Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-16 14:18:44 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቡሌ ምርጫ ክልል የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ በቀረበ ቅሬታ ላይ የሰጠው መግለጫ

ዝርዝሩን ለማንበብ ከስር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://nebe.org.et/am/node/856
2.7K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 11:45:47
Statement of the National Election Board of Ethiopia
3.0K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 14:45:54
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
1.1K views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 18:19:09
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 74 ንዑስ አንቀጽ 1(ሸ) ላይ በሚደነግገውና የፖለቲካ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባቸውን ቢያንስ በሦስት ዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ አለባቸው የሚለውን ግዴታ ለመፈጸም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ እየገጠማቸው ያለውን መስተጓጎልና አጠቃላይ ሁነቶችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ አካላት ነገ ረዕቡ መጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

• በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
• የቦርዱን የዕውቅና ባጅ ወይም የመጡበትን ብዙኃን መገናኛ መታወቂያ መያዝ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
መጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም
1.5K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:50:12
2.4K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 20:03:56 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ያካሄደው የሕዝበ ውሣኔ አፈፃፀም እና ውጤት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ዝርዝሩን ለማንበብ ከስር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://nebe.org.et/am/Referendum_Result
3.1K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 10:38:11
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ያስፈጸመውን ሕዝበ ውሣኔ አጠቃላይ ሂደት በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ አካላት ረቡዕ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል (የቀድሞ ኢንተርኮንቲነንታል) ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

• በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
• የቦርዱን የዕውቅና ባጅ ወይም የመጡበትን ብዙኃን መገናኛ መታወቂያ መያዝ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም.
2.6K viewsedited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 19:07:50 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወላይታ ዞን ሕዝበ ውሣኔ አፈጻጸምን አስመልክቶ ውሣኔ አሳለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደው ሕዝበ ውሣኔ፤ ከዞኖቹና ከልዩ ወረዳዎቹ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የደረሰውን ጊዜያዊ ውጤቶችን የማመሳከርና የማረጋገጥ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት የተረጋገጡ የ5 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ውጤቶች በቦርዱ ፀድቀው ለሕዝብ ይፋ ሆነዋል።

በሌላ በኩል በወላይታ ዞን የተደረገውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ የሂደቱን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ አዳጋች ሁኔታ የፈጠሩ፤ በምርጫ ሕጉና አግባብነት ባላቸው መመሪያዎች መሠረት እንደ ከባድ የአሠራር ጥሠት የሚቆጠሩ ተግባራት ቁጥራቸው ጥቂት በማይባል የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ተፈጽመው በመገኘታቸው፤ የጥሰቶቹን ስፋት እና የሚሸፍኑዋቸውን ጣቢያዎች በተመለከተ ቦርዱ ተጨማሪ ምርመራ እንዲከወን አዟል፤ የምርመራ ሥራው እንደተጠናቀቀም የመጨረሻውን ውሣኔ በጉዳዩ ላይ እንደሚሰጥም አሳውቋል።

በዞኑ የህዝበ ውሳኔ አፈፃፀም የታዩ ጥሠቶች ዝርዝር፦
I. የመራጮች መዝገብን በተመለከተ

1. በመራጮች ምዝገባ ወቅት በመዝገቡ ላይ የሠፈረው የመራጮች ፊርማ በድምፅ መስጫ ቀን ከተፈረመው ፊርማቸው ጋር የተለያየ መሆን፣
2. በምዝገባ ወቅት በጽሑፍ ፊርማ የተፈረመ በድምፅ መስጫ ቀን በጣት አሻራ የተፈረመ የመራጮች ዝርዝር በመዝገቦቹ ላይ መታየቱ፣
3. በምዝገባ ወቅት በጣት አሻራ የተፈረመ በድምፅ መስጫ ቀን በጽሑፍ ፊርማ የተፈረመ የመራጮች ዝርዝር በመዝገቦች ላይ መታየቱ፣
4. በመራጮች መዝገብ ላይ ለተመዘገቡ የተለያዩ መራጮች (በምዝገባ ወቅትም፣ በድምፅ መስጫ ቀንም) አንድ ዓይነት ፊርማ ተፈርሞ መገኘቱ፣
5. በመራጮች መዝገብ ላይ ከሚጠበቀው በላይ ብዛት ያለው የጣት አሻራ ምልክት (በመራጮች ምዝገባ ወቅትና በድምፅ መስጫ ቀን) የተደረገ መሆኑ፣
6. በመራጮች መዝገብ ላይ የመራጮቹ መረጃ ተሞልተው ፊርማቸው በጽሑፍም ሆነ በአሻራ አለመሥፈሩ፣
7. ከ18-50 ዕድሜ ያላቸውና ማንበብና መጻፍ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ በርካታ መራጮች በአሻራ እንደፈረሙ መታየቱ፣
8. በመራጮች ምዝገባ ቀን በአሻራ ተፈርሞ በድምፅ መስጫ ቀን ፊርማ መፈረም ባለበት ቦታ ላይ የራይት ምልክት መደረጉ፣
9. በመራጮች መዝገብ ላይ ስለመራጮቹ ሊሠፍሩ የሚገቡ የመራጮች መረጃ በአግባቡ አለመሞላታቸው፤

II. የድምፅ አሰጣጥና ውጤትን በተመለከተ

1. ጥርጣሬን በሚፈጥር ሁኔታ በበርካታ ጣቢያዎች በመራጭነት የተመዘገቡና በሕዝበ ውሣኔው ቀን የመረጡ የመራጮች ብዛት ዕኩል ሆኖ መታየት፣
2. የውጤት ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የማይፈቀዱ የዕርምት ሥራዎች መሠራቱና በሠነዶቹ ላይ ከፍተኛ ሥርዝ ድልዝ መታየቱ፣
3. የድምፅ መስጫ ወረቀት ብዛት፤ ከተመዘገቡና ድምፅ ከሰጡ መራጮችና ቁጥር አለመታረቅ፣
4. የውጤት መግለጫ ቅጾችና የመራጮች መዝገብ ላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች ፊርማቸውን በሠነዶቹ ላይ አለማሥፈራቸው፣
5. ብዛት ያላቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በአንድ ላይ ታጥፈው በድምፅ መስጫ ሣጥን ውስጥ ታጭቀው መገኘታቸው፣
6. በድምፅ መስጫ ቀን ድምፅ ለመስጠት ለተሠለፉ መራጮች ጊዜያዊ መታወቂያ ወረቀት በአካባቢ አሰተዳደር አካላት መታደል ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም
2.2K viewsedited  16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 18:44:06
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ በቦርዱ ታይቶ የጸደቀውን የጋሞ፣ ጌዴኦ እና የጎፋ ዞኖችን ውጤት ለማግኘት ከሥር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
https://nebe.org.et/am/Referendum_Result
2.2K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 13:12:25
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ) ላይ ያካሄደው የሕዝበ ውሣኔ በቦርዱ ታይቶ የጸደቀውን የአማሮ ልዩ ወረዳ ውጤት ለማግኘት ከሥር የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

https://nebe.org.et/am/Referendum_Result
2.0K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ