Get Mystery Box with random crypto!

አዋጅ – Awaje News

የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የሰርጥ አድራሻ: @na_le_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 190
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/awajenews

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-03 06:57:23 የሰሜን ዕዝ ሰማዕታትን በመዘከር ታሪካዊ አደራችንን እንወጣለን!!

ኢትዮጵያ በዘመኗ በርካታ ህልውናዋን የሚጋፉ እብሪት የወጠራቸው ሀገራት ወረራ ፈፅመው ጥቅምና ፍላጎታቸውን ለመጫን ተፈታትነዋታል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ጀግና መውለድ ታውቅበታለችና ጀግኖች ልጆቿ ጠላቶቿን በጦርና በጋሻ ተፋልመው እንደአመጣጣቸው በመመለስ ሉአላዊት ሀገር አስረክበውናል።

አሸባሪው ህወሓት ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ለ27 አመታት እንደፈለገ በህዝብ ሰብዓዊ መብቶች ላይ ሲረማመድ ቆይቶ ሀገሪቱን ለውድቀት የዳረገ ዘረፋ በማካሔዱና በዚህ ጦስ የነበረውን የፌዴራል መንግስት ሥልጣን በማጣቱ ገና በለውጡ ጅማሬ የህወሓት አመራሮች ሀገራዊ ለውጡን ማጥላላትን ሥራዬ ብለው ተያያዙት።

የሰሜን ዕዝ ሠራዊት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ መቀመጫውን በትግራይ ክልል አድርጎ ከትግራይ ህዝብ ጋር እድሜ ልኩን የኖረ ሠራዊት ነው። ዕዙ በሰውና በመሣሪያ የመከላከያን ከፍተኛ ድርሻ የያዘ የተቋሙ ግዙፍ ኃይል ነበር። ወቅቱ መኸር በመሆኑ ሠራዊቱ የአርሶ አደሩን ሰብል መሰብሰብ እና በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ በማባረር ውሎ አዳሩን ከትግራይ ገበሬ ጋር አድርጓል።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ህወሓት ከሰው ልጅ በማይጠበቅ ጭካኔና በአለም መድረክ ባልታዬ ክህደት ለዘመናት በቀበሮ ጉድጓድ እየኖረ ሲጠብቀው የኖረውን የሰሜን ዕዝ ሠራዊት በተኛበት ጥቃት ከፈተበት። ሀገር እንጠብቅ ህዝብ እናገልግል ያሉ፤ ቀን ገበሬ ሌሊት ጥበቃ ሆነው ለበርካታ አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ፣ ቀን ሀሩሩ ሌሊት ብርዱ ሳይበግራቸው፣ ክረምት ከበጋ የሚለፉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በህወሓት የክህደት በትር ሀገር አማን ብለው በተኙበት ተወጉ።

በዚያ ጥቃት ብዙዎቹ የሰሜን ዕዝ አባላት በግፈኛው የህወሓት ጥቃት ተገደሉ። በቅጡ እንኳ ሳይቀበሩ ጅብና አሞራ በላቸው። በሬሳቸው ላይ ከበሮ እየደለቁ ጨፈሩበት፡፡ ብዙዎቹ እየቆሰሉ አካላቸውን አጡ። እንዲሁም ታፍነው በርሐብና ውኃ ጥም እየተቀጡ ተንገላቱ። እነኝህ ታፋኝ የሰሜን ዕዝ አባላት በግፈኞች ዱላ ተደበደቡ። ተገደሉ። ሴት የሠራዊቱ አባላት በጉልበተኞች ተደፈሩ።

ህወሓት ምንም እንኳ የሰሜን ዕዝን ሲያጠቃ በብሔር እየመረጠ በርካታ ጓዶችን ይግደል እንጂ በወቅቱ "የራሴ" ለሚላቸው የትግራይ ተወላጆች እንኳ ከመጨከን ወደ ኃላ አላለም። የሰሜን ዕዝን በሚያጠቃበት ወቅት ለሴራው ያልተባበሩትን በርካታ የትግራይ ተወላጅ የሰሜን ዕዝ ሠራዊት አመራሮችንና አባላትን ገድሎ የጭካኔውን ጥግ አሳይቶናል።

የሰሜን ዕዝ አባላት ትምህርት ቤት ሠርተው ህፃናት ይማሩ ባሉ፣ ጤና ጣቢያ ሠርተው የእናቶችንና የህፃናትን ሞት እንቀንስ ባሉ፤ የውኃ ጉድጓድ ቆፍረው እናቶችን ከሸክም በገላገሉ የተከፈላቸው ወሮታ የግፈኛው ህወሓት ጥይት ሆነ።

ህወሓት ከሃያ አመታት በላይ ትግራይ ክልል እየኖረ ከአነስተኛ ደመወዙ ቀንሶ ገንዘብ አዋጥቶ፣ እጁና ትክሻው እስኪላጥ ድንጋይ ፈልጦና ተሸክሞ ትምህርት ቤት፣ ጤና ኬላ፣ የወጣቶች መዝናኛ የገነባ፤ የክረምቱን ጭቃ ሳይጠየፍ የአርሶ አደሩን ሰብል ሲኮተኩት እና ሲያርም ከርሞ፤ ጠዋት ብርዱን ቀን ፀሐዩን ሳይፈራ የደረሰውን ሰብል ሲያጭድ እና ሲወቃ፤ ምሽግ ውስጥ እየኖረ የጠበቀውን፣ የሞተለትንና የቆሰለለትን የሰሜን ዕዝ ሠራዊትን ክዶ የወጋ የጭካኔና የክህደት ጥግ መታወቂያው የሆነ የማፍያዎች ጥርቅም ነው።

አሸባሪው ህወሓት የጥቅምት 24ቱ የሰሜን ዕዝ የክህደት ጥቃት አልበቃው ብሎ ለሌላ ጦርነት ከመሰለፍ ወደ ኃላ አላለም። በ2013 ዓ.ም ሰኔ ወር መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አድርጎ ሠራዊቱን ከትግራይ ባስወጣበት ወቅት በየበርሃው ተበታትኖ የነበረውን ታጣቂውን አሰባስቦ የአፋርና አማራ ክልሎችን በስፋት ወረረ። በዚህ ወረራ ወቅትም አመራሮቹ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ መሔድ ካለባቸው እንደሚሔዱ እየማሉ ተናገሩ።

በአማራና አፋር ክልሎች ምንም የማያውቁ ንፁሀን ላይ ከባድ መሣሪያ በመተኮስ እና በጅምላ በመረሸን የጥፋት መሐላቸውን በተግባር አሳዩን። ጭና፣ ጋሊኮማ፣ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ያለርህራሔ ንፁሀን ዜጎችን በጅምላ ገደሉ። ከትልልቅ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እስከ የገበሬው ቤት ድረስ ዘረፉ፤ አወደሙ፤ አቃጠሉ። የአርሶ አደሩን ሰብል አጭደውና ወቅተው ከመውሰድ እስከ በእሳት ማቃጠል የደረሰ ጉዳት አደረሱ። ህሊናቸውን የሸጡ ህወሓታዊያን ከመነኩሴ እስከ ህፃናት ያሉ ሴቶችን አስገድደው ደፈሩ።

የጀመሩት ወረራ በጀግናው ሠራዊታችን ጠንካራ ምት ተፈረካክሶ ከአፋርና አማራ ክልል ተጠራርገው ሲወጡ መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርጎ ባለበት ሰአት ነሐሴ 18 ቀን ሦስተኛ ወረራ ከፈቱ።

ደብተር ይዘው ትምህርት ቤት መሔድ ከነበረባቸው ህፃናት እስከ መነኩሴ ድረስ በግድ ወደ ግንባር በማምጣት የትግራይን ህዝብ ለጥይት ማብረጃነት ተጠቀሙበት፡፡ ህወሓት ከሀገር ውስጥ ባንዳዎች እስከ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመተባበር ወረራ ቢከፍትም የብርቱውን ሠራዊታችንን ክንድ መቋቋም አልቻለም። ትንሽ ድል ሲያገኝ የሚፎክረው፤ ሲሸነፍ ደግሞ የሚያለቅሰው ህወሓት ከኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፈው ከፍተኛ ሀብት የውጭ ሀገር ሰዎችን (ሎቢስት) ቀጥሮ ፕሮፓጋንዳ ቢያስነዛም ውጤቱ ኪሳራ ሆኖበታል።

ይህን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮውን ለማሳካትም አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ ደግሞ በድርድር ጊዜ ሸምቶ ለማገገም ያለመታከት እየሠራ ይገኛል። ግን እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን። በየትኛውም ግንባር እንፈተናለን እንጂ ፈፅሞ አንሸነፍም።

ምንም እንኳ አሸባሪው ህወሓት ቀደም ብሎ በሰሜን ዕዝ ላይ ቀጥሎም በመላው ኢትዮጵያ ላይ የፈፀመው ጥቃትና ወረራ መዘዙ እስከዛሬ ድረስ ዘልቆ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እንዲሁም አለም አቀፍ ጫና ያስከተለ ቢሆንም ሁሉንም በአሸናፊነትና ድል እየተወጣን እንገኛለን።

ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን ባደረግነው ታላቅ ተጋድሎ ህወሓት ራሱ በለኮሰው ጦርነት ሊጠፋ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል፡፡ የሰማዕታቱን ፍሬ የምናይበትና ድሉን የምንዘክርበት ወቅት ላይ ነን።

እኛ አደራ የምንዘነጋ ሳንሆን የወንድሞቻችንን፣ የኢትዮጵያን ክብርና የግዛት አንድነት የማስጠበቅ ተጋድሎ ከዳር ለማድረስ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት በጀግንነት ለመክፈል የተዘጋጀን ነን።

አሸባሪው ህወሓት የፈፀመብን በደልና ሰቆቃ ተቆጥሮ የማያልቅ በታሪክና ትውልድ ፊት ይቅርታ የማይቸረው ነው፡፡ በወንድሞቻችን ላይ የደረሰውን ግፍና መከራም መቼም አንረሳውም፡፡ ነገር ግን እኛ እንደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኃይል ህዝብና ሀገርን አፅንተን የምናስቀጥል ህዝባዊ ሠራዊት ነን፡፡

ስለሆነም በደልን ስንቆጥር የምንኖር ሳንሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም የትግራይን ህዝብ ከህወሓት የዘመናት ባርነትና ጭቆና ነፃ ለማውጣት የከፈልነውንና እየከፈልን ያለነውን መስዋዕትነት አጠናክረን በመቀጠል የመጨረሻው የድል ዋዜማ ላይ ሆነን ሰማዕታትን እየዘከርን ኢትዮጵያችንን አስከብረን በአሸባሪው ህወሓት መቃብር ላይ ድላችንን እናበስራለን።

"ጥቅምት 24 መቼም አንረሳውም!!"

ክብርና ሞገስ ለተሰው ሰማዕታት!!
48 viewsNa le Tofek, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 22:10:30
57 viewsNa le Tofek, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 15:07:19
ሳክስ ከነሙሉ ክብሩ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ጋር አይደል እንዴ ያለው ወገን?!

"የንግስቲቱን ህልፈት ተከትሎ፣ የገነት በሮች ተከፍተው ብርሃናቸው በንግስቲቱ አስክሬን ላይ እያንፀባረቀ ነው " እያለን ነው Daily Mail የተሰኘው ታዋቂ ሚዲያቸው!
68 viewsNa le Tofek, 12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 22:55:38
ለማንኛውም የህወሓት ወያኔ ሽብር ሰነዱ እጄ ገብቷል እጅግ ብዙ ስለህነ ክፍል 1 2 3 ... እያልኩኝ እለቅልችኃለሁ:: ዝርክርኮች
107 viewsNa le Tofek, 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 10:40:56 መግቢያ

አምናና ታች አምና ለዐሥሩ ጣቶቼ ሥራ አልነበራቸውም፡፡ ለእኒህ ጣቶቼ ሥራ ፍሊጋ ደጋ ስወጣ፤ ቆላ ስወርድ ከዓመታት በፊት ነበልባል የሚባል የቅኔ ዘራፊ

በቅኔያችን ጥበብ በያዝነው ሆሣዕና፣

እንነጠቃለን በግዙፍ ደመና

ከሚለው ቅኔ “ጥበብ ተቀብራለች” ብሎ የነገረኝ ትዝ አለኝ፡፡ ቅኔዉን ከልጅነቴ ጀምሮ እኔም አውቀዋለሁ፡፡ የሊቁ ክፍለ-ዮሐንስ መወድስ ነው፡፡ ሊቁ ክፍሉዮሐንስ በዘመኑ ባንዲት ዕለት፣ በተመሳሳይ ሰዓት በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴና በሸዋ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቅኔማኅሌት ሲያገለግል ይውል ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የሸዋ ሊቃውንት ሊቁ ክፍለ-ዮሐንስ ከእነሱ ጋር በመንፈሳዊ አገልግሎት እንደ ዋለ በኩራት ሲናገሩ የጎንደር ሊቃውንት ደግሞ በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ እንደ ልማዱ አዳፋ ልብሱን ለብሶ ቅኔውን ሲገጨው መዋሉን ይናገራሉ፡፡ ባለ ቅኔዉ በተመሳሳይ ሰዓት ጎንደርና ደብረ ብርሃን ሥላሴ በመንፈሳዊ አገልግሎት ስለማሳለፉ ሲጠየቅ፡

ንሕነሂ በግብረ ቅኔ ዘበሆሣዕና፣

እምእደ ገፋዒ ወተገፋዒ ንትመሰጥ በደመና ሊል በመወድሱ መለሰ።

ቅኔው ከላይ ከላይ ሲተረጎም:

‹ብቅኔያችን ጥበብ በያዝነው ሆሣዕና፣

እንነጠቃለን በግዙፍ ደመና እንደ ማለት ነው። ነበልባል እንደ ነገረኝ በዚህ ቅኔ ውስጥ ጥበብ ተቀብራለች

ነበልባል ሌላም ተመሳሳይ ታሪክ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር።

“ከኢትዮጵያውያን ጠቢባን ሌላው ደግሞ ተዋነይ ይባል ነበር። ጠቢቡ ተዋነይ ከጎጃም ቅኔ ተቀኝቶ በተመሳሳይ ሰዓት ጎንደር ይደግም እንደ ነበር ዜና-ጥበቡ ይጠቁማል፡፡ ይህንን የኢትዮጵያ ዕፁብ ድንቅ ጥበብ የቅኔ ሊቃውንት በኩራት ይናገሩታል።

ባላገሮችም

‹‹ተዋነይ በጣና

ይመስላል ደመና ሲሉ ተዋነይ በደመና መጋለቡን ይተርካሉ” ብሎኛል ነበልባል፡

ነበልባል የነገረኝን ምሥጢር ለዐሥሩ ጣቶቼ ነገርኋቸው፡፡ ሥራ እንደ ፈጠርሁላቸው ቆጠሩት፡፡ ከዘመናት በፊት የነበረውን ሀገራዊ ፍልስፍና እየተሻሙ መክተብ ጀመሩ፡፡ ባለ ቅኔው ክፍለ ዮሐንስ መጣ፡፡ ተዋነይ ተገለጠ። ሌሎችም ሊቃውንት በየተራ መጡ፡፡ አሥሩ ጣቶቼ በቅኔው ውስጥ የተቀበረውን ምሥጢር ሀገርኛ ብዕር ጨብጠው መክተብ

ሲጀምሩ ጠቢቡ ሖረ ኩራዝ ለኮሱ፡፡ ወዲያው ግን ነፋስ በቤቱ ቀዳዳ ገብቶ አጠፋባቸው፡፡ ሊቅ ዐዕቁ ሐሽማል የሚባል በጨለማ ውስጥ ቀይ ብርሃን የሚፈነጥቅ መጽሐፍ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ሐሽማል ድቅድቁን ጨለማ ገፈፈው፡፡ ዐሥሩ ጣቶቼ ሲከትቡ እኔን እንቅልፍ ጣለኝ፡፡ ስነቃ ጠቢቡ ሖረ | ተሰውረዋል። ሊቅ ዐፅቁም ሐሽማልን ይዘው ከቤት ወጥተዋል፡፡ ዐሥሩ ጣቶቼ አንድ መጽሐፍ ጽፈዉ ስለ ስሙ ሲጨቃጨቁ ደረስሁ፡፡ ስሙን ሐሽማል በሉት አልኋቸው፡፡ ሐሽማል ብለው ጠሩት፡፡ እነሆ ሐሽማል ሆነ!!

ማዕበል ፈጠነ
56 viewsNa le Tofek, 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 10:40:53
46 viewsNa le Tofek, 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:24:54 እንዴት ነው ሀገሬ ወሎ ገራገሩ የሚመጀኑበት አድባሩ ደብሩ
ከቅቤው ከማሩ ከሸቱ ቀምሸ ናፍቆት ሱስ ሆኖብኝ ሲያከንፈኝ አመሸ

ይህን የሙዚቃ ስንኝ አድምጦ የልብ ምቱ የማይጨምር ኢትዮጵዊ ይኖራል ብዬ ላፍታም አልጠራጠርም ወሎ የአማራ ድምቀት ውበትና ኩራት የደግነቱ ማሳያ የዕምነቱ ማሰሪያ እንደሆነ ድፍን ጎንደሬ ጎጃምና ሸዋ የሚመሰክርለት በአማራነት ገመድ የተገመደ ማንነት ያለው እንደሆነ ድፍን ኢትዮጵያን ይመሰክራሉ፡፡
ዛሬ አወቅና ባዮች ዘመን ጊዜ የሰጣቸው ምራቃቸውን በወጉ ወዋጥ ያልጀመሩ ጉርባዎች እንዳሻቸው ተነስተው ከሚወደውና ከማይደራደርበት ወንድም እህቱ ሊነጥሉት #ክልል በሚል ስድብ ሰድበው በንቀት አይናቸው ተመልክተው የቡና መጠጫ አደረጉት እውነት ይህን ስንሰማ ይህን ስንመለከት ከዘፋኙ ስንኝ ተዋስኩ

አከራረምሽን እኔ አልጠይቅሽም
ቦርከና እምባዬ ነው ነግሮኛል አይዋሽም

አይደል ያለው ዘፋኙ እንደው ላፍታ ቀያችን በጠላት ቢደፈር የተራራቅን ችላ የተባባልን መሰላቸውና እንዳሻቸው ሊለያዩን ሴራ አሴብን ያም አልሆን አለ ብዙ ሁነን እንደ አንድ ቆምን ታየናቸው ለዚህም ነው የንዴት ስካር አናታቸው ላይ ወጥቶ #ክልል የሚል ስድብ ሰድበው ወሎን ሊያስከፉት ሽር ጉድ የሚሉት ያሳዝናል
ጦሳን ወጣሁ ወረድኩ ሀረጎንም ዞርኩት
እምባ ተናነቀኝ እኔም ተናነኩት
እኔን እናታለም እኔን እናንዋ
የኔ ደግ እንስፍስፍ የኔ ገራም ጨዋ
የወሎ ሸህ ሁሴን ያጠሩትን አጥር
ማንም አያፈርሰው ያም ቢጥር ያም ቢጥር

ተብሎ ማደል የተዜመው በቃ ዱብ እንቅ ብትሉ ወሎ አማራ ነው ነብር ዥጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን አይቀይሩትም


የወሎ ህዝብ በአማራነቱም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም ! አንድነቱን ለማጥፋት ፣ወግ ባህሉን ለመበረዝ፣እሴቱን ለመሸርሸር ሌት ከቀን የምትደክሙ ባለበጀቶች እባካችሁ ሌላ አጀንዳ ፈልጉ !!

@Na Le Ethiopia
59 viewsNa le Tofek, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:24:54
56 viewsNa le Tofek, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ