Get Mystery Box with random crypto!

✞  ድል_አለ_በስምህ ድል አለ በሰምህ ድል አለ በቃልህ /2/ ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ ባ | መዝሙረ ዳዊት

✞  ድል_አለ_በስምህ

ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድኃኔአለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በረሃ
አለፍነው  ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ስምህ ነው

አዝ____

በእልልታ ቢፈርሰ ኢያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው/2/

አዝ___
  
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማራ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ

አዝ____

የቆምነው ዛሬ በሕይወት
ስምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነህ ነው ክብርና ሞገስ

             ዘማሪ
  ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥