Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ዳዊት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurochh — መዝሙረ ዳዊት
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurochh
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 43.70K
የሰርጥ መግለጫ

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
☞ @mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-10-10 10:56:07
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
12.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 11:53:14 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መዝሙረ ዳዊት


ዘማሪ= ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

◦ ድል አለ በስምህ ◦

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
3.2K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 11:53:06 ✞  ድል_አለ_በስምህ

ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድኃኔአለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በረሃ
አለፍነው  ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ስምህ ነው

አዝ____

በእልልታ ቢፈርሰ ኢያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው/2/

አዝ___
  
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማራ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ

አዝ____

የቆምነው ዛሬ በሕይወት
ስምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነህ ነው ክብርና ሞገስ

             ዘማሪ
  ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
3.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 14:00:10 Watch "MK TV ቀጥታ ሥርጭት ከሚሊኒየም አዳራሽ በጦርነት ለተጎዳው ለሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከትን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር - ሰኔ 25 /2015 ዓ.ም." on YouTube
https://www.youtube.com/live/pkjwwiKUf_k?feature=share
5.8K views••●◉ Estifanos ◉●••, 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 22:16:03
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
7.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 22:15:46 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለመፍቀሬ ጥበብ ጠቢበ ጠቢባን ንጉሥ እስራኤል ወልደ ዳዊት ንጉሥ ቅዱስ ሰሎሞን በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ አደረስን

ሰኔ ፳፫(23) ሰሎሞን ወልደ ዳዊት ወአባ ኖብ ወመርቆሬዎስ ወቶማስ ወፊልጶስ ሰማዕት

ዘነግህ ምስባክ

እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉሥ
ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ
ከመ ይኩንኖሙ ለህዝብከ በጽድቅ

ትርጉም

አቤቱ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ
ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ
ሕዝብንም ጽድቅ

       መዝ ፸፩-፩
              71  1

ወንጌል

ማቴ ም ፲፪ ቁ ፴፰-፵፫
           12     38   43

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፲፫ ቁ ፩-፲፫
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፲፫-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፵፬-፶፬

ምስባክ

በጽሑ መላዕክት ወቦሙ መዘምራን
ማዕከለ ደናግል ዘባጥያት ከበሮ
በማኀበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር

ትርጉም

አለቆች ቀነቀኑ መዘምራን ይከተላሉ
ከበሮን በሚመቱ በቁነጃጀት መካከል
እግዚአብሔርን በጉባኤ

       መዝ ፷፯-፳፭
              67   25

ወንጌል

ማቴ ም ፲፩ ቁ ፲፪-ፍ.ም
           11     12  ፍፃሜው

ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ አው ዮሐንስ ዘወልደ ነጎድጓድ

"የኢያሱ የምስክሩ ሐውልት፤የጌዲዎን ፀምር፣የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይና የዘይት ቀንድ አንቺ ነሽ፤የተመካበት የዕሴይ ሥር፤የአሚናዳብም ሠረገላ የዳዊት መሰንቆ የሰሎሞንም አክሊል አንቺ ነሽ፤የታጠረች ተክል፣የተዘጋች የውኃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ "
       ቅዳሴ ማርያም
           ም ፩ ቁ ፴፬
               1     34
  
አው

"ድል ስለነሡ አምነው ንጹሓን ስለሆኑ ስለ ሰማዕታትም ሁሉ፤ተኩሎች እንደ በጎች ስለ በሏቸው ስለ መንጋህ "
     ቅዳሴ ዘወልደ ነጎድጓድ
          ም ፩ ቁ ፶፭
              1     55

ፆሙ ለማበርከት ያብቃን ቸሩ መድኃኔዓለም በምህረቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ምልጃዋ ቃል ኪዳኗዋ ይጠብቅ ከወልደ ዳዊት ከጠቢቡ ሰሎሞን በረከቱ ይደርብን መጽሐፍ ተግሳጽ መጽሐፍ ጥበብ መጽሐፍ መክብብ መጽሐፍ ምሳሌ መኃልይ ዘሰሎሞን ድርሰት የተቀበለ ፆም ፀሎት ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
6.3K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:13:11
ቀዳሜ ትዕይንቱ ለዳግማዊ ምኒሊክ ንጉሰ ነገስት ዘ_ኢትዮጵያ ርዕሰ አድባራት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልይስ ቤ/ክ

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
7.0K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:13:03 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

"ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት ናት "
   ሊቁ አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ቅዳሴ ቤት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረስን

ሰኔ ፳፩(21) በዓለ እግዝእትነ ማርያም ወጢሞቴዎስ ወተዝካር ተአምር ዘቶማስ

ዘነግህ ምስባክ

ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ
ተንሥአ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ
አንተ ወታቦተ መቅደስከ

ትርጉም

እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ
አንተና የመቅደስህ ታቦት

      መዝ ፻፴፩-፯
             131  7

ወንጌል

ሉቃ ም ፩ ቁ ፴፱-፶፯
           1    39   57

የቅዳሴ ምንባባት

ኤፌ ም ፪ ቁ ፲፫-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፬-፲፩
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪-፲፭

ምስባክ

ቀደስ ማኀደሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከለ ኢትትሐወክ
ወይረድአ እግዚአብሔር ፍጽመ

ትርጉም

ልዑል ማደሪያው ቀደስ
እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም
እግዚብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል

     መዝ ፵፭-፬
            45  4

ወንጌል

ማቴ ም ፲፮ ቁ ፲፫-፳
           16     13  20

ቅዳሴ

ዘእግዚእነ

❖ አቤቱ ለአዕይንተ ልቡና ውስጣዊ ብርሃንን ስጥ እያስቡህና ላንተ እየተገዙ አንተን ለይተው ያመስግኑህ ዘንድ ዕድላቸው አንተ ብቻ ነህና ❖
      ቅዳሴ እግዚእነ
       ም ፩ ቁ ፶፬
           1     54

በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ ሐሴት ያድርግል ፆሙ ለማበርከት ያብቃ ከቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ ቃል ኪዳኗዋ ይጠብቅን ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም የሰኔ ጎልጎታ መዓዛ ቅዳሴ የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ስግደት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
6.6K views••●◉ Estifanos ◉●••, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 22:12:30
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
6.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, edited  19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 22:12:18 ይህም ነቢይ በአራት ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ እሊህም ኢዮራም፣ አካዝያስ፣ ኢዩና፣ ዮአስ ናቸው የትንቢቱም ዘመን ከሀምሳ ዓመት በላይ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ከመምጣቱ አስቀድሞ ትንቢት ተናገረ ከዚህ በኋላም በሰለም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ ልመናዋ በረከቷም ወንዶችና ሴቶች ባሮቿ ከሆን ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር፣ በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                             
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

ለመቀላቀል  
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
    
@mezmurochh
   
@mezmurochh
   
@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛
6.1K views••●◉ Estifanos ◉●••, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ