Get Mystery Box with random crypto!

አዋጅ – Awaje News

የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የቴሌግራም ቻናል አርማ na_le_eth — አዋጅ – Awaje News
የሰርጥ አድራሻ: @na_le_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 190
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/awajenews

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-08-11 07:51:34 #መጀመሪያ_ይሙቀኝና_ማገዶውን_እጨምራለው!

“መጀመሪያ ይሙቀኛና ማገዶውን እጨምራለው ” የአብዛኛዎቻችን ሰዎች የህይወት መርህ ነው። ማገዶ ከሌለው ጓዳችን ውስጥ ሙቀት የምንጠብቀው ምን ከምን እንደሚቀድም ስለማናውቅ ነው።

ይህ አለማወቃችን ነው ያሰብናቸው ነገሮች እንዳይሳኩ፤ የጠበቅናቸው ነገሮች እውን እንዳይሆኑ የሚያደርገው። በቂ ማገዶ ሳንጨምር ሙቀት ልናገኝ አንችልም።

የቀዘቀዘው ኑሮዋችን እንዲሞቅ ከፈለግን በርከት ያለ ማገዶ መማገድ አለብን። ብዙዎቻችን ግን የሚጠበቅብንን ነገር ሳናደርግ፤ ማለትም ማገዶዋችንን ሳናሰናዳ የቀዘቀዘው ቤታችን እንዲሞቅ እንጠብቃለን። ሲበዛ የዋሆች ስለሆንን።

የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን ልንከፍለው የሚገባ ዋጋ አለ። መክፈል ያለብንን መስዋትነት ሳንከፍል ህልማችን እንደ አስማት በደቂቃ እውን እንዲሆን የምንጠብቅ ከሆነ ጊዜያችንን እያባከንን ነው።

አለመታደል ሆኖ ሰዎች የስኬት ጫፍ ላይ ሲደርሱ፤ ለብቻቸው የከፈሉትን ስቃይ፤ ማንም ሳያያቸው የደከሙትን ልፋት፤ ማንም ሳያመሰግናቸው ያፈሰሱትን ላብ የሚረዳ የለም።

ቶኒ ሮቢንስ የተባለ ጸሃፊ አንድ ደስ የሚል አባባል አለው “ሰዎች በአደባባይ የሚሸለሙት ለብቻቸው ለዘመናት ላፈሰሱት ጉልበት ነው” ይላል። እውነት ነው፤ እንደው በደፈናው ካየነው ከሰዎች ስኬት ጀርባ ያለውን ህይወት ስለማናውቅ፤ በቀላሉ የሚገኝ ይመስለናል።

ለዚህም ነው “ስኬትን አሳየኝና ዋጋውን እከፍላለው” የሚል አመለካከት የተጠናወጠን። ልክ “መጀመሪያ ይሙቀኝና ማገዶውን እጨምራለው” እንደሚለው ሞኝ።

ምልክት ፈላጊ መሆን ለምናስበው ነገር መክፈል ያለብንን መስዋትነት ወይም ዋጋ እንዳናውቅ ያደርገናል። ለምሳሌ መልካም ቤተሰብ ስጠኝና ጥሩ ሚስት እሆናለው የምትል ሴት፤ ማገዶውን ሳትጨምር ቤቷ እንዲሞቅ የምትሻ ሞኝ ናት።

መጀመሪያ የሚቀድመው መልካም ሚስት መሆን ስለሆነ። ጎበዝ ተማሪ አድርገኝና ማጥናት እጀምራለው የሚለውም ተማሪ እንደዛው፤ የጥናት ማገዶውን ሳይማግድ የትምህርትን ሙቀት የሚጠብቅ ተላላ ነው።

ጥሩ ጓደኛ ስጠኝና ጥሩ ሰው እሆናለው የምንለው ስንቶቻችን ነን? ትክክለኛዋን ሴት ሳገኝ ወይም ትክክለኛውን ሰው ሳገኝ የተስተካከለ ኑሮ እጀምራለው እያልን በእድሜያችን የምንቀልድ ብዙዎቻችን ነን።መቅደም ያለበት የገዛ እራሳችን ለውጥ መሆኑን ስለማናውቅ።

ሳናውቀው በተለያየ የህይወታችን ገጽታዎች ይህንን አመለካከት ይዘን ነው የምንጓዘው። ይህች ምድር ልክ እንደ ባንክ አካውንታችን ናት፤ ያላስገባንባትን ልናውጣባት ከሞከርን የማይቻል ብቻም ሳይሆን እራሳችንንም ችግር ውስጥ እየከተትን ነው።

በህይወታችን የምናገኘው ነገር አስከቀድመን የከፈልነውን ነው። 10ብር ባንካችን ውስጥ አስገብተን፤ 200ብር እናውጣ የምንል ከሆነ አይምሮዋችን በትክክል መስራቱን ማረጋገጥ አለብን።

ይህ አመለካከት ለህይወታችንም የሚሰራ ነውና። ያልሰጠነውን ለመቀበል የምንሞክር ከሆነ ትርፉ መከፋት ነው።

ሁሉ ነገር ዋጋ አለው። እንደሸቀጥ ሁሉ በህይወታችን የምንፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ የሚጠይቁት የተለያየ ዋጋ አለ። ልዩነቱ የምንከፍለው በገንዘብ አለመሆኑ ነው።

ለመልካም ኑሮ የሚከፈለውን ዋጋ ሳንከፍል መልካም ኑሮ እየጠበቅን ከሆነ ልክ ማገዶውን ሳያሰገባ ሙቀቱን እንደሚጠብቀው ሞኝ እየሆንን ነው። ምንም ነገር ሳናጠና ፈተናችንን በጥሩ ሁኔታ ለማለፍ እየተመኘን ከሆነ እራሳችንን እያታለልን ነው።

ጥሩ ሰራ ለመያዝ ፤ጥሩ ደሞዝ ለማግኘት የሚያስችለንን ብቃት ሳናከብት ደረጃውን ለመዝለል ከሞከርን ውጤቱ ውድቀት ነው።መልካም የትዳር አጋር ሳንሆን የሞቀ ጎጆ ስጠኝ እያልን ከሆነም ተሳስተናል።

ከሱስ ለመላቀቅ የሚከፈለውን ዋጋ ሳንከፍል፤ በተዓምር የተመሰቃቀለው ኑሮዋችን እንዲቀና የምንጠብቅ ከሆነ አሁንም ተሳስተናል።

ባጠቃላይ በማንኛውም መስክ ላይ መክፈል ያለብንን ነገር ሳንከፍል ውጤቱን መጠበቅ አንችልም።

የምንመኘውን ኑሮ ለመኖር የምንከፍለው ዋጋ ምን እንደሆነ በቅድሚያ ማወቅ አለብን።

ያንን ዋጋ ሳንከፍል ግን በባዶ ተስፋ ነገሮች እንዲስተካከሉ የምንሻ ከሆነ ጊዜያችንን ከማቃጠል በቀር የምንፈይደው አንድም ነገር የለም። ለራሳችን አዘውትረን መንገር ያለብን ነገር ቢኖር የምናገኘው የሰጠነውን ነው። ከኑሮዋችን ውስጥ የምንጠብቃቸው ነገሮች በቅድሚያ የህይወት ባንካችን ውስጥ መኖራቸውን ማወቅ መቻል አለብን። ያላስቀመጥነው አናገኘምና።

በህይወት ባንካችን ውስጥ ያስቀመጥነው መልካምነት ከሌለ፤ ይህች አለም እንዴት ክፉ ሆነችብኝ ብለን የማማረር ብቃቱ የለንም። ያከማቸነው ትጋት እና ስራ ከሌለ እንዴት ያሰብኩት አልተሳካም ማለት አንችልም።

ከላይ እንደተገለጸው ለሁሉም ነገር ዋጋ አለው፤ ያን ዋጋ ሳንከፍል ምኞታችንን የግላችን ለማድረግ አንችልም። ከምንም በላይ ደግሞ መቅደም ያለበትን ነገር ማወቅ አለብን፤ ከስኬታችን በፊት ስራ ይቀድማል፤ ከሙቀቱ በፊት ማገዶው መማገድ እንዳለበት ሁሉ
43 viewsNa le Tofek, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 07:10:22 ይህን እድል በፍጹም በቸልታ አይለፉት

አስደሳች ዜና ከኢትዮ ቴሌኮም

ይህ በጀት አመት ለኢትዮ ቴሌኮም #ethio_tel ወርቃማ እና ከፍተኛ ትርፍ ያገኘንበት እንደሆነ ይታወቃል ፣ ይህ ሲሆን ግን የእናንተ ደንበኛቻችን አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነበር ።

ይህን በማስመልከት በተለያዩ ጊዜያት ለደንበኞቻችን FREE VOICE ፣ FREE DATA and FREE SMS #ስጦታን ማበርከታችን አይዘነጋም ፣

በቅርቡም ድርጅታችን ያስተዋወቀው የቴሌ ብር #tel_birr መተግበሪያ 20 #ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን በመሻገሩ 20% ኢትዮጵያውያንን የዲጂታል ኢትዮጵያ አካል ማድረግ ችለናል ።

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ

ይህን አገልግሎት ከዚህም የበለጠ ተደራሽነቱን ለማስፋት እንደ ከዚህ ቀደሙ የእናንተ የደንበኛቻችን ትብብር ወሳኝ ነው ፣

ለዚህም ትብብርዎ እንደ ሁልጊዜው "የደንበኝነት ስጦታ" በሚል የተለያዩ ሽልማቶችን ባለእድል ልናደርግዎ ተዘጋጅተናል ፣

ኛ ዙር የኢትዮ ቴሌኮም #ethio_tel ቴሌ ብር #tel_birr የያጋሩ ይሸለሙ መልዕክት እጣ ዝርዝር ፣

1ኛ. ለ300 እድለኞች 100,000 ብር
2ኛ. ለ450 እድለኞች 80,000 ብር
3ኛ. ለ600 እድለኞች 50,000 ብር
4ኛ. ለ725 እድለኞች 20,000 ብር
5ኛ. ለ870 እድለኞች 30,000 ብር
6ኛ. ለ1225 እድለኞች 10,000 ብር
7ኛ. ለ1500 እድለኞች 5,000 ብር

ልብ ይበሉ! ተሸላሚ ለመሆን በመጀመርያ በጥንቃቄ ያንብቡ



ለመሸለም ይህንን መንገድ ብቻ ይከተሉ!

1.መጀመርያ ከታች ባለው ማስፈንጠርያ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ።



@tel_birr
@tel_birr
@tel_birr

2. በመቀጠል ከ50 ሰዎች በላይ ይህን መልዕክት በፍጥነት ሼር (Forward) ያድርጉ፤ ለበርካታ ሰው ሼር ያደረገ እድለኛ ይሆናል ።

3.በመቀጠል ከ40,000 በላይ አባላት ባሉት የ #ethio_tel ግሩፕ ውስጥ በርካታ ሰዎችን #Add ያድርጉ። ( https://t.me/ethio_teI ) በርካታ ሰዎችን የጋበዙ ተሳታፊዎች ተሸላሚ ይሆናሉ።

@ethio_teI
@ethio_teI
@ethio_teI

እስከ ነሐሴ 15 ድረስ ብቻ የሽልማቱ አሸናፊ ይሁኑ ! መልካም እድል!

ማሳሰቢያ

ትክክለኛው የ #ethio_tel የቴሌግራም #ገፅ እና #ግሩፕ ይህንን መልእክት እና የአሸናፊዎችን ዝርዝር የያዘ መሆኑን እና ሌላ ምንም አይነት የፎቶ እና የፅሁፍ #post የሌለው መሆኑን ያረጋግጡ ።

Ⓡሕግና ደንቦች ተፈፃሚነት አላቸው
ⓇAll Right Reserved

Tel_Birr
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ!

Copyright Ⓒ ethio tel Ⓒ 2022.

ISBN: R3985648569
TIN: 2014AA56

Ⓡ ethio tel Ⓒ
83 viewsNa le Tofek, 04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 22:51:40 የታላቆች አባት
የሠው ልጅ በስራው ከገነት ሲባረር
ቅጠል ተሸፋፍኖ በዱር ይኖር ነበር
የኃላ የኃላም ተፈጥሮ አምጾበት
ይጫጭር ጀመረ ድንግሊቷን መሬት
ያኔ የወረደው የስልጣኔ ዕውቀት
ሠውን አደረገው የዚች አለም አባት
ሲወርድ ሲዋረድ ይሄው በዘመኑ
መሬቲቷን ጭረው አዳሪዎች አሉ
ምን የነሱን ብቻ ጫጭረው ጫጭረው
ህይወት ያተርፋሉ የሌላን ጨምረው
የዕውቀት እርምጃ ጥንት የነበረውን
ዛሬም ይለካሉ ሳይቀይሩ ውሉን
ስልጣኔ አብቦ እውቀት ቢደረጅም
ቢተኮስ በሰማይ የሰው ልጅ ቢነጥቅም
መሰረቱ ያው ነው
እሱን ያሳደገው
መሬት ጭሮ ኮ ነው
አመድ አፋሽ ቢሆን የጁን ባያገኝም
ባለውለታ ነው ላሁኑ ስልጣኔ ለትናቱ አለም
ታዲያ ይኸን አባት ገበሬን ባላገር
እኮ ማን እረዳው ሞፈር ቀንበር ሲያስር
ኑሮው ሲጎሳቀል
ቀረ እንጂ አስተምሮ እሱ እየቆሰለ
በብርድ በፀሐይ ፊቱ እየከሠለ
እንኳን ያስተማረው ያሰበው ማን አለ
ዛሬም ያው እሱ ነው ገበሬ ባላገር
ተሸፋፍኖ ቅጠል የተገኘው በዱር
ትላንትም ነበረ ዛሬም መሬት ጫሪ
አድሮ አሱ አሳዳሪ
https://t.me/Na_Le_Ethiopia

66 viewsNa le Tofek, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 18:17:51 “ዘፈን መታሰሪያ ድሮ እንዳልነበረ
ወልቃይት ጠገዴ ያኮራኛል ጎንደር ሲዘፈን አደረ”

ነፃነትን የሚተካው ነፃነት ብቻ ነው። እንኳንስ በግፍ የተወሰደ ማንነት ያለ አግባብ የተወሰደች ዶሮም ታስቆጫለች። ታሳምማለች፣ ስለ ነፃነት የጮኹ ድምፆች፣ ስለ ነፃነት የታገሉ እጆች፣ ስለ ነፃነት የተራመዱ እግሮች፣ ስለ ነፃነት የሰሙ ጀሮዎች፣ ስለ ነፃነት የተመለከቱ ዓይኖች ብዙዎች ነበሩ። ስለ ማንነት መሞት፣ ስለ ማንነት መንገላታት፣ ስለ ማንነት መሰደድ።

መነሻዬ ከነገሥታቱ ሀገር፣ ከጥበቧ ከተማ፣ ከአርባራቱ ደብር መገኛ ጎንደር ነው። ታሪክ የዘከራቸው፣ ቅዱስ መንፈስ ያደረባቸው፣ ፍቅር የከተመባቸው ናቸው። በገነት ተራራ ግርማ፣ በጃን ተከል ዋርካ ጥላ፣ በፋሲል ግንብ ሞገስ፣ በአርባ አራት ታቦታት ቅዱስ መንፈስ ከምትኖረው ጎንደር ከተማ ከትሜ ነበር ያደርኩት። ጎንደር ኢትዮጵያዊነት ይሰበክባታል፣ በኢትዮጵያዊነት ይኖርባታል። ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ነገር ተሰርቶባታል። በጎንደር አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ነፃነት፣ አሸናፊነት፣ ታላቅነት፣ አርቆ አሳቢነትና ጀግንነት አለ። አዳሬ መልካም ነው።

የጨለማ ካባ ከምድር ላይ ሲገፈፍ፣ ብርሃን በተራው ምድርን ሊያደምቃት ሲወነጨፍ ከተኛሁበት ነቃሁ። ደስ የሚል ንጋት። መዳረሻየን ወደ በረሃው ለማድረግ አስቢያለሁ። ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራን ለመቃኘት ጓጉቻለሁ። ጀንበር ስትሞቅ፣ ዝምታን መርጣ ያደረችው ጎንደር ስትደመቅ በጎንደር ሰሜናዊ አቅጣጫ ወጥቼ ጉዞዬን ጀመርኩ። ጥቂት እንደተጓዝኩ የዳባት፣ የደባርቅ፣ የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክና ሊማሊሞ መሄጃን መንገድን ወደ ቀኝ ትቼ ሰሜን ምዕራቡን መንገድ ይዤ ጉዞዬን ቀጠልኩ።

መንገዱ የአርማጭሆን ምድር እያቆራረጠ፣ ጠገዴን እያስቃኘ፣ ወልቃይት ጠገዴን እያሳዬ፣ ሰቲት ሑመራን አቋርጦ ተከዜን የሚያሻግር ነው። የአርማጭሆ ኮረብቶች በአሻገር ሲታዩ ልብን ይሰርቃሉ። ቀልብን ይሰበስባሉ። አረንጓዴ ካባውን ያልተነጠቀው መልከዓ ምድር ማራኪ ውበትን ተጎናፅፏል። በግራና በቀኝ እንደ ቤተመንግሥት እልፍኝ አስከልካዮች የተሰደሩት ኮረብቶችን እየቃኘሁ ከአርማጭሆ የላይኛው ክፍል ወደታችኛው ወረድኩ።

ዝቅ እያሉ በሄዱ ቁጥር ወበቅ እየበዛ ይሄዳል። የሚጋረፍ ሞቃት አየር ይመጣል። አርማጭሆን ሲወርዱ በመንገዱ በስተቀኝ በኩል ኢትዮጵያን ድንጋይ ላይ ይመለከቷታል። በጥበበኛ አናፂ የታነፀች የምትመስለው ድንጋይ የኢትዮጵያን ካርታ ታሳያለች። የታደለ ምድር ድንጋዩ ኢትዮጵያን ቀርፆ ይዟል። ሰውም በኢትዮጵያ ፍቅር ተይዟል። እየተገረምኩ ጉዟችን ቀጠለ። ከተራራው እየወረዱ በሄዱ ቁጥር መልክዓ ምድሩ ውበቱ እየጨመረ ይሄዳል።

ሁልጊዜም በጥንቃቄ የሚኖረው የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ንቃቱ፣ ፍጥነቱ፣ አለባበሱና አረማመዱ ልብ ይሰርቃል። በየመንገድ ዳሩ የተሠሩ የበረሃ መንደሮችን እያቆራረጥን ሳንጃን አልፈን ወደፊት ገሰገስን። በረሃው እየተጋረፈ ነው። ጉዟችን ቀጥሏል። የበረሃ መንደሮችን አቆራርጠን ሶሮቃ ከተማ ደረሰን። በሶሮቃ ከተማ መውጫ አካባቢ በስተ ግራ በኩል እርጎዬ፣ አዲስ ዓለምና አብርሃጅራ የሚወስደውን መንገድ ያያሉ።

የእኔ ጉዞ ግን ወደዳንሻ ነበርና በስስት ተመልክቸው ወደፊት ገሰገስን። ሶሮቃ ከተማን እንዳለፉ ማንነታቸውን ተነጥቀው የኖሩ ዜጎችን ማግኜት ይጀምራሉ። አሸባሪው ትህነግ ያለማንነታቸው ማንነት ሰጥቶ፣ መስመር ሰርቶ በጭቆና የኖሩ ዜጎች ናቸው። ጉዟችን ቀጥሏል። ከወራት በፊት በዚያ ምድር ላይ የተካሄደውን የሕግ ማስከበርና የወያኔን ትቢት እያስታወስኩ ከነፍን።

ደማቋ ዳንሻ ከተማ ደርሰናል። ሙቀትና የሰው ድምቀት በከተማዋ ነግሷል። በመንገዱ ዳር በቆሙት አረንጓዴ ዛፎች ተቀምጠው የሚጨዋወቱ ሰዎች ብዙ ናቸው። የተዘናጋ ሰው አይታይም። ሁሉም ጥንቁቅና ንቁ ነው። የበረሃውን ሙቀት ተቀበለን። የሰው ፍቅርና ንቃት ደግሞ ሙቀቱን አስረሳን። አጄብ ነው። ዳንሻን አይቶ የማይገረም አይኖርም።

በዳንሻ የነበሩንን ሥራዎች እንጨርስ ዘንድ ጀንበርን በዳንሻ ከተማ ልናጠልቃት፣ ሌሊቱንም በዚያው ልናሳልፍ ተስማምተናል። ያሰብነውን ፈፀምን። ጀንበር ጠለቀች። ብርሃን ለጨለማ እጅ ሰጠች። ዳንሻ ግን በድምቀቷ ቀጠለች። በምሽትም የምትደምቀዋን ዳንሻን በቀስታ ቃኘኋት፣ ነፃነት ጠምቷቸው፣ ፍትሕ ተነፍጓቸው፣ ማንነታቸው ተወስዶባቸው ዓመታትን በትካዜ ያሳለፉት የወልቃይት ሰዎች ደስታ ላይ ናቸው።

ዘፈን ምረጡ፣ በተመረጠላችሁ ልብስ አጊጡ የሚል የለም። ያ ዘመን አልፏል። እንደ ጨለማ ተገፏል። እንደ እንቦይ ፍሬ ረግፏል። እንደ ጥላ አልፏል። በባሕል ማጌጥ፣ በሚስማማ መጨፈርና መደሰት ተጀምሯል። በአሸባሪው ትህነግ “ውጉዝ ከማርዮስ” ተብለው የነበሩ የአማርኛ ዘፈኖች በከተማዋ ዳር እስከዳር ከፍ ብለው ይሰማሉ። ቤቶች በደስታና በፍቅር ደምቀዋል። አጄብ ነው። ነፃነት ሲመለስ፣ ፍቅር ሲነግሥ ደስታውን በምን ይገልፁታል። ከተማዋ በደስታ ታመሰች።

ከተከዜ መለስ በሰፈሩት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች የግፍ ማዕበል ፈሷል። የጭካኔ ጥግ ደርሷል። የወልቃይት ሰዎች የተወሰደባቸው ከንብረት፣ ከቤትና መሬት ሁሉ ይልቃል። የተወሰደባቸው ማንነት ነውና። ማንነት የተፈጠሩበት፣ የወረሱት፣ የሚኖሩት፣ የሚያከብሩት፣ የሚጠብቁት ከደምና ከአጥንት ጋር የተዋሐደ እንጂ ሲፈልጉ የሚያወልቁት ሲሻ የሚያጠልቁት አይደለም። ማንነት በይሁንታ የሚሰጥ ስጦታም አይደለም። በግፍ የሚጭኑትም አይደለም። ማንነት ረቂቅ ነው።

የወልቃይት ሰዎች ግን ማንነት ተሰጥቷቸው፣ ያለኩት ማንነት ተሰፍቶላቸው። የእነርሱ ተወልቆባቸው የኖሩ ናቸው። ደስታቸው ሲሹት የነበረውን በማግኜታቸው ነው። በሰው ደስታ መደሰት ሰውነት ነውና ደስታቸው ደስ ይላል። በዳንሻ የምሽት ድምቀት ስደመም አምሽቼ ወደ ማደሪያዬ አቀናሁ። ሙቀቱ መጋረፉን አላቆመም። ዳንሻ እንደደመቀች ማደሪያዬ ተዘጋች። ነብሴም በእንቅልፍ አረፈች። ጠዋትን እንዳይ አደራ የሰጠሁት ፈጣሪ አደራው ሳያጓድል ብርሃን አሳየኝ። እኔም አመሰገንኩት።

ደማቋ ዳንሻ በጠዋትም መድመቅ ጀምራለች። ጉዟችን ይቀጥላል። ዳንሻን ተሰናበትናት። የዳንሻን ሰሜን ምሥራቅ ንፍቅ ይዘን ወደፊት ገሰገስን። የወልቃይት ጠገዴ ውብ ምድር ያማልላል። በበረኻው ውስጥ ሲጓዙ አልፎ አልፎ የመኖሪያ ቤቶች ይታያሉ። በመልካዓ ምድሩ መደመሜ አላቆመም። አጀብ ያሰኛል። ልብን ይፈትናል።

በዚያ ምድር በእግር ለማቆራረጥ ወንድነት ይጠይቃል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን በነፃነት ይንቀሳቀሱበታል። ያለ ስጋት ይኖሩበታል።
“ሰዎቹ ቀጭን ልባቸው ዳንዴ፣
የእነ አጅሮች ሀገር ወልቃይት ጠገዴ” የተባለላቸውም ለዚህ ነው።

በሰንሰለታማ ተራራዎች መካካል የተሠራውን መንገድ አቆራርጠን፣ ትንንሽ መንደሮችን አልፈን ወደ ወፍ አርግፍ ከተማ አቀናን። በመልካሙ ምድር፣ በደጉ ሕዝብ ላይ ወያኔ ግፍ አድርሷል። የግፍ ዘመን አልፎ መልካም ዘመን መጥቷልና የመከራው ጥላ የተነሳ ይመስላል። ጉዟችን ቀጥሏል። ሰንሰለታማ ተራራዎችን አቆራርጠን ወፍ አርግፍ ከተማ ከተምን። ወፍ አርግፍ ሽር ጉድ ላይ ናት። የነፃነቱ ነጋሪት እየተጎሰመ፣ ጥዑመ ዜማ እየተዜመ፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ እየተውለበለበ ከተማዋ ደምቃለች። ማደሪያችን ወርፍ አርግፍ ሆኗል። በዚህች ከተማ የጭንቅ ዘመን ታልፎባታል። ማንነት ተገፎ በቀል ተሰብኮባታል። ነፃነት ተረግጦባታል። ዘመን አልፎ ነፃነት ታውጆባታል። ማንነት ተመልሶባታል። ጀንበር ጠለቀች። ብርሃን እጅ ሰጠች።
69 viewsNa le Tofek, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:22:52
32 viewsNa le Tofek, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 13:47:56 አበጀሁ ጎንደር!!

አበጀሁ አማራ!!

ሀምሌ 5 የጎንደር ከተማ በጨለማ ድቅድቅ የገባችበት ለዛሬ የነፃነት ቀን ሲወለድ ከተማዋ ምጥ ውስጥ ነበረች።

ጎንደር የኢትዮጵያ መናገሻ ዋና ከተማ የዘመናዊ ፖለቲካ መነሻ የአንድነትና የጀግንነት ተምሳሌት የነፃነት ቀንዲል መዳራሻ በጀግኖች ልጆቿ ታፈራና ተከብራ ለኖረችው ኢትዮጵያ ዘውድ ናት ጎንደር።

የዚህ ዘመን የነፃነት ቀን የተጀመረው እዚህ ጎንደር ነው። ጎንደር ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ የዛሬውን የነፃነት ቀን ያስረከበችው አልጋ በአልጋ አይደለም ውድ ልጆቿን መስዋዕትነት ከፍላ ነው።

ይመስክር ጎንደር፡ ሸዋ ዳቦ ይመስክር፡ አራዳ ይመስክር፡ ህዳሴ ይመስክር ፒያሳ ይመስክር ማራኪና ቸቸላ--- ልደታና...ፋሲል… አዘዞ---ጠዳ… ኧረ መላው ጎንደር ይ መ ስ ክ ር

ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ፣ደቡብና ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ይ መ ስ ክ ር

ድፍን ሸዋ፣ ጎጃም፣ ወሎ… ይመስክር

የስንቱን የጎንደር አማራ ደም እዚሁ ከተማ ላይ ፈሰስ ሰጠኝ ባብልን የመሰለ ጀግና፣ ሲሳይን የመሰለ አይበገሬ አርበኛ፣ ሰለሞንን የመሰለ ታታሪ ወጣት፣ ቴወድሮስ በሁለት አፍ የተሳለ ትንታግ ልጅ

ብቻ ብዙዎቹን ሀምሌ 5 ነበር ለነፃነታቸው ፊታችን ላይ ያጣናቸው።

የትግሉ አቀጣጣይ ጀግናው ኮሮኒል ዘውዱ የዘመናችን ዳግማዊ ቴዎድሮስ የጎንደር አማራ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

የጎንደር ትግል በመላ አማራ በቀናትን ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ማዕበል በማስነሳት መላ አማራ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ በጋራ በመነሳት የአማራን ነፃነት የኢትዮጵያን ትንሳኤ አብስሯል።

ዛሬም የጎንደር መናገሻነት የአማራ የፖለቲካ መነሻ የኢትዮጵያ የአንድነት መስተጋብር አቅፋ ይዛ አማራ ጠል የሆኑ ቡድኖችን በተባበረ ክንድ ከሌሎች የክልላችን ህዝቦች ህብረት በመፍጠር ለመጪው ትውልድ የነበረውን ትርክት አስወግዳ አዲስ ታሪክ ለመከተብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ናት።

አበጀሁ ጎንደር

አበጀሁ አማራ

መልካም የነፃነት ቀን
53 viewsNa le Tofek, 10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 13:41:29 አበጀሁ ጎንደር!!

አበጀሁ አማራ!!

ሀምሌ 5 የጎንደር ከተማ በጨለማ ድቅድቅ የገባችበት ለዛሬ የነፃነት ቀን ሲወለድ ከተማዋ ምጥ ውስጥ ነበረች።

ጎንደር የኢትዮጵያ መናገሻ ዋና ከተማ የዘመናዊ ፖለቲካ መነሻ የአንድነትና የጀግንነት ተምሳሌት የነፃነት ቀንዲል መዳራሻ በጀግኖች ልጆቿ ታፈራና ተከብራ ለኖረችው ኢትዮጵያ ዘውድ ናት ጎንደር።

የዚህ ዘመን የነፃነት ቀን የተጀመረው እዚህ ጎንደር ነው። ጎንደር ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ የዛሬውን የነፃነት ቀን ያስረከበችው አልጋ በአልጋ አይደለም ውድ ልጆቿን መስዋዕትነት ከፍላ ነው።

ይመስክር ጎንደር፡ ሸዋ ዳቦ ይመስክር፡ አራዳ ይመስክር፡ ህዳሴ ይመስክር ፒያሳ ይመስክር ማራኪና ቸቸላ--- ልደታና አዘዞ---

ይመስክር የአርማጭሆ ምድር ይመስክር ጠገዴ - ወገራ -ደንቢያና በለሳ-- አለፋና ጣቁሳ--

የስንቱን የጎንደር አማራ ደም እዚሁ ከተማ ላይ ፈሰስ ሰጠኝ ባብልን የመሰለ ጀግና፡ ሲሳይን የመሰለ አይበገሬ አርበኛ፡ ሰለሞንን የመሰለ ታታሪ ወጣት፡ ቴወድሮስ በሁለት አፍ የተሳለ ትንታግ ልጅ - - - - - - ብቻ ብዙዎቹን ሀምሌ 5 ነበር ለነፃነታቸው ፊታችን ላይ ያጣናቸው።

የትግሉ አቀጣጣይ ጀግናው ኮሮኒል ዘውዱ የዘመናችን ዳግማዊ ቴዎድሮስ የጎንደር አማራ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

የጎንደር ትግል በመላ አማራ በቀናትን ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ማዕበል በማስነሳት መላ አማራ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ በጋራ በመነሳት የአማራን ነፃነት የኢትዮጵያን ትንሳኤ አብስሯል።

ዛሬም የጎንደር መናገሻነት የአማራ የፖለቲካ መነሻ የኢትዮጵያ የአንድነት መስተጋብር አቅፋ ይዛ አማራ ጠል የሆኑ ቡድኖችን በተባበረ ክንድ ከሌሎች የክልላችን ህዝቦች ህብረት በመፍጠር ለመጪው ትውልድ የነበረውን ትርክት አስወግዳ አዲስ ታሪክ ለመከተብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ናት።


አበጀሁ ጎንደር

አበጀሁ አማራ



መልካም የነፃነት ቀን
114 viewsNa le Tofek, 10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ