Get Mystery Box with random crypto!

መግቢያ አምናና ታች አምና ለዐሥሩ ጣቶቼ ሥራ አልነበራቸውም፡፡ ለእኒህ ጣቶቼ ሥራ ፍሊጋ ደጋ ስወ | አዋጅ – Awaje News

መግቢያ

አምናና ታች አምና ለዐሥሩ ጣቶቼ ሥራ አልነበራቸውም፡፡ ለእኒህ ጣቶቼ ሥራ ፍሊጋ ደጋ ስወጣ፤ ቆላ ስወርድ ከዓመታት በፊት ነበልባል የሚባል የቅኔ ዘራፊ

በቅኔያችን ጥበብ በያዝነው ሆሣዕና፣

እንነጠቃለን በግዙፍ ደመና

ከሚለው ቅኔ “ጥበብ ተቀብራለች” ብሎ የነገረኝ ትዝ አለኝ፡፡ ቅኔዉን ከልጅነቴ ጀምሮ እኔም አውቀዋለሁ፡፡ የሊቁ ክፍለ-ዮሐንስ መወድስ ነው፡፡ ሊቁ ክፍሉዮሐንስ በዘመኑ ባንዲት ዕለት፣ በተመሳሳይ ሰዓት በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴና በሸዋ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቅኔማኅሌት ሲያገለግል ይውል ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የሸዋ ሊቃውንት ሊቁ ክፍለ-ዮሐንስ ከእነሱ ጋር በመንፈሳዊ አገልግሎት እንደ ዋለ በኩራት ሲናገሩ የጎንደር ሊቃውንት ደግሞ በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ እንደ ልማዱ አዳፋ ልብሱን ለብሶ ቅኔውን ሲገጨው መዋሉን ይናገራሉ፡፡ ባለ ቅኔዉ በተመሳሳይ ሰዓት ጎንደርና ደብረ ብርሃን ሥላሴ በመንፈሳዊ አገልግሎት ስለማሳለፉ ሲጠየቅ፡

ንሕነሂ በግብረ ቅኔ ዘበሆሣዕና፣

እምእደ ገፋዒ ወተገፋዒ ንትመሰጥ በደመና ሊል በመወድሱ መለሰ።

ቅኔው ከላይ ከላይ ሲተረጎም:

‹ብቅኔያችን ጥበብ በያዝነው ሆሣዕና፣

እንነጠቃለን በግዙፍ ደመና እንደ ማለት ነው። ነበልባል እንደ ነገረኝ በዚህ ቅኔ ውስጥ ጥበብ ተቀብራለች

ነበልባል ሌላም ተመሳሳይ ታሪክ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር።

“ከኢትዮጵያውያን ጠቢባን ሌላው ደግሞ ተዋነይ ይባል ነበር። ጠቢቡ ተዋነይ ከጎጃም ቅኔ ተቀኝቶ በተመሳሳይ ሰዓት ጎንደር ይደግም እንደ ነበር ዜና-ጥበቡ ይጠቁማል፡፡ ይህንን የኢትዮጵያ ዕፁብ ድንቅ ጥበብ የቅኔ ሊቃውንት በኩራት ይናገሩታል።

ባላገሮችም

‹‹ተዋነይ በጣና

ይመስላል ደመና ሲሉ ተዋነይ በደመና መጋለቡን ይተርካሉ” ብሎኛል ነበልባል፡

ነበልባል የነገረኝን ምሥጢር ለዐሥሩ ጣቶቼ ነገርኋቸው፡፡ ሥራ እንደ ፈጠርሁላቸው ቆጠሩት፡፡ ከዘመናት በፊት የነበረውን ሀገራዊ ፍልስፍና እየተሻሙ መክተብ ጀመሩ፡፡ ባለ ቅኔው ክፍለ ዮሐንስ መጣ፡፡ ተዋነይ ተገለጠ። ሌሎችም ሊቃውንት በየተራ መጡ፡፡ አሥሩ ጣቶቼ በቅኔው ውስጥ የተቀበረውን ምሥጢር ሀገርኛ ብዕር ጨብጠው መክተብ

ሲጀምሩ ጠቢቡ ሖረ ኩራዝ ለኮሱ፡፡ ወዲያው ግን ነፋስ በቤቱ ቀዳዳ ገብቶ አጠፋባቸው፡፡ ሊቅ ዐዕቁ ሐሽማል የሚባል በጨለማ ውስጥ ቀይ ብርሃን የሚፈነጥቅ መጽሐፍ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ሐሽማል ድቅድቁን ጨለማ ገፈፈው፡፡ ዐሥሩ ጣቶቼ ሲከትቡ እኔን እንቅልፍ ጣለኝ፡፡ ስነቃ ጠቢቡ ሖረ | ተሰውረዋል። ሊቅ ዐፅቁም ሐሽማልን ይዘው ከቤት ወጥተዋል፡፡ ዐሥሩ ጣቶቼ አንድ መጽሐፍ ጽፈዉ ስለ ስሙ ሲጨቃጨቁ ደረስሁ፡፡ ስሙን ሐሽማል በሉት አልኋቸው፡፡ ሐሽማል ብለው ጠሩት፡፡ እነሆ ሐሽማል ሆነ!!

ማዕበል ፈጠነ