Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-05 18:05:01 ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነገው’ለት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም. በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔው በድምፅ መስጫ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አሠራጭቶ አጠናቀቀ።

ቦርዱ ሥርጭቱን ያከናወነው በ31 ማዕከላት ሥር ባሉ 3,771 ምርጫ ጣቢያዎች ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ብርብርና ቁጫ ላይ የተከፈቱ የተፈናቃይ ጣቢያዎች ናቸው። ሥርጭቱ የተከናወነው ከጥር 25 እስከ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲሆን፤ ምርጫ ጣቢያዎቹም በነገው ዕለት ለሚከናወነው የሕዝበ ውሣኔ የድምፅ መስጠት ሂደት በሙሉ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። ጣቢያዎቹ በነገው ዕለት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ክፍት የሚሆኑ ሲሆን፤ ቦርዱ መራጮች በተጠቀሰው ሰዓት ወደተመዘገቡበት ጣቢያ በመሄድ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ያሳውቃል።
2.3K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 17:01:52
2.5K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 08:01:36
4.5K views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 10:01:40
3.0K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 16:17:12
ማስታወቂያ:- የቡሌ ምርጫ ክልል ድጋሚ ምርጫን ይመለከታል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ጎን ለጎን በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ የድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ በወሠነው መሠረት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ምርጫው በጋራ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ስለሆነም ከዚህ በፊት በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ ለመምረጥ የተመዘገባችሁ ወይንም ምርጫው ላይ የተሣተፋችሁ ግለሰቦች በሙሉ በድጋሚው ምርጫ ላይ እንድትሣተፉ እየጠየቅን፤ በድጋሚ ምርጫው ላይ ለመሣተፍ የሕዝበ ውሣኔው የመራጮች ምዝገባ ላይ የተመዘገባችሁ መሆን የማይጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ሕዝበ ውሣኔው ከድጋሚ ምርጫው ጋር አይገናኝም። በተጨማሪም ድምፅ ወደ’ምትሰጡበት ምርጫ ጣቢያ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ካርድ መያዝ፤ ከዚህ በፊት በምሥክር የተመዘገባችሁ ከሆነ ደ’ሞ የምሥክርነት ሠነዱን መያዝ፤ ሠነዱ በእጃችሁ የማይገኝ ከሆነ ደ’ሞ በዕለቱ ነዋሪነታችሁን የሚያረጋግጡ የቀበሌው ነዋሪዎችን በመያዝ ምርጫውን መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጎን ለጎን በሚካሄዱት ሕዝበ ውሣኔ እና የድጋሚ ምርጫ ላይ በምርጫ አስፈጻሚነት የምትሣተፉ ሠራተኞች፤ ቀደም ሲል በወሰዳችሁት ሥልጠናና በሕጉ መሠረት መራጮችን እንድታስተናግዱ ቦርዱ ያሳውቃል።
2.5K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 15:15:32



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ በፓለቲካ ፓርቲዎች መካከል የተደረገ የክርክር መድረክ
4.0K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 15:28:46
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ያለዎትን ጥያቄ እና አስተያየት፤ በቦርዱ ፌስቡክ ገፅ በአስተያየት መስጫው ላይ ይጻፉልን።

በሚጽፉልን ጥያቄና አስተያየት ላይ መልስ ለመስጠት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ረዕቡ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌስቡክ የቀጥታ ሥርጭት የሚቀርቡ ይሆናል።
https://bit.ly/40eAXN1

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም.
5.2K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 14:26:31
ማስታወቂያ:- የቡሌ ምርጫ ክልል ድጋሚ ምርጫን የሚታዘቡ የፓርቲ ወኪሎችን በተመለከተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ጎን ለጎን በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ የድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ በወሠነው መሠረት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ምርጫው በጋራ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በመሆኑም በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተወዳደራችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ማለትም የብልጽግና ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢ.ዜ.ማ) እና የጌዲኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በምርጫ ክልሉ ምርጫ በሚካሄድባቸው 83 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለሚታዘቡ የፓርቲ ወኪሎች ቦርዱ የታዛቢነት መለያ ባጅ ስለሚያዘጋጅ፤ በእያንዳንዳቸው ጣቢያዎች ላይ አንድ ተቀማጭ ወኪል እንዲሁም በምርጫ ክልል ተንቀሳቅሰው ለሚታዘቡ 10 ተንቀሳቃሽ ወኪሎች ከጥር 24 እስከ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ የታዛቢዎቻችሁን ዝርዝር በመያዝ በቡሌ ማስተባበሪያ ማዕከል በመገኘት በዝርዝሩ መሠረት መለያ ባጅ እንድትወስዱ ቦርዱ ያሳውቃል።
5.7K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:33:52 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲደገም ውሣኔ በተላለፈባቸው ምርጫ ክልሎች ላይ በዚህ ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በምቃንና ማረቆ ሁለት ምርጫ ክልል፣ በአፋር ክልል ደሉል ምርጫ ክልል እንዲሁም በቤኒሻንጉል ክልል መንጌ ምርጫ ክልል ላይ ለሚያካሂደው የድጋሚ ምርጫ፤ ምርጫውን የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም በተጠቁሱት አካባቢዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከጥር 19 እስከ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡‐
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የመኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን በድምሩ 250 ብር
• በክልሉን የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ ይመረጣል፤ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።
በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረበውን መሥፈርት የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከጥር 19 እስከ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 14 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ፡ በእነዚህ ምርጫ ክልሎች የሚካሄደው የድጋሚ ምርጫ በመሆኑ በስድስተኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የተሣተፋችሁ ምርጫ አስፈጻሚዎች ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 19 ቀን 2015 ዓ. ም.
https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment
8.0K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 15:17:23
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያካሄደው የመራጮች ምዝገባ አጠቃላይ አኅዛዊ መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ በ3769 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ ባጠቃላይ 3,028,770 የመራጮች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 493 የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል።

አጠቃላይ የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽ 1,575,371 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 1,453,399 ሴቶች ናቸው። ከተመዘገቡት የአካል ጉዳተኞች ውስጥም እንዲሁ 296 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 197 ሴቶች ናቸው። ከላይ የተመለከቱት አኅዞች ቀደም ሲል ቦርዱ ይፋ ባደረገው ጊዜያዊ የመራጮች ቁጥር ላይ ባለመጠናቀቃቸው ያልተካተቱትን ጣቢያዎች እንዲሁም የድጋሚ ቆጠራ የተደረገባቸውን ጣቢያዎች ጭምር የያዘ ሲሆን፤ ድምር ውጤቱም በማዕከል ደረጃ የመጨረሻ የሚባለው የማረጋገጥ ሥራ የተከናወነበት ነው።

የሪፖርቱን ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ሠንጠረዥ ላይ ያገኙታል።
8.9K viewsedited  12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ