታዬ ሆይ ከርቀት የምትቀበለው ወዳንተ ተመላሽ ባርያ አድርገን።አሚን

SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ