Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-16 09:14:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የተወሠኑ ምርጫ ክልሎች ላይ በተያዘው ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት በአማራ ክልል በሮቢት፣ በኤፌሶን፣ በማጀቴ፣ በሞላሌ እና በአርጎባ ልዩ ምርጫ ክልሎች ለሚያካሄደው ምርጫ፤ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በተጠቁሱት አካባቢዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንድታመለከቱ ቦርዱ ይጠይቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• መኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250 በድምሩ፣
• በክልሉ የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ ይመረጣል፣ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረበውን መሥፈርት የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተያያዘውን ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ለስምንት ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።

https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም.
1.9K viewsedited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 17:15:18
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች ( ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ዲራሼ) ላይ ሕዝበ ዉሣኔ ለማካሄድ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር በተያይዘ የቦርዱ የሎጅስቲክ ሥራ ክፍል ሕዝበ ዉሣኔውን በማስፈጸም ለሚሠማሩ ሠራተኞች የሥልጠና ሠነዶችና ቁሳቁሶችን እንዲሁም በሕዝበ ዉሣኔ ቀን በምርጫ ጣቢያ ላይ ለኦፕሬሽን ማስፈጸሚያ የሚያገለገሉ ቁሳቁሶችን፤ ማለትም የድምፅ መስጫ ሣጥን እና የሚሥጥራዊ ድምፅ መስጠት ሂደቱን መከለያ ወደ`ተመረጡ የሕዝበ ዉሣኔ ማስተባበርያ ማዕከላት አሠራጭቷል፡፡
3.0K views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 13:52:43
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መ. ኢ. አ. ድ) ሚያዚያ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ በፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የተካሄደው የፓርቲው የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የተጓደሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እጅ በማውጣት መደረጉ በዐዋጅ አንቀጽ 74(3) መሠረት በየደረጃው ያሉ አመራሮች አመራረጥ ግልጽ፣ ነፃ እና ፍትሐዊ እንዲሁም በሚሥጥር በሚሰጥ ድምፅ የሚመረጡ መሆን እንዳለበት ከሚደነግገው ጋር የተቃረነ በመሆኑ ፓርቲው ሕጉን መሠረት በማድረግ በድጋሚ ጠቅላላ ጉባዔ ሊያካሂድ እንደሚገባ ወሥኗል።

በተጨማሪም በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በዐዋጁ መሠረት ተሻሽለው መቅረብ ያለባቸውን አንቀጾች ቦርዱ የለየ ሲሆን፤ በዚም አግባብ ከሕጉ ጋር የሚቃረኑ የደንቡ አንቀጾች የታገዱና በዐዋጅ 1162/2011 ላይ በዝርዝር የሠፈሩት ድንጋጌዎች በተግባር እንዲፈጸሙ እንዲደረግ፤ እንዲሁም ይህ ውሣኔ ከተገለጸበት ከታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ፤ ይህም ሲሆን በድጋሜ የሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በተከተለ መልኩ መሆን እንዳለበት ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ላይ ያገኙታል፡፡
1.5K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 15:27:54
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አ. ህ. ዴ. ድ/ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ያሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ያሉ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ጋር የሚቃረኑ አንቀጾች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ፤ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔው በቀጣይ ስብሰባው አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርጎ ሪፖርት እንዲያቀርብ የወሠነ ሲሆን፤ ፓርቲው ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ እና የተላለፉ ውሣኔዎችን የመዘገበ መሆኑን ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ላይ ያገኙታል።
3.7K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 13:16:45 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በሶማሌ ክልል (በጅግጅጋ) በሚገኙ ሁለት ምርጫ ክልሎች ለሚከናወነው ጠቅላላ ምርጫ፤ በምርጫ አስፈጻሚነት ለመሥራት ፍላጎት ላላቸው የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች 6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የተወሠኑ የምርጫ ክልሎች ላይ በተያዘው ዓመት ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት በሶማሌ ክልል (በጅግጅጋ) ሁለት በአንድ ምርጫ ክልል ለሚያካሂደው የድጋሚ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም በጅግጅጋ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት “በገለልተኝነት” ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንድታመለከቱ ቦርዱ ይጠይቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• መኖሪያ አድራሻ፦ በጅግጅጋ እና በዙሪያው ወረዳ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ ከ12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250
• በክልሉ የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆን ይመረጣል፤
• የሥራ ቦታ፦ በጅግጅጋ ሁለት ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች እና ምርጫ ጣቢያዎች
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤ ከዚህ በፊት በምርጫ ክልሉ የተሣተፉ አስፈጻሚዎች በዚህኛው ምርጫ ማመልከት አይችሉም።
በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረቡትን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ጅግጅጋ በሚገኘዉ የቦርዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት በመገኘት እንድትመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 04 ቀን 2015 ዓ.ም.
3.8K viewsedited  10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 11:24:41
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተደረጉ ምርጫዎች ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንቡን አስገዳጅ ድንጋጌዎች የተቃረኑ አፈጻጸሞችን ገምግሟል። በተጨማሪም በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በዐዋጁ መሠረት ተሻሽለው መቅረብ ያለባቸውን አንቀጾች ቦርዱ የለየ ሲሆን፤ በዛም አግባብ ፓርቲው ይህ ውሣኔ ከተገለጸበት ከታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በድጋሜ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ፤ ይህም ሲሆን በድጋሜ የሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በተከተለ መልኩ መሆን እንዳለበት ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ላይ ያገኙታል።
3.9K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 17:28:20
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ቦ. ዴ. ፓ) መጋቢት 10 እና 11 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተደረጉ ምርጫዎች ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የሚቃረኑ አፈጻጸሞችን ገምግሟል። በተጨማሪም በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በዐዋጁ መሠረት ተሻሽለው መቅረብ ያለባቸውን አንቀጾች ቦርዱ የለየ ሲሆን፤ በዛም አግባብ ፓርቲው ይህ ውሣኔ ከተገለጸበት ከታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ፤ ይህም ሲሆን በድጋሜ የሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በተከተለ መልኩ መሆን እንዳለበት ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ላይ ያገኙታል።
2.1K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 08:43:58
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ አካላት ዛሬ ሰኞ ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው ሞዛይክ ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

• በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
• የመጡበትን ብዙኃን መገናኛ መታወቂያ መያዝ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም.
2.8K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 14:25:31
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለመዘገብ ከቦርዱ ዕውቅና ላገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ የሚያካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ ለመዘገብ አመልክተው ከቦርዱ ዕውቅና ለተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃን ባሙያዎች ታኅሣሥ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰጠውን ሥልጠና በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ቦርዱ እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚደረገው ሕዝበ ውሣኔ ሦስተኛው እንደሆነ አስታውሰው፤ መገናኛ ብዙኃኑ በሕዝበ ውሣኔው ሂደት በሚሠሯቸው ዘገባዎች ከወገንተኝነትና ከጥቅም ግጭት ነፃ ሆነው ኃቅንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን መሠረት ባደረገ መልኩ መዘገብ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።

ምርጫ በኢትዮጵያ፣ የምርጫ ዓይነቶች እና ባህሪያት፣ የምርጫ ዑደት፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ-ምግባር እና አሠራር መመሪያ ላይ የተቀመጡ የመገናኛ ብዙኃኑ መብትና ግዴታዎችን እንዲሁም ኃቅን ማጣራት፣ የሐሰተኛና የአደናጋሪ ዜናዎች ልዩ ባህሪያት፣ የተዛባ መረጃን የመለያ መንገዶች በሥልጠናው ትኩረት ከተደረገባቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ቦርዱ ሕዝበ ውሣኔውን ለመዘገብ ፍላጎት ላላቸው መገናኛ ብዙኃን ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከሬዲዮ፣ ከቴሌቭዥን፣ ከኅትመትና ከኦንላየን የተውጣጡ 17 መገናኛ ብዙኃን አመልክተው፤ ለ171 ዘጋቢዎቻቸው የዕውቅና ባጅ አግኝተዋል።
2.8K views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 17:43:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 እስከ ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሄድ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን ተከትሎ የመራጮችን መዝገብ ለአምስት ቀናት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ።
ቦርዱ የመራጮችን መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ያደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. (ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳይጨምር) እስከ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው።

የተጠናቀቀው የመራጮች ምዝገባ፤ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ የመራጮች ምዝገባው በተሠረዘባቸውና በቦርዱ ውሣኔ በድጋሜ ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. (ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳይጨምር) እስከ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች አይጨምርም።
243 views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ