Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለመፍቀሬ ጥበብ ጠቢበ ጠቢባ | መዝሙረ ዳዊት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለመፍቀሬ ጥበብ ጠቢበ ጠቢባን ንጉሥ እስራኤል ወልደ ዳዊት ንጉሥ ቅዱስ ሰሎሞን በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ አደረስን

ሰኔ ፳፫(23) ሰሎሞን ወልደ ዳዊት ወአባ ኖብ ወመርቆሬዎስ ወቶማስ ወፊልጶስ ሰማዕት

ዘነግህ ምስባክ

እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉሥ
ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ
ከመ ይኩንኖሙ ለህዝብከ በጽድቅ

ትርጉም

አቤቱ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ
ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ
ሕዝብንም ጽድቅ

       መዝ ፸፩-፩
              71  1

ወንጌል

ማቴ ም ፲፪ ቁ ፴፰-፵፫
           12     38   43

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፲፫ ቁ ፩-፲፫
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፲፫-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፵፬-፶፬

ምስባክ

በጽሑ መላዕክት ወቦሙ መዘምራን
ማዕከለ ደናግል ዘባጥያት ከበሮ
በማኀበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር

ትርጉም

አለቆች ቀነቀኑ መዘምራን ይከተላሉ
ከበሮን በሚመቱ በቁነጃጀት መካከል
እግዚአብሔርን በጉባኤ

       መዝ ፷፯-፳፭
              67   25

ወንጌል

ማቴ ም ፲፩ ቁ ፲፪-ፍ.ም
           11     12  ፍፃሜው

ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ አው ዮሐንስ ዘወልደ ነጎድጓድ

"የኢያሱ የምስክሩ ሐውልት፤የጌዲዎን ፀምር፣የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይና የዘይት ቀንድ አንቺ ነሽ፤የተመካበት የዕሴይ ሥር፤የአሚናዳብም ሠረገላ የዳዊት መሰንቆ የሰሎሞንም አክሊል አንቺ ነሽ፤የታጠረች ተክል፣የተዘጋች የውኃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ "
       ቅዳሴ ማርያም
           ም ፩ ቁ ፴፬
               1     34
  
አው

"ድል ስለነሡ አምነው ንጹሓን ስለሆኑ ስለ ሰማዕታትም ሁሉ፤ተኩሎች እንደ በጎች ስለ በሏቸው ስለ መንጋህ "
     ቅዳሴ ዘወልደ ነጎድጓድ
          ም ፩ ቁ ፶፭
              1     55

ፆሙ ለማበርከት ያብቃን ቸሩ መድኃኔዓለም በምህረቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ምልጃዋ ቃል ኪዳኗዋ ይጠብቅ ከወልደ ዳዊት ከጠቢቡ ሰሎሞን በረከቱ ይደርብን መጽሐፍ ተግሳጽ መጽሐፍ ጥበብ መጽሐፍ መክብብ መጽሐፍ ምሳሌ መኃልይ ዘሰሎሞን ድርሰት የተቀበለ ፆም ፀሎት ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥