Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-04 17:05:50
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሱማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሱፌፓ) ሕጋዊ የክልል ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ሰጥቷል።
2.2K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 10:57:52
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት የመሣተፍ ፍላጎት ላላቸው የሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሥልጠና እና ዕውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ በታዛቢነት የመሣተፍ ፍላጎት ላላቸው የሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት ስድስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማመልከቻቸውን አስገብተው የተገመገሙ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አራቱ ግምገማውን አልፈውና አስፈላጊውን ሥልጠና ወስደው ዕውቅና አግኝተዋል። ዕውቅና ያገኙት ታዛቢ ድርጅቶች ባመለከቱት መሠረት ለጠቅላላው የምርጫ ዑደት 5,274 ታዛቢዎችን እንደሚያሰማሩ ይጠበቃል።
ግምገማውን ያለፉት ታዛቢ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች
• የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE)፣
• ድሬ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት (DICDO)፣
• የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ/EHRCO) እና
• የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ናቸው።

በሕዝበ ውሣኔው የመራጮች ምዝገባ ሂደት፤ ኢ.ሰ.መ. ኮ’ን ጨምሮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተውጣጡ 117 ታዛቢዎችና 17 ሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪዎች በመሥክ ላይ ይገኛሉ።
917 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 10:22:45
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢ.ሰ.መ.ኮ) የሰብአዊ መብት ተከታታዮች እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ እና በቡሌ ምርጫ ክልል የሚፈፀመው የድጋሚ ምርጫ ሂደት የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ እንዲከታተሉ ለ 17 የኢ.ሰ.መ.ኮ ሰራተኞች የሰብአዊ መብት ተከታታይነት (Human Rights Monitors) እውቅና ሰጠ።
የሰብአዊ መብት ተከታታዮቹ በምርጫ ጣቢያዎች እና የምርጫ ማስተባበሪያ ፅ/ቤቶች ተገኝተው ለኮሚሽኑ በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብት ክትትልን አስመልክቶ በህግ የተሰጠውን ሀላፊነት በአስቻይ ሁኔታ ለመፈፀም የሚያስችል የመለያ ካርድ ወይም ባጅ በቦርዱ የተሰጣቸው ፣ የምርጫ ህጉን እና ኮሚሽንኑ ያቋቋመውን አዋጅ-ማእቀፍ በማድረግ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በማድረግ ነው።

የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ክትትል የመራጮች ምዝገባ ወቅት፣ በህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ እለት እና የድህረ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ወቅትንም ይጨምራል።ኮሚሽኑ የመራጮች ምዝገባ ክትትሉ በአምስት ዞኖች በአንድ ልዩ ወረዳ እና ተፈናቃይ ዜጎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተለያዩ መመዘኛዎችን በመጠቀም የክትትል ቦታዎችን በመምረጥ እንዲሁም የተለያዩ ስነ-ዘዴዎችን በመጠቀም ክትትሉን እንደሚያካሂድ ለቦርዱ ገልጿል ።
1.2K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 19:11:25 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምዝገባ የተሰረዘባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች በተመለከተ የተሰጠ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ እያከናወነ ባለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት፤ በቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል በተዋቀሩ የክትትልና የቁጥጥር ቡድን አማካኝነት በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ የተወሠኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን ማረጋገጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔ ጣቢያዎቹ ላይ የተደረገው ምዝገባ እንዲሠረዝ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱም ሙሉ በሙሉ እንዲቆምና እንዲሁም የጣቢያዎቹ ሠራተኞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የመራጮች ምዝገባውም አዲስ ሠራተኞች ተመልምለው በድጋሚ እንዲደረግ መመሪያ በሰጠው መሠረት፤ የመራጮች ምዝገባው በተሠረዘባቸው ጣቢያዎች ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የመራጮች ምዝገባ ስለሚካሔድ፤ ቀደም ሲል በእነዚህ ጣቢያዎች የተሠረዙ መዝገቦች ላይ ሕጉን ተከትሎ የተመዘገቡት እንዲሁም አዲስ መመዝገብ የሚፈልጉ መራጮች በተጠቀሱት ቀናት (ከታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ውጪ) በጣቢያዎቹ ቀርበው እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።
ቦርዱ በጣቢያዎቹ ላይ ክትትሉን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ዳግመኛ መሠረታዊ የሕግ ጥሠት የሚፈጸም ከሆነ በአካባቢው የሚካሄደውን የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ የሚሠርዝ መሆኑን ያሳውቃል።

የድጋሚ ምዝገባ የሚደረግባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዱቦ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ዱቦ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዶላ ምርጫ ጣቢያ ሦስት ንዑስ ጣቢያ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ቤታሎ ለ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ጫማ ሄምቤቾ ምርጫ ጣቢያ አምስት
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ወርሙማ ሀ
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ማንቴ ጌራራ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ጌራራ ሦስት
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ቶሜ ጌሬራ ምርጫ ጣቢያ ቶሜ ጌሬራ አራት
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ዋጭጋ ቡሻ ምርጫ ጣቢያ ዋጭጋ ቡሻ 02
• ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል ጃዉላ ጎሬ አዳ ምርጫ ጣቢያ
• ጎፋ ዞን ሳውላ ጃዉላ ውጋ መሸተላ ምርጫ ጣቢያ ሀ
• ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል፣ ቡልቂ ከተማ ምርጫ ጣቢያ ቡልቂ 01 ሀ
• ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል ገልጣ ሜላንቴ ምርጫ ጣቢያ ገልጣ ሀ
• ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል በቶ ታዉን ምርጫ ጣቢያ ሁለት
• ጋሞ ዞን ብርብር በፋርጎሳ ምርጫ ጣቢያ
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ሀ1
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ለ2
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2_3
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2_2
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2-1
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሳ 1ሀ
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ሀ
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ታኅሣሥ 24 ቀን 2015 ዓ.ም.
2.4K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 16:57:38
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቋመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ከዚሁ ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሕዝበ ውሣኔው የሚሣተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑም ሰዓት በአንድ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማቆያ ካምፕ ውስጥ ላሉ መራጮች፤ ሰባት ልዩ ምርጫ ጣቢያዎችን ማለትም በኮንሶ 3፣ በአሌ 3 እና በዲራሼ 1 ምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም፤ የመራጮች ምዝገባን የተመለከተ “ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች” ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የተዋረድ ሥልጠና ሰጥቷል፤ ለመራጮች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች ሥርጭቱንም እንዲሁ አጠናቋል።

በዚህም መሠረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመራጮች ምዝገባ ከነገ ቅዳሜ ታኅሣሥ 22 እስከ ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወን ይሆናል።
2.2K viewsedited  13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 16:07:54
ከታኅሣሥ 11 እስከ ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከናወነው የመራጮች ምዝገባ ሪፖርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከታኅሣሥ 11 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በ3753 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ምዝገባ 1,773,670 መራጮችን የመዘገበ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 217 የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል። አጠቃላይ የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽ 943,076 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 830,594 ሴቶች ናቸው። ከተመዘገቡት የአካል ጉዳተኞች ውስጥም እንዲሁ 111 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪ 106 ወንዶች ናቸው።

የሪፖርቱን ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ሰንጠረዥ ላይ ያገኙታል።
2.4K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 10:27:49
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለኅብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ (ኅዴነፓ) ሕጋዊ የክልል ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ሰጥቷል።
1.8K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 14:04:16
2.9K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 11:46:04 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሣኔ በሚካሄድባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተፈጸሙ የሕግ ጥሠቶችን በተመለከተ የወሰዳቸው የዕርምት ዕርምጃዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያከሂደው ሕዝበ ውሣኔ የምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም የመራጮች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህንንም የምዝገባ ሂደት ለመከታተትልና ለመቆጣጠር ከቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል የተዋቀረ ቡድን ከታኅሣሥ 16 - ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባደረገው የክትትል ሥራ፤ በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ ከታች በዝርዝሩ ላይ በተጠቀሱት የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል።

ቦርዱም የቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ በተጠቃሾቹ ጣቢያዎች ላይ የተደረገው ምዝገባ እንዲሠረዝ ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱም ሙሉ በሙሉ እንዲቆምና እንዲሁም የጣቢያዎቹ ሠራተኞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ፣ በተጨማሪም ሁሉም የምርጫ ጣቢያው ሠራተኞች እና ግብር-አበሮቻቸው በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በኩል የወንጀል ምርመራ እንዲደረግባቸው የወሠነ ሲሆን፤ የመራጮች ምዝገባውም አዲስ ሠራተኞች ተመልምለው በድጋሚ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል። በቀጣይም ቦርዱ ምዝገባውን ለማከናወን እና ያለፉትን የምዝገባ ቀናት ለማካካስ የሚያስፈልጉትን ተጨማሪ ቀናት እና ምዝገባው እንደገና የሚጀመርበትን ቀን የሚያሳውቅ ይሆናል።
የሕግ ጥሠቶች የተፈጸሙባቸው ጣቢያዎች እና የተፈጸሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ዝርዝር

1. በዎላይታ ዞን ዱቦ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ዱቦ የተፈጸመው ጥሠት፦ አቶ መሰለ ኤሊያስ ከሚባል ግለሰብ ስም ዝርዝር በመቀበል በመራጮች መዝገብ ላይ መመዝገብ፣ በተጨማሪም የቦርዱ ሠራተኛ ላልሆነ አቶ ወልዴ ወራጆ ለተባለ ግለሰብ ቁልፍ በመስጠት ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ማድረግ
2. በዎላይታ ዞን ዶላ ምርጫ ጣቢያ ሦስት ንዑስ ጣቢያ የተፈጸመው ጥሠት፦ አቶ አርጃ አሊሶ ከሚባል ግለሰብ ስም ዝርዝር በመቀበል በመራጮች መዝገብ ላይ መመዝገብ
3. በዎላይታ ዞን ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ቤታሎ ለ የተፈጸመው ጥሠት፦ ግለሰቦች ፊርማ ሳይፈርሙ የመራጭነት ካርድ እንዲወስዱ ማድረግ
4. በዎላይታ ዞን ጫማ ሄምቤቾ ምርጫ ጣቢያ አምስት የተፈጸመው ጥሠት፦ በመዝገቡ ላይ ላልፈረሙ ግለሰቦች ካርድ መስጠት
5. በዎላይታ ዞን ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ወርሙማ ሀ የተፈጸመው ጥሠት፦ ግለሰቦች በግንባር ምርጫ ጣቢያ ሳይቀርቡ እና ሳይፈርሙ መራጮች መዝገብ ላይ መመዝገብ
6. በዎላይታ ዞን ማንቴ ጌራራ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ጌራራ ሦስት የተፈጸመው ጥሠት፦ ግለሰቦች በግንባር ምርጫ ጣቢያ ሳይቀርቡ እና ሳይፈርሙ መራጮች መዝገብ ላይ መመዝገብ
7. በዎላይታ ዞን ቶሜ ጌሬራ ምርጫ ጣቢያ ቶሜ ጌሬራ አራት የተፈጸመው ጥሠት፦ ግለሰቦች በግንባር ምርጫ ጣቢያ ሳይቀርቡ እና ሳይፈርሙ መራጮች መዝገብ ላይ መመዝገብ
8. በዎላይታ ዞን ዋጭጋ ቡሻ ምርጫ ጣቢያ ዋጭጋ ቡሻ 02 የተፈጸመው ጥሠት፦ የመራጮች ፊርማ ሳይፈርሙ ግለሰቦች እንዲመዘገቡ እና ካርድ እንዲወስዱ ማድረግ
9. ጎፋ ዞን ጃዉላ ጎሬ አዳ ምርጫ ጣቢያ የተፈጸመው ጥሠት፦ ተመሳሳይ የሆነ ወይንም በአንድ ሰው የተፈረመ በሚመስል ፊርማ ከአንድ በላይ ካርዶችን ወጪ ማድረግ
10. ጎፋ ዞን ጃዉላ ውጋ መሸተላ ምርጫ ጣቢያ ሀ የተፈጸመው ጥሠት፦ ግለሰቦች የመራጮች መዝገብ ላይ ሳይፈርሙ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ማድረጋቸው ይጠቀሳሉ።
ስለሆነም ቦርዱ በቀጣይም የክትትል ሥራውን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ማንኛውም ተመሳሳይ ተግባራት ሲከናወኑ ያየ ግለሰብ በነፃ ስልክ መስመር 778 ላይ ደውሎ ጥቆማውን ማቅረብ እንደሚችል ቦርዱ ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም.
4.1K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 16:40:59
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከዚህ በፊት ያከናወናቸው ጉባዔና በቀጣይ ማድረግ ስለሚገባው ጉባዔ አስመልክቶ ያሳለፈው ውሣኔና ለፓርቲው ያሳወቀበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።
2.5K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ