Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-28 10:54:17
11.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:18:14
በወላይታ ዞን የሚደረገው የድጋሚ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ እና የምርጫ ሂደት ሰኔ 12 በአንድ ቀን ስለሆነ እርስዎም በእለቱ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ይሳተፉ።
1.2K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 14:50:51
Chairwoman of the National Election Board of Ethiopia (NEBE), H.E. Ms. Birtukan Midekssa with EHRC's Chief Commissioner Daniel Bekele met H.E. Mr. Jochen Flasbarth, the State Secretary of BMZ and German Ambassador to Ethiopia Stephan Auer, On June 7, 2023, Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) hosted a delegation from the German Ministry for Economic Cooperation and Development (BMZ) at its headquarters in Addis Ababa.
Click the bellow link for more:
https://fb.watch/l46nEMISyC/?mibextid=2Rb1fB
4.5K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:45:45
ድምፅሽ ነገሽን ይወስናል!
2.1K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 10:42:04
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በሚገኘው የወላይታ ዞን ሰኔ 12 የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ይደረጋል።
3.7K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 08:46:39
በሕዝበ ውሣኔ ሕዝቦች ያለ ምንም አድሎ እና እንግልት ውሣኔያቸውን ወይም ፍላጎታቸውን ይገልፃሉ።ግልጽ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓትን ለማረጋገጥ ቦርዱ ባረቀቀው ዝርዝር የአሠራር ሥርዓት መመሪያ መሠረት ይፈፀማል።
5.1K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 15:41:24
ህዝበ ውሳኔ በሕገ-መንግሥቱ ወይም አግባብ ባላቸው ህጎች መሠረት ሲወሰን የህዝብን ፍላጎት ለመለካት ወይንም የህዝብን ውሳኔ ለማወቅ የሚደረግ የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ነው፡፡
5.7K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 17:06:25
11.4K views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 17:05:54 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን ለሚያካሄደው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን የሚያካሄደው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ላይ ለሚሣተፉ በየደረጃው ለሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ሰጠ። ከግንቦት 16 ቀን እስከ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በተሰጠው ሥልጠናም የሥራ ትውውቅ፣ የውጤት ማመሳከር፣ የማዳመርና የይፋ አደራረግ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለዞንና ለማዕከል አስተባባሪዎች የተሰጠ ሲሆን፤ ለመሥክ አሠልጣኞችም እንዲሁ የአሠልጣኞች ሥልጠና በሶዶ ከተማ ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ቦርዱ በወላይታ ዞን ውስጥ በተቋቋሙ 12 ማስተባበሪያ ማዕከላት ላይ ለ3608 የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች በሁለት ዙር ሥልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ዙር ሥልጠና ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሰጥ፤ የሁለተኛ ዙር ሥልጠናም እንዲሁ ከግንቦት 26 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

በወላይታ ዞን የተካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ለምን መድገም እንዳስፈለገ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ ይኸውም በወላይታ ዞን የተፈጸሙ የሕግ ጥሠቶችን፤ ከድምፅ አሰጣጥና ውጤት አስተዳደር/አገላለጽ ሂደት ጋር የተያያዙ ምርጫ ነክ ወንጀሎችን፣ የሚያስከትሉትን የወንጀል ተጠያቂነትና የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጻሚዎች ኃላፊነቶችን የሥነ-ምግባር ደንብ በማጣቀስ ጭምር ሥልጠናው ተሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ ከመራጮች ምዝገባና ድምፅ መስጫ ቀን አስቀድሞ ስለሚደረጉ ዝግጅቶች እንዲሁም የምርጫ ጣቢያዎችን ተደራሽና አካታች ለማድረግ መሠራት ስላለባቸው ሥራዎች፤ በመራጮች ምዝገባና በድምፅ መስጫ ቀንም ጥቅም ላይ ስለሚውሉ ቁሳቁሶች የተመለከተ ገለጻ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በሥልጠናው ወቅት በመራጭነት የመመዝገብና የድምፅ መስጠት ሂደትን፣ የድምፅ ቆጠራ ሂደትን፣ የውጤት ማመሳከርና መለየትን፤ እንዲሁም የምርጫ ጣቢያ ቁሳቁሶች በሚታሸጉበት ወቅት መከተል ስለሚገባው ሥርዓት በንድፈ ሃሳበና በተግባር ልምምድ የታገዘ ሥልጠና ተሰጥቷል።
10.4K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 12:50:39
8.9K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ