Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-05 17:37:39
9.5K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 17:36:28
7.6K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:23:37
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የተለያዩ የሥራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት የNational Democratic Institute (NDI) ሰፋ ያሉ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮችን አስመልክቶ ያሠራውን የህዝብ አስተያየት የዳሰሳ ጥናት (Public Opinion Survey) ግኝቶችን ትላንት ሚያዚያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. አቀረበ። ዝርዝሩን ለማንበብ ከስር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/100066827943709/posts/pfbid0wzBW4sacC4Ls3aAyLRtxhYz74kdJjiyiwfSMXXitWPaxECzbmKLoQPngcivT6suxl/?mibextid=Nif5oz
1.9K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 17:47:17
39 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 17:46:00
77 views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 17:44:35 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዓለም ዐቀፍ የሴቶች ታሪክ ወርን አከበረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓለም ዐቀፍ የሴቶች ታሪክ ወርን አከበረ። የቦርዱ አመራር አባላትን ጨምሮ የቦርዱ ሠራተኞች የተገኙበትን መድረክ በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ቦርዱ የሴቶችን ተሣትፎ ለማረጋገጥ በሕጎቹ ላይ ካኖራቸው አስገዳጅ ድንጋጌዎች በተጨማሪ፤ በተግባር በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተግባራት ላይ የቦርዱ ሴት አመራሮችና ባለሞያዎች በቁጥጥር እንዲሁም በአመራር ሰጪነት ያሳዩት የአፈጻጸም ብቃት ዕኩል ነን ከማለት ባለፈ ዐቅማቸውን በተግባር ያረጋገጠ ጭምር እንደነበር አስታውሰዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ከሆኑት ዘውዴ አበጋዝና አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካዔል ጋር የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በውይይቱም በሴቶች መብት ተሟጋችነትና ባለሞያነት ያካበቱትን የሕይወት ልምዳቸውን፣ የሴቶች ትግል በዘመናት ውስጥ የነበረውን ዓይነተኛ ባህሪያት፣ የተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ስኬቶችና የታለፉት ተግዳሮቶችን አስመልክቶ በዝርዝር ሃሳባቸውን አካፍለዋል።
የፓናል ውይይቱን ተከትሎ ቦርዱን ከሦስት ዓሥርት ዓመታት በላይ ላገለገሉ ሴት ባለሞያዎች የዕውቅና ሠርተፍኬት በዋና ሰብሳቢዋ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን፤ የሕይወት ልምዳቸውንም እንዲሁ እንዲያጋሩ ተደርጓል። በመጨረሻም የቦርዱ የሥርዓተ ፆታና ማኅበራዊ አካታችነት የሥራ ክፍል ቀደም ሲል ይህን መድረክ ታሳቢ አድርጎ ባካሄደው ውድድር አሸናፊ ለሆኑት ሴት የቦርዱ ባለሞያዎች የአጭር ጊዜ ነፃ የትምህርት ዕድል እንዳመቻቸላቸው አስታውቆ የመድረኩ ማብቂያ ሆኗል።
133 views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:38:01
1.9K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:37:57
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካል ጉዳተኛ ሴቶች የአትሌቲክስ ውድድር እና የ2015 ዓ. ም. ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ. ሜ. ሩጫ በፎቶ።
#ቦታዬ፣ #መብቴ፣ #ድምፄ
መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ. ም
1.9K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 11:20:27
2.2K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 17:00:45
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔዎቻቸውን ለማካሄድ እያጋጠሟቸው ያሉትን የሕግ ጥሠቶች አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የላከው ደብዳቤ ከታች ተያይዟል።
2.2K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ