Get Mystery Box with random crypto!

ብዙ ሰዎች ለአካላዊ ጤናቸው ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በአመት ሁለት ጊዜ የህክምና ክትትል (ቼክ አፕ) | አዋጅ – Awaje News

ብዙ ሰዎች ለአካላዊ ጤናቸው ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በአመት ሁለት ጊዜ የህክምና ክትትል (ቼክ አፕ) ያደርጋሉ፤ እንዲህ አይነት ልምድ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን የሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉቀት፣ ጨጓራ፣ ጥርስና የመሳሰሉ አካላት ደህንነት ብቻ የጤናማነት ምልክት ሊሆን አይችልም።

የአለም ጤና ድርጅት ጤና ለሚለው ቃል ትርጉም ሲሰጥ ጤንነት ማለት "ሙሉ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ማሕበራዊ ደህንነት ነው እንጂ አለመታመም ብቻ አይደለም" ይላልና።
WHO defines health as well-being, “a state of complete physical, mental and social well- being and not merely the absence of disease or infirmity”.

ለመሆኑ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

አንድ ሰው የአዕምሮ ጤንነት አለው የምንለው ግለሰቡ ያልተዛነፈ አስተሳሰብ፣ ባሕርይና ስሜት ሲኖረው እንዲሁም ከማሕበረሰቡ ጋር ተቀላቅሎና በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ መኖር ሲችል ነው። እስቲ በዝርዝር እንመልከታቸው፦

ሀ) የአስተሳሰብ ጤንነት (cognitive health)

ጥሩ የማሰብ፣ የማስታወስ (memory)፣ የማሰላሰል፣ ፍሰት ያለው ሀሳብ የማፍለቅ፣ የትኩረት፣ የማቀድ፣ ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ችሎታዎች  የአስተሳሰብ ጤንነትን ያመላክታሉ።

ለ) የስሜት ደህንነት (emotional well-being)

አንድ ሰው የስሜት ጤንነት አለው ለማለት በብዛት በቀን ውስጥ የሚያስተናግዳቸውን ስሜቶች ማወቅ አስፈላጊ ነው። በብዛት ከአሉታዊ ስሜቶች (ለምሳሌ ንዴት፣ ጥላቻ፣ ፍርሃት፣ ቂም...ወዘተ) ይልቅ አዎንታዊ ስሜቶችን (ለምሳሌ ፍቅር፣ መገረም፣ ተስፋና ደስታ) የሚያስተናግድ መሆን አለበት።

ሐ) ጤናማ የህይወት ዘይቤ (Healthy life style)
አንድ ግለሰብ ሰናይ ባሕርያት አሉት የምንለው የሚያደርጋቸውን ነገሮች (አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አነጋገር...ወዘተ) ተመልክተን ነው። ለምሳሌ በብዛት አትክልትና ፍራፍሬ ይመገባል፣ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ ሰው ይረዳል፣ አይሳደብም፣ አልኮል አይጠጣም፣ አይቅምም፣ አያጨስም፣ ነውጠኛ አይደለም...ወዘተ።

መ) ማሕበራዊ ደህንነት (social well-being)
ጥሩ አስተሳሰብ፣ አካላዊ ጤንነት፣ አዎንታዊ ስሜትና የሕይወት ዘይቤ አንድን ሰው ጤናማ ነው ለማለት መሉ መስፈርት አይሆኑም። ያ ሰው ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖር፣ ሀሳቡን ማስረዳት፣ የሌሎችም ሀሳብ መረዳት በጠቅላላው ከሌሎች ጋር በጥሩ ሁኔታ አብሮ መኖር አስፈላጊ ነው።

መደምደሚያ

ጤንነት አካላዊ ደህንነት እንዲሁም አለመታመም ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ጤናማ የባሕርይ እና የአዕምሮ ጤንነታችንን መጠበቅ አለብን