Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-18 07:27:39
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ጊዜያዊ ውጤት የማዳመር ሥራ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ አጠናቆ በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል።

ቦርዱ የመጨረሻውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እየሰራ ይገኛል፡፡ ቀደም ሲል ቦርዱ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ የመጨረሻውን በቦርድ የተረጋገጠ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ እንደሚያደርግ የገለፀ ቢሆንም በርከት ያሉ ግድፈቶችና የምርጫ ህግ ጥሰቶች በቦርዱ የምርጫ ክትትል ቡድን እንዲሁም በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ የማጣራት እና ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደበት ግዜ ለማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡

በዚህም የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ስራ የዲራሼ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞ፣ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ውጤቶችን የማጣራትና የማረጋገጥ ስራ ተጠናቆ ውጤታቸው በቦርዱ ፀድቋል። በቀጣይም በቀሪዎቹ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ማለትም በአማሮ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ እና የጎፋ ግዜያዊ ውጤቶች የማጣራትና የማረጋገጥ ሂደት እንደተጠናቀቀ ቦርዱ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በቦርዱ ታይቶ የፀደቀውን ውጤት ለማግኘት ከሥር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
https://nebe.org.et/am/Referendum_Result
1.1K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 16:28:42
ማስታወቂያ: ቦርዱ የሚያካሂደውን የሕዝበ ውሣኔው ጊዜያዊ ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ እንድትታዘቡ ጥሪ ስለማቅረብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ጊዜያዊ ውጤት የማመሳከር ሥራ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ አጠናቆ በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶችን ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ የመጨረሻውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የጀመረ ሲሆን፤ ይህንን የመጨረሻ የሆነውን የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ሥራ ለመታዘብ በቦርዱ ዕውቅና የተሰጣችሁ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች እና በቦርዱ የዘገባ ፍቃድ የተሰጣችሁ የመገናኛ ብዙኃን አካላት እንዲሁም ቦርዱ በድጋሚ ያካሄደውን የቡሌ ምርጫ ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ ለመታዘብ ዕውቅና የተሰጣችሁ የፓርቲ ወኪሎች በሙሉ በማስተባበሪያ ማዕከሉ በመገኘት የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ሂደቱን መታዘብ የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

በቀጣይም ቦርዱ በማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የተጣራውንና በቦርዱ የተረጋገጠውን የመጨረሻው የሕዝበ ውሣኔ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.
1.4K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 18:48:51 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝበ ውሣኔውን ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ማድረግ ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደው የሕዝበ ውሣኔ ድምፅ የመስጠት ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የማዳመር ሥራው ድምፅ በተሰጠባቸው ጣቢያዎች የተከናወነ ሲሆን፤ ውጤቱም ጥር 30 ቀን 2015 ከጠዋት ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎች ለሕዝብ ይፋ ተደርጓል።

የተዳመረና የተመሳከረ ጊዜያዊ ውጤት በልዩ ወረዳ ደረጃ ይፋ ከተደረገባቸው ውስጥ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ እና ባስኬቶ ሲጠቀሱ፤ በዞን ደረጃ ደ’ሞ በኮንሶ ይፋ ተደርጓል። በተጠቀሱት ቦታዎች የጊዜያዊ ውጤቱ የማዳመርና ማመሳከር ሥራው ከጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የተሠራ ነው።
ከላይ በተጠቀሱት ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የምርጫ ቁሳቁሶችና የምርጫ ውጤቶች ወደ ማዕከላት የተሰበሰበ ሲሆን፤ በቡርጂ ልዩ ወረዳም እንዲሁ ውጤት የማዳመር ሥራው በመሥራት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፤ በጌዲኦ እና በጎፋ ዞኖች በማስተባበሪያ ማዕከል ደረጃ የማመሳከር ሥራ ተጠናቆ በዞን ደረጃ ለሕዝበ ውሣኔ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ። በቀጣይም በነዚህ ዞኖች የውጤት ማዳመርና ማመሳከር ሥራው እንደተጠናቀቀ ጊዜያዊ ውጤቶቹ ለሕዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።

ከሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተሰበሰበውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የሚያከናወን ሲሆን፤ ይህም በማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የሚደረገው የመጨረሻ ውጤት የማረጋገጥ ሥራ ሲጠናቀቅ በቦርዱ ፀድቆ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል።
ቦርዱ በድምፅ መስጫው ቀን በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመከናወን ላይ የነበረውን ድምፅ የመስጠት ሂደት የጎበኘ ሲሆን፤ በማዕከል ደረጃም በወላይታና በጨንቻ የተካሄደውን የውጤት ማዳመር ሥራ ጎብኝቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም
2.1K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:38:16
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ በማስፈጸም ያለውን የሕዝበ ውሣኔ ድምፅ መስጠት ሂደትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ አካላት ዛሬ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ በሚገኘው ኃይሌ ሪዞርት ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

• በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
• የቦርዱን የዕውቅና ባጅ ወይም የመጡበትን ብዙኃን መገናኛ መታወቂያ መያዝ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም.
3.9K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:22:56
በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ማዕከል በአርባምንጭ ከተማ የእድገት በር ምርጫ ጣቢያ ኮንሶ ሀ ድምፅ የመስጠት ሂደት በፎቶ
3.6K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 14:45:16
ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ማዕከል፣ ዶይሳ ቀበሌ፣ ዶይሳ ምርጫ ጣቢያ አሻም 01 ድምፅ የመስጠት ሂደት በፎቶ
78 views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 13:59:15 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ እያካሄደ ባለው የሕዝበ ውሣኔ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው መራጮች ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ

ቦርዱ በተለያዩ የመርጫ ጣቢያዎች ላይ እያደረገ ባለው ክትትል መሰረት የደረሰባቸው ግኝቶች እና የወሰዳቸው እርምጃዎች ከስር ተዘርዝረዋል
• 9 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተለያዩ የምርጫ ቁሳቁስ ጉድለት ሪፓርት የተደረገ ሲሆን ይህንኑ ለመቅረፍ በምርጫ ማእከል ደረጃ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል
• 38 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለድምፅ መስጫ ቀን ከተመደቡ ተጨማሪ አስፈፃሚዎች ውስጥ በድምፅ መስጫ ቀን በጣቢያዉ ያልተገኙ በመኖራቸው ቦርዱ ይህንኑ ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ይገኛል
• የድምፅ መስጫ ወረቀት ጉድለት በተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ 11 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ይህንኑ ለመቅረፍ ከዞንና ከወረዳ ማስተባበሪያ ማእከላት በመጠባበቂያ ከተያዘው ላይ እንዲሟላ ተደርጓል

ህግ መተላለፍን በተመለከተ
• ቦርዱ ከሰዓታት በፊት ይፋ ያደረገውን የወላይታ ዞን ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመ የሕግ ጥሠትን ተከትሎ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ፓሊስ ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር 2ህ/6851/71/1 በላከው መረጃ በምርጫ ጣቢያው ላይ ተፈጸመ የተባለው የሕግ ጥሠት ላይ ዕርምጃ መውሰዱን ለቦርዱ አሳውቋል። በዚህም መሠረት የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ መስቀሌ ባሳን እና አቶ አበበ አይዛ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በፓሊስ ኮሚሽኑ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም ቦርዱ በሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ የተቋረጠውን የድምፅ የመስጠት ሂደት እንዲቀጥል ወሥኗል።
• በይርጋ ጨፌ ማስተባበሪያ ማእከል ስር በሚገኘው አዳሜ ምርጫ ጣቢያ ሱኬ ላይ የምርጫ ጣቢያው ሠራተኛ ወደ መራጮች የሚሥጥር ድምፅ መስጫ/መከለያ በመግባትና መራጮች ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ምልክት ሲያደርጉ በማየቱ እንዲሁም በተመሳሳይ ጣቢያ ሌላ የጣቢያ ሰራተኛ የድምጽ መስጫ ወረቀትን መራጮች ወደ ሳጥን ከማስገባታቸው በፊት ተቀብላ ከፍታ ስታይ የተገኘች በመሆኑ በዐዋጁ የተደነገገውን የመራጮች በሚሥጥር ድምፅ የመስጠት መብትን ተላልፈው በመገኘታቸው በተፈፀመው የሕግ ጥሠት ላይ ቦርዱ በጣቢያው ሠራተኞችን ከስራ የማሰናበት ዕርምጃ ወስዷል። በቀጣም ይህን ጣቢያ አስመልቶ ሌሎች እምጃዎች ሲኖሩ ቦርዱ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
• በጋሞ ሰላም በር በዶሞኦ ቀበሌ በዶሞኦ ምርጫ ጣቢያ ወማለ 1 ላይ 17 መራጮች ከቀበሌ ደብዳቤ በማጻፍ ያለምንም የማንነት ማረጋገጫ ሊመርጡ የነበረ በመሆኑ እንዲሁም ከተመዘገቡበት ማንነት ጋር ያልተገናኘ የመታወቂያ ወረቀት እና የድምጽ መስጫ ካርድ ይዘው ወደ’ምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ የመጡ ግለሰቦች ድምጽ እንዳይሰጡ ተደርጓል።
670 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 10:14:26
በቡርጂ፣ ጨንቻ፣ ሰላም በርና በሀመር ምርጫ ማእከል ሎኮፖር ምርጫ ጣቢያ የድምፅ መስጠት ሂደት በፎቶ
1.8K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 09:03:50
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ድምጽ የመስጠት ሂደት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ቦርዱ በተለያዩ የመርጫ ጣቢያዎች ላይ እያደረገ ባለው ክትትል በወላይታ ዞን፣ በበሌ የምርጫ ማዕከል፣ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አረጋግጧል፡፡ በዞኑ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ድምፅ በመስጠት ሂደት ወቅት የቀበሌ አስተዳደር ሀላፊዎች ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ብዛት 105 የሚሆን የግለሰብ ጊዜያዊ መታወቂያዎችን በመያዝ ድምፅ ለመስጠት ለተሰለፋ ዜጎች በማደል ህገ ወጥ ተግባር ላይ በመሰማራታቸው ቦርዱ ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመው የህግ ጥሰት እስኪጣራ ድረስ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወስኗል፡፡ በቀጣይም ቦርዱ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ክትትል የሚያደርግ ሲሆን ተከስተው ሲገኙ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም
2.1K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 08:47:18
2.0K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ