Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-02 12:50:09 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን በሚካሄደው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ የመራጮች ትምህርት ላይ ከሚሣተፉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን በሚካሄደው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔን ምርጫ ላይ የመራጮች ትምህርት ተደራሽነት ላይ ለሚሠሩና በቦርዱ የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገላቸው ሰባት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አካሄደ። ዐላማውን ድጋፍ የሚደረግላቸው ድርጅቶች የሚደረግላቸውን ድጋፍ በምን አግባብ መጠቀም እንዳለባቸው፤ እንዲሁም ከዕቅድ አንጻር አፈጻጸማቸውና የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረባቸውን አስመልክቶ ግልጽ መግባባት ላይ ለመድረስ ያደረገውን ውይይት በንግግር የከፈቱት የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶ/ር አበራ ደገፋ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ቦርዱ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ካስፈፀመባቸው አካባቢዎች የወላይታ ዞን አንዱ እንደሆነ አስታውሰው፤ በዞኑ ላይ በተካሄደው የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ሂደት ላይ ጉልህ የሕግ ጥሠት መፈጸሙን ተከትሎ ውጤቱ እንደተሠረዘና አሁንም ቢሆን የድጋሜ ሕዝበ ውሣኔ ሂደቱ ላይ ተመሳሳይ የሕግ ጥሠት ቢፈጸም፤ የቦርዱ ውሣኔ ከቀደመው የተለየ እንደማይሆን፤ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህ እንዳይሆን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ተግባራቸውን እንዲፈጽሙ አሳስበዋል።

የገንዘብ ድጋፉ ዋና ዓላማ የመራጮች ትምህርቱን የተደራሽነት ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማድረስ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ድርጅቶቹም ይሄንኑ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ፤ የሥራ ሪፖርትም ሲያቀርቡ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በምን መልኩና በምን ያህል ተደራሽ እንዳደረጉ በግልጽ ማስቀመጥ እንደሚጠበቅባቸው፤ ቦርዱም ለዚህም የሚሆን የሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ አዘጋጅቶ እንደሚልክ ተገልጿል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ በዕቅዳቸው መሠረትና የተደረገላቸውን የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም እያንዳንዳቸው የት እና በምን መልኩ የመራጮች ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ እንዳሰቡ የገለጹ ሲሆን፤ ገለጻቸውንም ተከትሎም የድርጅቶቹ ዕቅድ ግልጽና የሚለካ መሆን እንዳለበት፤ ይህም ሲባል የመራጮች ትምህርት ለማስተማር በዕቅድ በያዟቸው ወረዳዎች ውስጥ ያሉትን ልዩ ሥፍራዎችና ተደራሽ የሚደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች በጊዜ መለየት እንዳለባቸው አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የመራጮች ትምህርቱ በሚሰጥበት ወቅት በዞኑ የተካሄደው ሕዝበ ውሣኔ እንዲደገም ያደረጉት ምክንያቶችን በማስታወስ የሕግ ጥሠቶቹ እንዳይደገሙ ዜጎች የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ማድረግ እንደሚያስፈልግ፤ እንዲሁም መራጮች የመራጮች ምዝገባውና ድምፅ የመስጠት ሂደቱ በተመሳሳይ ቀን የሚደረግ መሆኑን ተረድተው በዕለቱ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት መረጃዎቻቸውን በአግባቡ በማስሞላትና በመፈርም ድምፃቸውን መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል።

በውይይቱ መጨረሻም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ በተሰጠው አስተያየት መሠረት ሁሉንም የዞኑ ወረዳዎች በመራጮች ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል፤ በዞኑ ቀድሞ በነበሩት ሰባት ወረዳዎች ወይም በአዲሱ አወቃቀር ባሉት 18 ወረዳዎች እና ስድስት የከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍለው ትምህርቱን ለመስጠት ተስማምተው የውይይቱ ማብቂያ ሆኗል።
8.7K viewsedited  09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 16:16:25
ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዎላይታ ዞን ላይ ለሚያስፈጽመው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ፤ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆናችሁ አመልካቾች፣ ቦርዱ በ6ተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ በምርጫ አስፈጻሚነት ተሳተፋችሁ ድጋሚ ጥሪ የቀረበላችሁ፣ በአዲስ መልክ በኦንላይን ያመለከታችሁ ፣ የጹሁፍ መልእክት በመላክ ያመለከታችሁ፤ በግንባር መጣችሁ ፈተና በመውሰዳቹ እና በመመዝገባችሁ እያመሰገንን በተለያዩ ምክንያቶች መምጣት ላልቻላችሁ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ያመለከታችሁ አመልካቾች ለመጨረሻ ጊዜ ፈተና እና ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 05 እና 06 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ባሉት የስራ ሰዓታት በመሆኑ በእነዚህ ቀናት ስታዲም በሚገኘው ጊዮን ሆቴል ፈተና እንድትወስዱ እያሳሰብን በምትመጡበትም ጊዜ የቀበሌ መታወቂያ እና የባንክ ደብተር ኮፒ ይዛችሁ እንድትመጡ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
6.5K viewsedited  13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:30:24
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ ዐዋጁን መሠረት በማድረግ የመሥራች ጉባዔውን እንዲያከናውን መወሠኑን ያሳወቀበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።
7.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 10:39:59
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ ዐዋጁን መሠረት በማድረግ የመሥራች ጉባዔውን እንዲያከናውን መወሠኑን ያሳወቀበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።
7.6K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 09:32:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው ይነሣልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ ያደረገበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።
7.9K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 09:42:46
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የድጋሚ ህዝብ ውሳኔ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ነው።
በዚሁ መሠረት በዎላይታ ዞን ስር በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ህዝበ ውሳኔ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም የዎላይታ አካባቢ ነዋሪ የሆናችሁ፣ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በዎላይታ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣
• የስራ ቆይታ ፦ ከ8 እስከ 10 ቀን
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ ለ7 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment/
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም.
9.3K viewsedited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 11:59:01
8.6K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 11:58:11
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን የሚካሄደውን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔን ምርጫ በተመለከተ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር ምክክር አካሄደ::
ዝርዝሩን ለማንበብ ከስር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
National Election Board of Ethiopia
10.1K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 16:52:22
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በሚገኘው የዎላይታ ዞን ላይ የሚያካሄደው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የትግበራ አፈጻጸም ዝርዝር ዕቅድ ማሳያ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳ።
8.8K views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 10:28:36
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የድጋሚ ህዝብ ውሳኔ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ነው።
በዚሁ መሠረት በዎላይታ ዞን ስር በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ህዝበ ውሳኔ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆናችሁ፣ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በዎላይታ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣
• የስራ ቆይታ ፦ ከ8 እስከ 10 ቀን
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ ለ5 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment/
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም.
13.7K viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ