2023-01-17 11:43:49
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ እንዲደገም ውሳኔ በተላለፈባቸው ምርጫ ክልሎች ላይ በዚህ ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ነው።
በዚሁ መሠረት በአማራ ክልል በአዴት፣ አምባሰል፣ ባቲ፣ እስቴ 3፣ መርጦ ለማርያም፣ ራያ ቆቦ ምርጫ ክልሎች ላይ ለሚያካሄደው የድጋሚ ምርጫ፤ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም በተጠቁሱት አካባቢዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከጥር 9 እስከ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም. እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• መኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን በድምሩ 250 ብር፣
• የክልሉን የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ ይመረጣል፤ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተጠቀሱን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከጥር 9 እስከ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት ስምንት ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ማሳሰቢያ፡ በእነዚህ ምርጫ ክልሎች የሚካሄደው የድጋሚ ምርጫ በመሆኑ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሣተፋችሁ ምርጫ አስፈጻሚዎች ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም.
2.8K views08:43