2022-06-30 14:54:52
#የኛ_ዘመን_ወጣት_ሚና
በጎንደር አዘዞ ጠዳ ክፍለከተማ "የኛ ዘመን ወጣት ሚና" በሚል መሪ ቃል ወጣቶች ጋር በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት በቅርቡ በኦነግ ሸኔ እና በተለያዩ ጊዜያት የሂወት መስዋዕትነት እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሀን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል።
መድረኩን የመሩት የጎንደር ከተማ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ወጣት ቶፊቅ እስማኤልሀኪም ሲሆኑ በመድረኩ ላይ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል። ፕሮግራሙን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ይሁን ዳምጤ ናቸው።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ የሆኑት ወጣት ሀይለ ማሪያም ፋሲል ሲሆኑ በሰነዱም በዚህ ዘመን ያለን ወጣቶች በሀገራችን የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን፣ የተሰሩ የልማትና የዲሞክራሲ ማጎልበት ስራዎችን ማወቅና ማበረታታት እና ሚዲያውን የሰላምና የልማት መሳሪያ እንዲሆን በመቅረፅ በጉልህ መንቀሳቀስና ሀገራችንን ወደ ቀደመ ክብሯ መመለስ እንደሚጠበቅብን ተገልጿል።
በተጨማሪም በሰነዱ ወጣቱ በክረምት ወራት በበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ በመሠማራት ሀገሩን ብሎም ራሱን መጥቀም እንዳለበት እና በያዝነው አመት ለታቀዱት የክረምት በጎፈቃድ ተግባራት አጋዥ እንዲሆኑ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ጥሪ ተላልፎል።
የኛ ዘመን ወጣቶች ህብር ብሔራዊ ወንድማማችነት በመገንባት ለሃገራችን አንድነትና ዘላቂ ሰላም ላይ በመትጋት ለሚያጋጥሙ ችግሮች የመፍትሔ አካል መሆን አለብን ሲሉ ወጣት ቶፊቅ ገልፀዋል።
በመጨረሻም የወጣቱን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ፣ ከህግ ማስከበር አንፃር፣ ሀገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት ከወጣቱ ምን ይጠበቃል፣ ከኑሮ ውድነት አኳያ እንዲሁም ከክረምት በጎፈቃድ ተግባሮች አንፃር በርካታ ጥያቄዎች ከውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስተው በመድረኩ መሪዎች ምላሽ በመሰጠትና ወጣቱ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል የሀገሩን ዳር ድንበር ማስጠበቅ እንዳለበት መልዕክት በማስተላለፍ ውይይቱ ተጠናቋል።
68 views𝐓𝐚𝐦𝐢𝐫𝐚𝐭 𝐘𝐢𝐫𝐝𝐚𝐰, 11:54