Get Mystery Box with random crypto!

አዋጅ – Awaje News

የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የሰርጥ አድራሻ: @na_le_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 190
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/awajenews

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-14 11:53:07
እናት ለዘላለም ትኑር!

መልካም የእናቶች ቀን!
May 14 mother's day

የእናቶች ቀን እናቶችን፣ እናትነትን እና እናቶች በህብረተሰቡ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ የምናስብበት ቀን ነው። ዘመናዊው የእናቶች ቀን የተከበረው በ1908 እ.ኤ.አ. ነበር።

መነሻው ጃርቪስ የተባለች ሴት እናቷን ለመዘከር ባዘጋጀቸው ዝግጅት ሲሆን ጃርቪስ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የእናቶች ቀን በአሜሪካ እንዲታወቅ እና እንዲከበር የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ማድረግ ጀመረች። ከ6 አመት በኋላ ውጤቱ ሰምሮላት በ1914 በዓሉ መከበር እንደጀመረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ::

   ክብር ለእናቶቻችን
25 viewsNa le Tofek, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:59:37 Channel name was changed to «አዋጅ – Awaje News»
07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:58:47 Channel photo updated
07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:56:00
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም በ80 ዓመቷ ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡


https://t.me/awajenews
34 viewsNa le Tofek, edited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 16:42:45
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኢትዮሪካ የተሰኘ አዲስ አልበም ሊለቅ ነው

በቅርብ ቀን የሚወጣው የተወዳጁ የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)  ''ኢትዮሪካ'' አልበም በሰዋሰው መተግበሪያ እንደሚለቀቅ ተገልጿል።

"ኢትዮሪካ" አልበም.......
36 viewsNa le Tofek, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:03:33 ብዙ ሰዎች ለአካላዊ ጤናቸው ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በአመት ሁለት ጊዜ የህክምና ክትትል (ቼክ አፕ) ያደርጋሉ፤ እንዲህ አይነት ልምድ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን የሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉቀት፣ ጨጓራ፣ ጥርስና የመሳሰሉ አካላት ደህንነት ብቻ የጤናማነት ምልክት ሊሆን አይችልም።

የአለም ጤና ድርጅት ጤና ለሚለው ቃል ትርጉም ሲሰጥ ጤንነት ማለት "ሙሉ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ማሕበራዊ ደህንነት ነው እንጂ አለመታመም ብቻ አይደለም" ይላልና።
WHO defines health as well-being, “a state of complete physical, mental and social well- being and not merely the absence of disease or infirmity”.

ለመሆኑ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

አንድ ሰው የአዕምሮ ጤንነት አለው የምንለው ግለሰቡ ያልተዛነፈ አስተሳሰብ፣ ባሕርይና ስሜት ሲኖረው እንዲሁም ከማሕበረሰቡ ጋር ተቀላቅሎና በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ መኖር ሲችል ነው። እስቲ በዝርዝር እንመልከታቸው፦

ሀ) የአስተሳሰብ ጤንነት (cognitive health)

ጥሩ የማሰብ፣ የማስታወስ (memory)፣ የማሰላሰል፣ ፍሰት ያለው ሀሳብ የማፍለቅ፣ የትኩረት፣ የማቀድ፣ ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ችሎታዎች  የአስተሳሰብ ጤንነትን ያመላክታሉ።

ለ) የስሜት ደህንነት (emotional well-being)

አንድ ሰው የስሜት ጤንነት አለው ለማለት በብዛት በቀን ውስጥ የሚያስተናግዳቸውን ስሜቶች ማወቅ አስፈላጊ ነው። በብዛት ከአሉታዊ ስሜቶች (ለምሳሌ ንዴት፣ ጥላቻ፣ ፍርሃት፣ ቂም...ወዘተ) ይልቅ አዎንታዊ ስሜቶችን (ለምሳሌ ፍቅር፣ መገረም፣ ተስፋና ደስታ) የሚያስተናግድ መሆን አለበት።

ሐ) ጤናማ የህይወት ዘይቤ (Healthy life style)
አንድ ግለሰብ ሰናይ ባሕርያት አሉት የምንለው የሚያደርጋቸውን ነገሮች (አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አነጋገር...ወዘተ) ተመልክተን ነው። ለምሳሌ በብዛት አትክልትና ፍራፍሬ ይመገባል፣ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ ሰው ይረዳል፣ አይሳደብም፣ አልኮል አይጠጣም፣ አይቅምም፣ አያጨስም፣ ነውጠኛ አይደለም...ወዘተ።

መ) ማሕበራዊ ደህንነት (social well-being)
ጥሩ አስተሳሰብ፣ አካላዊ ጤንነት፣ አዎንታዊ ስሜትና የሕይወት ዘይቤ አንድን ሰው ጤናማ ነው ለማለት መሉ መስፈርት አይሆኑም። ያ ሰው ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖር፣ ሀሳቡን ማስረዳት፣ የሌሎችም ሀሳብ መረዳት በጠቅላላው ከሌሎች ጋር በጥሩ ሁኔታ አብሮ መኖር አስፈላጊ ነው።

መደምደሚያ

ጤንነት አካላዊ ደህንነት እንዲሁም አለመታመም ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ጤናማ የባሕርይ እና የአዕምሮ ጤንነታችንን መጠበቅ አለብን
75 viewsNa le Tofek, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:03:23
55 viewsNa le Tofek, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 17:40:55

83 viewsNa le Tofek, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:35:57 #ኢድ_ሙባረክ_ኩሉ_አሚን_ወአንቱን_ቢኸይር
28 viewsNa le Tofek, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 21:23:16 ከጉግል ውጭ መጠቀም የምንችላቸው ‘የመረጃ ማሰሻዎች’ እንዳሉ ያውቃሉ?

በአንድ ቀን ስንት ጊዜ ‘ጉግል’ ያደርጋሉ? ጉግል በእያንዳንዱ ሰከንድ 63 ሺህ ጥያቄዎች እንደሚጠየቅ በገጹ ጽፏል። በቀን ውስጥ ወደ 5.6 ቢሊዮን ገደማ ጥያቄዎች ያስተናግዳል።

ብዙዎቻችን ከቃላት ትርጉም አንስቶ ስለማንኛውም ጉዳይ ‘አማካሪያችን’ ጉግል ከሆነ ቆይቷል።

የመረጃ ደኅንነት ባለሙያዎች ግን ጉግል መረጃ ሲሰጠን በምላሹ የእኛን መረጃ እየወሰደ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

የእኛን ማንነት፣ ምን እንደምንወድ፣ ምን እንደምንጠላ፣ ምን ማድረግ እንደምንፈልግ፣ ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት እንደምንችል፣ የት መሄድ እንደምናዘወትር ወዘተ ይመዘግባል።

ስለእኛ የሚከማቸው የተደራጀ መረጃ ለማስታወቂያ ድርጅቶች ወይም የተለያየ ምርት ለሚሸጡ ተቋሞች ይሸጣል።

መረጃው የሚሰበሰበው የኢሜይል መገልገያውን ጂሜይልን እና ዩቲዩብን ጨምሮ ከሁሉም ከጉግል ጋር የተያያዙ ገጾች ነው።

ይህ መረጃ፣ የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች በፍላጎታቸው፣ በዘራቸው፣ በዕድሜያቸው፣ በጾታቸው እንዲሁም በሌሎች የማንነት መገለጫዎቻቸው ልክ የተሰፋ ማስታወቂያ (targeted ad) ሰለባ እንዲሆኑ ያደርጋል የሚለው አንደኛው ትችት ነው።

ሁለተኛው ደግሞ የግል መረጃ ለሦስተኛ ወገን ከተላለፈ በኋላ ሰዎች የት እንዳሉ፣ ከማን ጋር ምን እንደተነጋገሩ፣ ምን እንደሸመቱ እና ሌሎችም መረጃዎች በምስጢር አለመያዛቸው ነው።

ትችቶቹ የሚሰነዘሩት ጉግል ላይ ብቻ አይደለም። ሌሎች መረጃ ማሰሻ (search engine) አቅራቢዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች ላይም ነው።

ጉግል ግንባር ቀደሙ እና በርካታ ተጠቃሚ ያለው መረጃ ማሰሻ ስለሆነ ነው በትችቱ በዋነኛነት የሚነሳው።

ጉግል ከግል መረጃ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ የሚሰነዘርበትን ወቀሳ ተከትሎ ‘የተሻለ አማራጭ አለን’ የሚሉ ሌሎች መረጃ ማሰሻ አቅራቢዎች ወደ ገበያው ገብተዋል። እነሱስ ምን ያህል ይታመናሉ? ሌላ ጥያቄ ነው።

ባለንበት ፈጣን የመረጃ ዘመን የግል መረጃን ምን ያህል ምስጢራዊ አድርጎ መቀጠል ይቻላል? የሚለው አጠያያቂ ነው። ቢያንስ ግን የግል መረጃችንን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በተሻለ ደረጃ የሚጠብቁ ከጉግል ውጭ ያሉ መረጃ ማሰሻዎችን በዚህ ዘገባ እንመለከታለን።

ስለ አማራጭ መረጃ ማሰሻዎች እንዲነግረን የጠየቅነው የአይኮግ ላብስ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ ጌትነት አሰፋን ነው። ከ200 በላይ ፕሮግራመሮች ያለው ተቋሙ ላለፉት አሥር ዓመታት ሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) እንዲሁም ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ይሠራል።
42 viewsNa le Tofek, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ