Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 43.70K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-26 22:12:18 ከዚህም በኋላ ሒዶ ወደ ኢያሪኮ ገባ የዚያች አገር ሰዎችም ጌታችን እነሆ እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት። ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውኃው ምንጭ ጨመረው እንዲህም አላቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ አጣፈጥሁት። ከዚያች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ኤልሳዕ እንደተናገረ ያ ውኃ ጣፋጭ ሆነ።

ከዚያም አገር ወደ ቤተል ወጣ ሲወጣም ከከተማው ሲወጡ ታናናሽ ልጆችን በጎዳና አገኘ እነርሱም አንተ ራሰ በራ ውጣ ውጣ እያሉ ይዘባበቱበት ጀመር። ወደ ኋላው ተመልሶ በአያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ረገማቸው የዚያን ጊዜ ሁለት ድቦች ከዱር ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለት ልጆችን ገደሉ።

ከነቢያት ልጆች አንዲት ሴት ነበረች ወደ ኤልሳዕም ጮኸች ባሪያህ ባሌ ሞተ ባሌ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ ባለዕዳ ሁለቱን ልጆቼን ወስዶ ይገዛቸው ዘንድ መጣ አለችው። ኤልሳዕም አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ በቤትሽስ ምን አለሽ አላት ዘይት ካለበት ማሰሮ በቀር ለእኔ ለባሪያህ ምንም የለኝም አለችው።

ሔደሽ ከጎረቤትሽ ሁሉ የሸክላ ዕቃና ባዶ ዕቃዎችን ተዋሺ አታሳንሺ። ወደ ቤትሽም ገብተሽ በአንቺና በልጆችሽ ላይ ደጁን ዝጊ በዚያ በሸክላ ዕቃም ዘይቱን ገልብጪው የመላውንም አንሥተሽ አኑሪው አላት። እርሷም ወደ ቤቷ ገብታ በልጆቿና በእሷ ደጃፏን ዘጋች እነርሱ ያቀርቡላት ነበር እርሷም እየቀዳች ትገለብጥ ነበር። ከዚህ በኋላ ልጆቿን ዳግመኛ የሸክላ ዕቃ አቅርቡልኝ አለቻቸው የሸክላ ዕቃ ሁሉ አለቀ የለም አሏት ከዚህ በኋላ ያም ዘይት ተገታ።

እርሷም ሒዳ ለእግዚአብሔር ነቢይ ነገረችው አልሳዕም ሒጂ ይህን ዘይት ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈዪ የቀረውን ዘይት ግን የልጆችሽን ሰውነትና ያንቺን ሰውነት አድኚበት አላት።

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ በአንዲቱ ቀን ወደ ሱማን ሔደ በዚያም አገር አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች ወደዚያ ከመሔድ ውሎ አድሮ ነበርና እህል ይበላ ዘንድ አቆመችው። ያቺም ሴት ባሏን እነሆ ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ ቅዱስ ነው ዘወትር በእኛ ዘንድ እያለፈ ይሔዳል። ትንሽ እልፍኝ እንሥራለት አልጋም እንዘርጋለት መብራት የሚበራበት መቅረዝንና ወንበርን ጠረጴዛንም እናዘጋጅለት ወደ እኛም በመጣ ጊዜ በዚያ ይደር አለችው።

ከዚህም በኋላ በአንዲቱ ቀን ወደዚያ ገብቶ በእልፍኙ አደረ። ደቀ መዝሙሩ ግያዝንም ያቺን የሱማን ሴት ጥራት አለውና ጠራት እርሷም መጥታ በኤልሳዕ ፊት ቆመች። እነሆ ይህን ሁሉ ክብር አከበርሽኝ ምን ላድርግልሽ ከንጉሥ ዘንድ ከአለቃም ዘንድ ቢሆን ጉዳይ እንዳለሽ ንገሪኝ በላት አለው እርሷም እኔስ በወገኖቼ መካከል እኖራለሁ አለችው። ምን ላድርግላት አለ ደቀ መዝሙሩ ግያዝም ልጅ የላትም ባሏም ሽማግሌ ነውና የሚታዘንላት ሴት ናት አለው። ደግሞ ጥራት አለው በጠራትም ጊዜ መጥታ በደጃፍ ቆመች። ኤልሳዕም የዛሬ ዓመት እንደዛሬ ልጅ ትወልጃለሽ አላት እኔን አገልጋይህን ጌታዬ አታሰቅቀኝ አለችው።

ከዚህም በኋላ ያቺ ሴት ፀንሳ ኤልሳዕ በነገራት ቀን በዓመቱ ወንድ ልጅን ወለደች። ያም ልጅ አድጎ ከአባቱ ጋራ ወደ አዝመራው መጣ። አባቱን ራሴን ራሴን አለው የሕፃኑም አባት ብላቴናውን ወደ እናቱ አስገባው አለው። ብላቴናውም ያንን ልጅ ወደ እናቱ አስገባው እናቱም እስከ ቀትር በጉልበቷ ላይ አስተኛችው።

ከዚህም በኋላ በሞተ ጊዜ አውጥታ በእግዚአብሔር ነቢይ ዐልጋ ላይ አስተኛችው ዘግታበትም ወጣች። ባሏንም ጠርታ ወደ እግዚአብሔር ነቢይ እሔዳለሁና አንድ አህያና ከብላቴኖች አንድ ብላቴና ስደድልኝ አለችው። ባሏም መባቻ ያይደለ ቅዳሜ ያይደለ ዛሬ ለምን ትሔጃለሽ አላት እጅ እነሣው ዘንድ እሔዳለሁ አለችው። አህያውንም ጫኑላት አገልጋይዋንም ተነሥ እንሒድ ባልኩህ ጊዜ መሔድን አትከልክለኝ ና ተከተለኝና ወደ እግዚአብሔር ነቢይ ወደ ቀርሜሎስ እንሒድ አለችውና ሔደች።

ኤልሳዕም ያቺን ሴት ስትመጣ በአያት ጊዜ ብላቴናው ግያዝን ያቺ ሴት ሱማናዊቷ ሴት ናት። አሁንም ሩጠህ ሒደህ ተቀበላት ደኅና ነሽን ባልሽስ ደኅና ነውን ልጅሽስ ደኅና ነውን በላት አለው እርሷም ደኅና አለችው። ወደ ኤልሳዕም ዘንድ ወደ ተራራው ደርሳ እግሩን ያዘችው ግያዝም ሊከለክላት መጣ ኤልሳዕም ሰውነቷ አዝናለችና ተዋት እግዚአብሔር ግን ነገሩን ሠውሮኛልና አልነገረኝም አለው። አታሰቅቀኝ ያልኩህ አይደለምን በውኑ እኔ ከአንተ ከጌታዬ ልጅን የለመንኩት መለመን አለን አለችው።

አልሳዕም ግያዝን ወገብህን ታጠቅ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሒድ ሰውም ብታገኝ እንዴትነህ አትበለው እንዴት ነህ ቢልህም አትመልስለት በትሬንም በሕፃኑ ግንባር ላይ አስቀምጣት አለው። የዚያም ሕፃን እናት እንዳልተውህ ሕያው እግዚአብሔርን በረከትህን አለችው ኤልሳዕም ተነሥቶ አብሮአት ሔደ። ግያዝም በፊታቸው ይሔድ ነበር ሩጦም ቀደማቸው በትሩንም በዚያ ልጅ ግንባር ላይ ጣላት ነገር ግን አልሰማውም አልተናገረውም ግያዝም ተመልሶ ኤልሳዕን ተቀብሎ ያ ልጅ አልተነሣም አለው።

ኤልሳዕም ወደ ቤት ገብቶ ሕፃኑን ሙቶ በዐልጋ ላይ ተኝቶ አገኘው በሁለታቸውም ላይ ደጃፉን ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ወደ ዐልጋውም ላይ ወጥቶ በዚያ ሕፃን ላይ ተኛ አፉን በአፉ ላይ ዐይኖቹን በዐይኖቹ ላይ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ በላዩ ላይ ተኛ የዚያም ልጅ ሰውነት ሞቀ።

ከዚህ በኋላ ተነሥቶ በቤቱ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ተመላለሰ ዳግመኛም ወጥቶ በዚያ ልጅ ላይ ተኛ እስከ ሰባት ጊዜ እንዲህ አደረገ ከዚያም በኋላ ያ ልጅ ዐይኑን ገለጠ ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ ያቺን ሱማናዊት ሴት ጥራት አለው።

ጠርቷትም ወደርሱ ገባች ኤልሳዕም እነሆ ልጅሽን ውሰጂ አላት እርሷም ከእግሩ ላይ ወድቃ ሰገደችለት ልጅዋንም ይዛ ወጣች። የሶርያ ሰው ንእማንም ወደርሱ በመጣ ጊዜ በዮርዳኖስ ውኃ ከለምጹ አዳነው ንእማንም ብዙ እጅ መንሻ ወርቅና ብር ልብሶችንም አመጣለት ከእርሱም ምንም ምን አልወሰደም።

ደቀ መዝሙሩ ግያዝም ተደፋፍሮ ንእማንን ተከተለው ምክንያትም ፈጥሮ ንእማንን እንዲህ አለው ከኤፍሬም አገር ከነቢያት ልጆች ሁለት ሰዎች መጥተውብኛልና አንድ መክሊት ብርና ሁለት ልብሶች ስጣቸው ብሎሃል አለው ንእማንም ሁለት መክሊቶችንና ሁለት ልብሶችን ሰጠው።

ኤልሳዕም ግያዝ ያደረገውን አውቆ ረገመው የንእማንም ለምጽ ገንዘብ ወዳጅ በሆነው በግያዝ ላይ ተመለሰ። በሰማርያም ረኃብ ጸና ከሶርያ ሰዎች የተነሳ የአህያ መንጋጋ በአምሳ ወቄት ብር እስቲለወጥ ድረስ ኵስሐ ርግብም የድርጎ አራተኛ በአምስት ብር እስቲሸመት ድረስ በሀገራቸው የሶርያ ሰዎች ሰፍረው ተቀመጡ። በዚህ ነቢይ ጸሎትም በአንዲት ቀን ረኃቡ ተለወጠ ጥጋብም ሆነ። በዘመኑም ብዙ ድንቆችና ተአምራቶችን አደረገ በሞተም ጊዜ በመቃብር ውስጥ አኖሩት በዚያም ወራት የሞአብ ሰዎች አገራቸውን ከበቡ። ይቀብሩም ዘንድ ሌላ ሰውን አመጡ አደጋ ጣዮችንም በአዩ ጊዜ የዚያን ሰው ሬሳ በኤልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት የዚያም ሰው ሬሳ በኤልሳዕ ዐፅም ላይ ወረደ የኤልሳዕንም ዐፅም በነካው ጊዜ ያ በድን ድኖ በእግሮቹ ቆመ።

@mezmurochh
5.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 22:12:18 ሰኔ_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ በዚች ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው፣ ከገልገላ አውራጃ አለሙት ከምትባል ቦታ የሆነው የሳፋጥ ልጅ #ታላቁ_ነቢይ_ኤልሳዕ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)

ሰኔ ሃያ በዚች ቀን በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው። አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው። አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው። የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው። ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ። ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው። ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች። ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ። ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው። ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው። ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ። ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ። ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል። በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው። ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል። ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው። የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት። ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት።›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14። እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው።

ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ። እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ።

ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል። በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል። ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም። እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸውን ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር።

ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት። ሐዋ 20፡28። በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰው ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል። ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል።

✞ ነብዩ_ኤልሳዕ ✞

በዚህችም ዕለት ከገልገላ አውራጃ አለሙት ከምትባል ቦታ የሆነው የሳፋጥ ልጅ ታላቁ ነቢይ ኤልሳዕ አረፈ። የዚህም ነቢይ መጠራቱ እንዲህ ኾነ ኤልያስ አልፎ ሲሔድ የሳፋጥ ልጅ ኤልሳዕን በፊቱ ዐሥራ ሁለት ጥምድ አስጠምዶ ሲያሳርስ አገኘው እርሱም በነዚያ የተሾመ ነበር ኤልያስም ሔዶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት።

ኤልሳዕም ጥማዱን ትቶ ኤልያስን ተከተለው ኤልሳዕም አባቴ እወድሃለሁ አንተንም እከተላሉሁ አለው ኤልያስም ብላቴናዬ አድርጌሃለሁና ተመለስ አለው። እርሱም ኤልያስን ከመከተል ተመለሰ ዐሥራ ሁለቱንም ጥምድ በሬዎች ወስዶ አረደ በላመ ፈጅ ጋኖችም ቀቅሎ ለሕዝቡ አቀረበላቸው እነርሱም በሉ ኤልያስንም ተከትሎት ሔደ ብላቴናውም ሆነ።

ብዙ ዘመናትም ሲያገለግለው ኖረ። ኤልያስም በሚያርግበት ጊዜ ኤልሳዕን ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ አለው ኤልሳዕም በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ሆኖ ይደርብኝ አለው።

ኤልያስም ኤልሳዕን ድንቅ ነገርን ለመንከኝ ነገር ግን ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ብታየኝ ይደርብህ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ባታየኝ ግን አይሆንልህም አለው።

ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ፈረስና የእሳት ሠረገላ መጣ ወደ መካከላቸውም ገብቶ አራራቃቸው ኤልያስም በመነዋወጥና በጥቅል ነፋስ እንደዚህ ወደ ሰማይ ዐረገ። ኤልሳዕም አይቶ የእስራኤል ኃይላቸውና ጽንዓታቸው አባ አባ ብሎ ጮኸ። ከዚህ በኋላም ዳግመኛ አላየውም ልብሶቹንም ከሁለት አድርጎ ከፈላቸው። ኤልያስም ለኤልሳዕ መጠምጠሚያውን ጣለለት በኤልሳዕ ራስ ላይም ወረደ ኤልሳዕም ተመልሶ በዮርዳኖስ ባሕር ዳር ቆመ። በራሱ ላይ የወረደች የኤልያስንም መጠምጠሚያ ይዞ ውኃውን መታባት ውኃውም አልተከፈለም የኤልያስ ፈጣሪ ወዴት ነው ይህስ እንዴት ነው አለ ከዚህ በኋላም ውኃውን መታው ውኃውም ተከፍሎ ወዲያና ወዲህ ቆመ ኤልሳዕም ተሻገረ።

በዚህም ኤልሳዕ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በዕጥፍ እንደተቀበለ ታወቀ። ኤልያስ የወንዙን ውኃ እንድ ጊዜ ከፈለ። ኤልሳዕ ግን ሁለት ጊዜ ከፈለ ኤልያስ አንድ ምውት አስነሣ ኤልሳዕ ግን ሁለት ምውት አስነሣ።

@mezmurochh
6.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 20:52:40
ገብርሔር

የተፈጥሮን ፀጋ ያለ ስጋት ለገዳማውያን

በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል ብለው ሰውነታቸውን በፊቱ መከራውን ያስችሏታል!

በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ፣ በምድረበዳ ፣ በተራራ ፣ በዋሻ እና ጉድጓድ የሚኖሩ ገዳማውያን እናቶች የተፈጥሮን ሂደት ወይም የወርአበባ እንዴት ያስተናግዱት ይሆን?

ብዙ ሴት መነኮሳይት እናቶች እና እህቶች የተፈጥሮ ሂደት ፈተናቸው ነው!

በዓታቸውን ዘግተው ስለሀገር ሰላም ሌትተቀን ለሚጸልዩ ሴት መነኮሳያት ከሰኔ 5 እስከ ሐምሌ 5 የሚቆይ ልዩ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተዘጋጅቷል!

ይህ ብቻ አይደለም በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በየገዳማቱ ላሉ በአልጋ ላይ ለቀሩ አረጋውያን መነኮሳት የንፅህና መጠበቅያ ከ1000 በላይ ዳይፐር እና ለ2000 ሴት መነኮሳት የ6ወር የንፅህና መጠበቅያ ፓድ እንዲሁም ከ40 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለእነዚሁ ገዳማውያን ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ለዚህ የበረከት ጥሪ እኔ ፣ አንቺ ፣ አንተ ሁላችንም ተጋብዘናል።

በአይነት ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሾላ የካ ፖሊስ ጣብያ ፊትለፊት እልፍ ፀጋ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ መተው ያበርክቱ።

የህክምና ባለሞያዎች ሙያዊ እገዛችሁ ያስፈልገናል እና ኑ አብረን ገዳማውያንን እናክም።

ይህንን በጎ አላማ በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000480421209

ወይም

በአቢሲኒያ ባንክ
95999328

ደብረ ቁስቋም በማለት በመለገስ ለገዳማውያን እናቶች እህቶች እንድረስላቸው!

ለበለጠ መረጃ፡-0912920992 ፣ 0923289169 ወይም 0986348964

የተፈጥሮን ፀጋ ያለ ስጋት ለገዳማውያን

በምችሉት ቻናል ያላችሁ ሁላችሁም በአምላከ ቅዱሳን ስም እጠይቃለው ለሁሉም አድርሱልኝ
7.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 15:53:42

6.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 06:55:55
የ ጻድቃኔ_ማርያም ቤተልሄም

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
9.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 06:55:44 መዝሙረ ዳዊት

➫ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ
   ➫ መዝሙር፦ ማርያም እንወድሻለን

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            @mezmurochh    
            @mezmurochh    
            @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
8.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 06:55:31 ✞ ማርያም እንወድሻለን

ማርያም እንወድሻለን/2/
ስለወለድሽ የህይወት ምግብን
ማርያም እንወድሻለን

ድክመቴን አትይ…………ማርያም
በሀጢያት መወደቄን……..ማርያም
ተስፋዬ አንቺ ነሽ ……….ማርያም
እስከለተሞቴ …………….ማርያም
ላልከዳሽ ምያለሁ ………..ማርያም
ከስርሽ ላልጠፋ ………….ማርያም
ገፀ በረከቴ ……………….ማርያም
የህይወቴ ዋስትና ………..ማርያም

አዝ_____

የምእመናን ውበት ……....ማርያም
ዘውድ አክሊላቸው ………ማርያም
ድንግል አንቺ እኮ ነሽ …….ማርያም
የመንገድ ስንቃቸው ……...ማርያም
ምስክር ነኝ ለአንቺ ………ማርያም
እንደነብያቱ ………………ማርያም
ስጦታ መሆንሽን …………ማርያም
ለአዳም ልጆች ሁሉ ………ማርያም

አዝ__

ሞገስና ፀጋ ……………ማርያም
በጌታ ፊት ያለሽ ………ማርያም
ዋስ ጠበቃችን ነሽ….….ማርያም
እንዴት ነበር ያኔ …….ማርያም
ጌታን ስትወልጂ ……..ማርያም
የእረኞቹ ደስታ ………ማርያም
የመላእክት ዝማሬ ……ማርያም


                  መዝሙር
         በ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ


  ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

    ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥       @mezmurochh     ✥
    ✥       @mezmurochh     ✥
    ✥       @mezmurochh     ✥
    ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
7.7K views••●◉ Estifanos ◉●••, 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 11:42:34
ጸበለ_ማርያም

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
7.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 11:39:48 ይቅር በላቸው›› አለችው፡፡ በዚኽም ምክንያት በጌታችን ቸርነትና በእርሷም አማላጅነት ብዙ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቷት በክብር ዐረገ፡፡

ዳግመኛም ጌታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ሦስት በትሮችን ሰጥቷት በእነርሱ እየተመረኮዘች እስከሲኦል ድረስ ትሄድና ነፍሳትን ታወጣና ታስምር እንደነበር ራሷ ተናገረች፡፡ ዳግመኛም ስትናገር ‹‹ሰማያውያን ብዙ ስሞች አወጡልኝ፣ ‹የወይን ፍሬ› እያሉ ይጠሩኛል፣ ‹የበረከት ፍሬ› የሚሉኝም አሉ፣ ‹የገነት ፍሬም› ይሉኛል›› አለች፡፡ ዳግመኛም ከልዑል ዘንድ ብዙ ጸጋዎች እንደተሰጣት በሕይወት ሳለች ለአንደ ደገኛ ቄስ ነገረችው፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አምላክን በድንግልና የወለደች ክብርት እመቤታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገለጠችላትና ‹‹ስሜን የተሸከምሽ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን›› አለቻት፡፡ እመቤታችንም ብዙ ምሥጢርን ከነገረቻት በኋላ ጡቶቿንም አጠባቻትና በጸጋ የከበረች አደረገቻት፡፡ በስሟም ብዙ ተአምራትን የምታደርግ ሆነች፡፡

ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ እንደነቢያት የሚመጣውን ሁሉ እንዳለፈ አድርጋ ትናገራለች፡፡ ዳግመኛም የትምህርታቸውን ፍለጋ ስለተከተለችና ለሕጋቸው ስለተገዛች ከሐዋርያት ጋር ዕድል ተሰጣት፡፡ ሦስተኛ ግድ ሳይሏት በፈቃዷ ስለተቀበለቻቸው ግርፋቶቿና ስላገኛት መከራ የሰማዕታት ዕድል ተሰጣት፡፡ ከደናግል መነኮሳትም ዕድል ተሰጣት-መነኩሲትም ድንግልም ናትና፡፡ ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም መልካም የሆነውን ተጋድሎዋን ከፈጸመችና ጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከገባላት በኋላ በሰላም ዐርፋለች፡፡ እንደ ንግሥት ዕሌኒም የሞቷን መስቀል ተሸክማ ተጠብቆላት ወዳለ ተስፋዋ በክብር ሄደች፡፡ ዕረፍቷ መስከረም 18 ነው፡፡ ጥር 18ም ዓመታዊ በዓሏ ነው። ገዳሟ የሚገኘው ጃማ ወረዳ ልዩ ስሙ አህያ ፈጅ ከሚባለው አካባቢ ነው።

የቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣

(ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ጸበለ ማርያም፣ ደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት የንህበት ቅድስት ጸበለ ማርያም ቤ/ክ ያሳተመው፡፡)

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                             
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

ለመቀላቀል  
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
    
@mezmurochh
   
@mezmurochh
   
@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛
7.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 11:39:48 ​✞ ቅድስት ጸበለ ማርያም ​✞

እርሷም በጎኗ ተኝታ የማታውቅ፣ በጌታችን 40 ጾም ወራት ከሰንበት በቀር ምንም የማትቀምስ፣ ነብሮች የእግሯን ትቢያ ይልሱላት የነበረች ታላቅ ኢትዮጵያዊት ቅድስት ናት። ቅድስት ጸበለ ማርያም ጌታችን በደሃ ሰው ተመስሎ ተገልጦ ቁራሽ እንጀራ የለመናት በኃላም በጀርባዋ አዝላ የሸኘችው ታላቅ እናት ናት። እርሷም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ ከደናግል መነኮሳትም ዕድል ተሰጣት-መነኩሲትም ድንግልም ናትና።

ቅድስት ጸበለ ማርያም ትውልዷ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ቀሐ አካባቢ ነው፡፡ ወላጆቿ አባቷ እንድርያስና እናቷ መስቀል ክብራ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር ኮትኮተው አሳደጓት፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተከስተ ብርሃን የተባለ ደገኛ ባሕታዊ ወደ አባቷ ቤት መጥቶ ባደረበት መንፈስ ቅዱስ ኀይል የቅድስት ጸበለ ማርያምን ጸጋ አወቀ፡፡

ለወላጆቿም ‹‹ይኽቺ ልጅ ወደፊት ነፍሳት የሚድኑባት የከበረች ትሆናለች›› ብሎ በእርሷ ላይ ትንቢት ተናገረ፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ በጋብቻ ሕግ እንድትወሰን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ጸበለ ማርያም ‹‹ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር አጭቶኛልና ፈጣሪዬን በድንግልና ለማገልገል ተስያለሁ›› በማለት ተቃወመቻቸው፡፡ ወደ አንድ ደገኛ ባሕታዊም ዘንድ ሄዳ በጸሎቱ ከዚህ ነገር እንዲያድናት ተማጸነችው፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ከጠየቀላት በኋላ ማድረግ የሚገባትንና ወደፊት የሚገጥማትን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ለዕጣን እንዲሆን ጌጧን ሁሉ አውጥታ ሸጠችና ‹‹መሥዋዕቴን አሳርግልኝ›› ብላ ለባሕታዊው ሰጠችው፡፡ እርሱም ከጸለየላት በኋላ የጸሎቱን ምላሽ ነገራት፡፡

ወለጆቿም ያለፈቃዷ በሕግ ቢያጋቧትም ቅድስት ጸበለ ማርያም ግን በሌሊት ማንም ሳያያት ከጫጉላ ቤት ወጥታ ሄዳ በልዳው ፀሐይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች ቤ/ክ ሄዳ እያለቀሰች ጸሎት አደረገች፡፡ እመቤታችንም ከሚካኤል ወገብርኤል እንዲሁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገለጠችላትና እንዲጠብቋት ነገረቻቸው፡፡ ቤተሰቦቿም እንዳያዝኑባት ፈርታ ተመልሳ ወደ ባሏ ዘንድ ብትገባም ባሏ በግብር እንዳያውቃት መላእክቱ ይጠብቋት ነበር፡፡ ባሏንም ሰውነቷ እንደእሳት ያቃጥለው ነበር፡፡ እርሱም አእምሮውን ከሳተ ከ3 ቀን በኋላ ሲነቃ የደረሰበትን ለቤተዘመዶቹ ባስዳቸው ጊዜ ‹‹ከገዳም የመጣች ከሆነች ለእኛ ልትሆን አይገባም›› አሉና አስጊጠውና ሸልመው መልሰው ወደ ቤተሰቦቿ ላኳት፡፡

አባቷም ዳግመኛ ወደባሏ እንድትመለስ በማስገደድ ብዙ አሰቃቂ ግርፋት ቢገርፋትም በተአምራት ምንም እንዳላገኛት ሆነች፡፡ ከዚኽም በኋላ ወጥታ ወደ ምድረ በዳ ሄደች፡፡ ወደ ገዳምም ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ስትጸልይ አድራ አረፍ ስትል ነብር መጥቶ የእግሯን ትቢያ ይልሳት ነበር፡፡ ከዚያም ወጥታ ንህበት ወደሚባል ሀገር መጥታ ቶማስ ከሚባል መነኩሴ ጋር በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ቆማ ስትጸልይ እንባዋ መሬቱን ያርስ ነበር ነገር ግን ሰው እንዳያውቅባት አፈር በላዩ ትጨምርበታለች፡፡ በአንድ ዕለትም በቤ/ክ ቆማ ስትጸልይ በሁለቱ ማዕዘን የተቀበሩ ምውታን ሲጮኹ ሰማቻቸው፣ እነርሱ ግን በሲኦል ነበሩ፡፡ ጩኸታቸውንም በሰማች ጊዜ በእንባዋ ላይ እንባን በጸሎቷም ላይ ጸሎትን ጨምራ ስለእነርሱ ለመነች፡፡ ስለእነርሱም ሱባኤ ያዘች፡፡ በባሕርይው ቸርና ይቅርባይ የሆነ ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ እነዚያን ነፍሳት ማረላት፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም በምግባርና በትሩፋት በጾም በጸሎት ጸንታ ከኖረች በኋላ የምንኩስና ቀንበርን ትሸከም (በመንናኔ ትኖር) ዘንድ በብሕትውና ወደሚኖረው ታላቁ አባት ወደ አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር የደረሰው ነው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያምም ካስተማራትና በኋላ አመነኮሳትና ስሟን ‹‹ጸበለ ማርያም›› ብሎ ሰየማት፡፡ ከዚኽም በኋላ ተጋድሎዋን እጅግ በማብዛት ትሕርምትን ገንዘብ አደረገች፡፡ ከዕንጨት ፍሬዎች ውጭ የማትመገብ ሆነች፡፡ በተቀደሰችው የጌታችን 40 ጾም ወራት ግን ከሰንበት በቀር እርሱንም ፈጽሞ አትቀምስም፣ እስከ ፋሲካም ድረስ ከበዓቷ ስለማትወጣ ማንም አያያትም ነበር፡፡ ከመነኮሰችም ጊዜ ጀምሮ በጎኗ ተኝታ አታውቅም፡፡ ባመማት ጊዜም ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፡፡ በውርጭ ቅዝቃዜ መከራን እየተቀበለች በባሕር ውስጥም ቆማ እየጸለየች ታድራለች፡፡ በስግደቷም በቀን እስከ 8 እልፍ ትሰግድ ነበር፡፡ ከወንድሟ ቶማስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማረች፡፡ የዮሐንስን ወንጌልና የራእዩን መጽሐፍ ዘወትር በማንበብ ትጸልያለች፡፡ የእመቤታችን በዓል በሆነ ጊዜ አርጋኖን ውዳሴዋን በቀን ሦስት ጊዜ ታነባለች፣ አንቀጸ ብርሃንንም በየሰባቱ ጊዜ ትጸልያለች፡፡ የዳዊትንም መዝሙር በፈጸመች ጊዜ የጌታችንን መከራ ግርፋት እያሰበች ራሷን ሺህ ጊዜ ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም አገዛዛቸው መልካም ይሆን ዘንድ ስለ ጳጳሱና ስለ ንጉሡ አንድ አንድ ሺህ ጊዜ፣ ስለ መነኮሳትም ሺህ ጊዜ፣ ስለኃጥአንም ሺህ ጊዜ ራሷን ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም ነጭ ዕጣን በእጇ ይዛ ሰባት ቀን እስኪሆን ድረስ ዕንባዋን ታፈስበታለች፣ ያም ነጭ ዕጣን ከዕንባዋ ብዛት የተነሣ ጥቁር ይሆናል፡፡ በዓል በሚሆንበት በሰባተኛው ቀን አስቀድማ ዐውቃ በመሠዊያ ያሳርገው ዘንድ ያን ዕጣን ለቄሱ ትሰጠዋለች፡፡ እግዚአብሔርም እንደሱራፌል የጽናሕ መዐዛና እንደኪሩቤል ዕጣን ሽታ አድርጎ ከቄሱ እጅ ሲቀበል በግልጽ ታያለች፡፡

ቅድስት እናታችን እሾህ ያለው የብረት ዛንዠር በወገቧ ትታጠቃለች፡፡ በወገቧና በጭኖቿ ያሰረችው ርጥብ የላም ቁርበት ከአጥንቶቿ ጋር ይጣበቃል፡፡ በደረቀም ጊዜ ሥጋዋ እየተቆራረጠ ይወድቃል፣ በምድርም ውስጥ ትቀብረዋለች፡፡ አምስት ጊዜም እንደዚህ እያደረገች ራሷን ጎዳች፣ ከዳነም መልሳ ታቆስለዋለች፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገለጠላትና ‹‹ወዳጄ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእንዲህ ያለ የቁስል መከራ መሠቃየት ይበቃሻል›› ካላት በኋላ ተሰወረ፡፡ እርሷ ግን ሰባት ጊዜ እስኪሆናት ድረስ ይህንን አደረገች፡፡ በዚህም ጊዜ ሥጋዋ እጅግ ታመመ፡፡ ሥጋዋ እንደ ድንጋይ ደርቆ ቢቀር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደተላለፈች ዐውቃ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተወች፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅድስት ጸበለ ማርያም እየጸለየች ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቆሰለ ችግረኛ ደሃ ሰው ተመስሎ ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገልጦ ወደ እርሷ በመምጣት ቁራሽ እንጀራ ለመናት፡፡ እርሷም ፈጥና ይዛ መጥታ ሰጠችው። እንጀራውንም ተቀብሎ ሲያበቃ ‹‹በመንገድ ብዛት ደክሜአለሁና በጀርባሽ አዝለሽ ትሸኚኝ ዘንድ እወዳለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ለድሆች አዛኝ ናትና አዝላው የድንጋይ መወርወሪያ ያህል እንደወሰደችው ቁስሉ ይድን ጀመር፡፡ ወዲያውም ቁስሉ ድኖ ምንም እንዳላገኘው ፍጹም ደህነኛ ሰው ሆነ፡፡ ያንጊዜም ፊቱ እንደፀሐይ አበራ፣ ሁለንተናውም ተለወጠ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ከጀርባዋ ወርዶ በፊት ለፊቷ ቆመና ‹‹የከበርሽ አገልጋዬ ጸበለ ማርያም ሆይ! ምን እንዳድርግልሽ ትወጃለሽ?›› አላት፡፡ እርሷም ከድንጋጤዋ የተነሣ እንደበድን ሆና መሬት ላይ ወደቀች፡፡ ጌታችንም አበረታትና እጇን ይዞ አነሣትና ‹‹የልብሽን መሻት ለምኚኝ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላኬ ሆይ ! በፊትህስ ሞገስ ካገኘሁ በሲኦል ያሉ ነፍሳትን
6.5K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ