Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የሰርጥ አድራሻ: @keabawandebet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው እሮብ እና ቅዳሜ ብቻ ይጠብቁን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-01-01 08:34:49
108 views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 21:11:52 እኔን አዳምጡ እስኪ









366 views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 18:07:51
#ይዘዙን!

በፈለጉት ዲዛይን በጥራት እንሰራለን !

  #ከአልባሳት

➛ #ጋቢ እና #ፎጣ
➛ #ነጠላ እና #አልጋ ልብስ እና ለሴቶች የእጅ ቦርሳ በፈለጉት ዲዛይን እና ጥለት እንሰራለን

➻ #ቲሸርት እና #ሱሪ ባማረ ዲዛይን እንሰራለን

(#ለበዓላት፣ #ለፅዋ ማህበር፣#ለሰርግ፣ #ለልደት)በብዛት ካዘዙን በሚፈልጉት ቀን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እንሰጥዎታለን !

መጪው #ጥምቀትም አይደል ? ቲሸርት ለማሰራት ወደ አዲስ አበባ መሄድ አይጠበቅብዎትም ! ከወዲሁ ወደኛ ጎራ ብለው የፈለጉትን ዲዛይን መርጠው ይዘዙን! በጥራት እና  በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራልዎታለን!
   
➤ለመምህራን እና ለህክምና ባለሙያዎች #ጋዎን እናዘጋጃለን !!

      የንፅህና መጠበቂያ
ቆሻሻን ድራሹን የሚያጠፉ
➛ #የልብስ ሳሙናዎች
➛እና ወደር የሌለው #ፈሳሽ ሳሙና እና #ላርጎ እኛጋ አለ።

➛አልኮል እና ሳኒታይዘር አለን!

#ጧፍ እና #ሻማ ከፈለጉ በብዛት እና በጥራት አምርተን እናቀርብልዎታለን !

ዋጋቸው እጅግ ተመጣጣኝ ! በጥራት ደግሞ አንደራደርም !

 
ኑ !  የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸመት ገዳሙን ይደግፉ!

የጂንካ አንቀፀ ብፁኣን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም !!

የገዳሙ አስተዳደር  የአባ ኤፍሬም

+251989810622
306 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 20:26:33 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት

ክፍል ሁለት

ነገር ግን ነገሥታት ሰማያዊውን የክብር አምላክ ሊያመልኩ መጡ፤ ወታደሮች የኃይል አዛዥ የሆነውን እርሱን ሊያገለግሉት መጡ፤ ሴቶች ከሰው የተወለደው ኀዘናቸውን ወደ ደስታ እንዲቀይርላቸው ሊያዩት መጡ።

ደናግላን የድንግልን ልጅ ሊያዩ መጡ ። ምክንያቱም የጡትን ምንጭ እንደሚፈስ ወንዝ የሚያደረገውን የጡትና የወተት ፈጣሪ ከድንግል እናቱ የልጆችን ምግብ ተመግቧልና ።

ሕፃናት ከሕፃናት አፍ ምስጋናን ለመቀበል ሕፃን የሆነውን ለማየት መጡ።

ጨቅላዎች በሄሮድስ ክፋት ምክንያት ምስክር የሆነውን ጨቅላ ሊያዩት መጡ ።

ወንዶች ሰው የሆነውንና የባሮችንም ኀዘን ያጠፋውን ለማየት መጡ።

እረኞቹ ለበጎቹ ብሎ ሕይወቱን የሚሰጠውን መልካም እረኛ ለማየት መጡ።

ካህናት በመልከ ጸዴቅ ሥርዓት ሊቀ ካህን የሆነውን ለማየት መጡ።

ባርያዎች ባርነትን በነጻነት ሊያከብር ፣ የባሪያን መልክ[2] የያዘውን ለማየት መጡ።

ዓሣ አጥማጆች ከዓሣ አጥማጆች መሐል የሰው አጥማጅ የሚያደርገውን እርሱን ሊያዩት መጡ።

ቀራጮቹ ከቀራጮች መሐል ወንጌላዊውን የሾመውን ለማየት መጡ።

ዘማውያን ለዘማዊቷ ዕንባ እግሩን የሚሰጠውን ለማየት መጡ።

ግልጽ አድርጌ እንዲህ ብዬ ልናገር ሁሉም ኃጢአተኞች የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔርን በግ ለማየት መጡ።

ሰብዓ ሰገል አብረው ሆነው፣ እረኞች እያመሰገኑ፣ ቀራጮች መልካሙን ዜና እየተናገሩ፣ ዘማውያን ሽቱ ይዘው፣ ሳምራውያን የሕይወትን ምንጭ እየተጠሙ፣ ከነናዊቷ ሴት ጥርጥር በሌለበት እምነት የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔርን በግ ሊያዩ መጡ።

ሁሉም ሰው እየፈነጠዘ ስለሆነ እኔም መፈንጠዝና ማሸብሸብ በዓሉን ማክበርና መደሰት እፈልጋለሁ።

ነገር ግን እኔ የምዘምረው ክራር በመምታት ፣ ጸናጽል በመጸንጸል ፣ ዋሽንት በመንፋት ወይም ችቦ በመለኮስ አይደለም ።

እኔ ግን በዝማሬ መሳሪያዎች ፈንታ የክርስቶስን መጠቅለያ ጨርቅ በመልበስ እንጂ።

ይህ ተስፋዬ ነው፣ ሕይወቴ፣ ድኅነቴ፣ ክራሬና ዋሽንቴ ነው።

ስለዚህ እነዚህን ለብሼ እመጣለሁ በዚህም በእነርሱ ኃይል የቃላትን ኃይል ተቀብዬ ከመላእክቱ ጋር አብሬ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን” እያልኩ ከእረኞቹ ጋር ደግሞ “ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” (ሉቃ 2፥14) እላለሁ።

ይቀጥላል

https://t.me/KeAbawandebet
319 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 19:12:05 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት

አዲስና እንግዳ የሆነ ምሥጢር ይታየኛል፤ እረኞቹ ባዶ የሆነ ድምፅ ሳይሆን የመላእክትን ዝማሬ ሲዘምሩ በጆሮዬ ይሰማኛል።

እግዚአብሔርን በምድር የሰውን ልጅ ደግሞ በሰማይ አይተዋልና መላእክት ይዘምራሉ፤ ሊቃነ መላእክት ያሸበሽባሉ፤ ኪሩቤል ይዘምራሉ፤ ሱራፌልም እያመሰገኑ ሁሉም በአንድነት በዓሉን እያከበሩ ነው።

ከፍ ያለው እርሱ በቀደመው ምክሩ ራሱን ዝቅ አደረገ ። ያ ዝቅ ብሎ የነበረው ሥጋ ደግሞ ለሰው ልጅ ባለው ፍቅር ምክንያት ከፍ አለ።

ዛሬ ቤተልሔም ሰማይ መስላለች ፣ በከዋክብት ፈንታ የመላእክትን ዝማሬ ተቀበለች፤ በፀሐይ ፈንታ ጻድቁን ሳትወስነው ያዘችው። እንዴት እንደሆነ አትጠይቁ ።

እግዚአብሔር ሲፈቅድ /ሲያዝ/ የተፈጥሮ ሕግ ይሻራል።

እርሱ ስለ ፈቀደ ስለ ወደደና ሥልጣን ስላለው ወረደ ፣ አዳነን ። ሁሉንም ነገር ደግሞ እግዚአብሔር ላይ እንዲመሠረት አደረገ ።

ዛሬ ከጥንት ጀምሮ የነበረው እርሱ ተወለደ ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበረውም ያልነበረውን ሆነ ።

እርሱ አምላክነቱ ሳይለቅ እግዚአብሔር ሳለ ሰው ሆነ ። እርሱ ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ አልተለየም።

በተመሳሳይ መልኩም እግዚአብሔር የሆነው ከሰውነት በማደግ አይደለም ።

ነገር ግን አካላዊ ቃል ሆኖ ሳለ መከራ ሊቀበል ስለማይችል ባሕርይው ሳይቀየር ሰው ሆነ።

ነገር ግን በአንድ መልኩ ተወልዶ ሳለ አይሁድ እንግዳ የሆነ ልደቱን አልተቀበሉም ።

ፈሪሳውያን ደግሞ አምላካዊ መጻሕፍትን አሳስተው ተረጎሙ፣ ጸሐፍትም ሕጉ ላይ ከተጻፈው በተቃራኒው ተናገሩ።

ሄሮድስ የተወለደውን ሕጻን ሊያከብረው ሳይሆን ሊገድለው በማሰብ ፈለገው።

ዛሬ ግን ሁሉም ነገር እነርሱን እንደሚቃረናቸው አዩ። መዝሙረኛው እንዲ

መዝሙረኛው እንዲህ ይላል፡- “ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም” (መዝ 78፥4)።

ነገሥታቱ በሰማያዊው ንጉሥ ተደንቀው ሊያዩት መጡ። እርሱ መላእክትንና ሊቃነ መላእክትን፣ ኃይላትን፣ ዙፋናትን፣ አጋእዝትን፣ ሥልጣናትን ሳያስከትል እንግዳ በሆነና ባልተለመደ መንገድ መጥቷል።

እርሱ መላእክቱን ከሥልጣኑ ውጭ ሳያደርጋቸው[1] በመሐላችን ሰው ሲሆንም አምላክነቱን ሳይተው ዘር ካልተዘራበት ማኅፀን ወጣ።

ይቀጥላል

https://t.me/KeAbawandebet
303 views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 20:33:13 ምን ላድርግ ?

አባ ፓምቦ አባ እንጦንስን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “ምን ላድርግ ?” ሽማግሌውም እንዲህ አለው ፡- “በራስህ ጽድቅ አትተማመን ፣ ስላለፈው ድርጊትህ አትቆጭ ፣ ምላስህንና ሆድህን ተቆጣጠር ።”

ብዙ ዘርተው ጥቂት ማጨድ ያቃታቸው ፣ ፍቅር ሰጥተው ስድብ የተመለሰላቸው ፣ ለማስደሰት ሞክረው ሰዎች የተከፉባቸው ፣ የቤታቸውን ጣራ በጠገኑ ቊጥር ያፈሰሰባቸው ፣ መልካም ለመሆን ሞክረው አስመሳይ የሚል ስም የተሰጣቸው ፣ ሲያጠፉም ሲያለሙም ምስጋና የተነፈጋቸው ፣… “ምን ላድርግ ?” በማለት ግራ የመጋባት ጥያቄ ያቀርባሉ ። አባ ፓምቦ ግን “ምን ላድርግ ?” ያለው ለእግዚአብሔር ለመኖር ፣ ለወደደው አምላክ የተመረጠውን ለማድረግ አስቦ ሲሆን ፣ ጥያቄ ግራ የመጋባት ሳይሆን ቀኙን የመምረጥ ነው።

ሁለት የደነዙ ቢላዎች እንኳ ሲሳሳሉ ምላጭ ይሆናሉ ። ሁለት የበረቱ አባቶችማ እርስ በርሳቸው ሲመካከሩ ይኸው ለትውልድ የምክር ብርሃን ይፈነጥቃሉ ። ድንጋይና ድንጋይ ፣ እንጨትና እንጨት እንኳ ሲፋጭ እሳት ይወጣቸዋል ። የተቀደሱ አባቶችማ ሲጠያየቁ ረቂቅ የሆነው መንፈሳዊ ኑሮና መንፈሳዊ ውጊያ ፍንትው ብሎ ይብራራል ። አባ ፓምቦ አባት ቢሆንም ከአባ እንጦንስ ለመመከር ዝቅ ያለ ነበር ። ለመሞላት ዝቅ ማለት ያስፈልጋል ። ከወራጁ ከፍ ያለ ማድጋ አይሞላም ። ዝቅ ያለና ባዶ ሁኖ የቀረበ ማሰሮ ግን ይሞላል ። በዚህ ጨለማ ባጠላበት ዓለም ላይ የቅዱሳን አባቶች ምክር የሚመራ ኮከብ ነው ። ኮከቡም የሚያደርሰው ክርስቶስ ጋ ነው ። ክርስቶስ ጋ የደረሰም ይሰግዳል ፤ ያለውን ሁሉ ይሰጣል ።

ከመደበኛ የትምህርት መርሐ ግብር ለየት ያለው ጥያቄና መልስ ያለው መማማር ነው ። ጥያቄና መልስ መምህርና አስተማሪውን የሚያሳትፍ ትልቅ የትምህርት መርሐ ግብር ነው ። መምህሩ በውስጡ የተደበቀውን እውቀት የሚያወጣው በጥያቄ ነው ። የመምህሩ መደበኛ ትምህርት ለተማሪዎቼ “ይህ ያስፈልጋቸዋል” ብሎ ያቀረበው ማዕድ ሲሆን ጥያቄ ግን ተማሪው “ይህ ያስፈልገኛል” ብሎ ያማረው ምግብ ነው ። ጥያቄ የተማሪ የነጻነት ሜዳ ነው ። የማይረሱ ትምህርቶች በጥያቄና መልስ የሚሰጡ ናቸው ። አስተማሪው ተማሪውን የሚያውቅበት ፣ የራሱን እውቀትና ምን ያህል ማስተማሩን የሚለካበት ሚዛን ጥያቄ ነው ። ጥያቄ አስተማሪ ይበልጥ እንዲያነብ ያደርገዋል ። የሚጠይቅ ተማሪ ሲጠይቅ አላውቅም እያለ ነውና ጥያቄ ትሑት ያደርጋል ። በርግጥ ለፈተና የሚጠይቁ ያልታደሉ ወገኖች አሉ ። ጥያቄ ተማሪና አስተማሪን ያቀራርባል ። የምናመልከው አምላክ ጥያቄን የሚፈራ አምላክ አይደለም ።

አባ ፓምቦ፡- “ምን ላድርግ ?” ብሎ ጠየቀ ። ይህ ጥያቄ የእውቀት ጥያቄ ሳይሆን የመለወጥና ክርስትናን ተጨባጭ የማድረግ ጥማት ነው ። ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ሃምሳ ሲያስተምር በትምህርቱ የተነካው ሕዝብ፡- “ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት፡- ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው።” የሐዋ. 2፡37 ። ምን ላድርግ ? ማለት ልብ ሲነካ የሚቀርብ ጥያቄ ነው ። አንድ ሰው የክርስቶስ ፍቅር በልቡ ውስጥ ሲጠልቅ ምን ላድርግ ? ይላል ።

አባ እንጦንስ ካስተላለፈው ምክር አንዱ፡- “በራስህ ጽድቅ አትተማመን” የሚል ነው ። “ምን ላድርግ ?” ለሚል ጥያቄ ስላለፈው አድራጎትህ አትተማመን የሚል መልስ መስጠቱ የሚገርም ነው ። ለቀጣይ አድራጎት ለተጠየቀ ጥያቄ መልስ ተደርጎ የተሰጠው ያለፈው በጎነትህ ላይ አትተማመን የሚል ነው ። የቅዱሳን አባቶች ሁሉ የሠመረ ጎዳና በራሳቸው በጎነት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ መደገፋቸው ነው ። ነቢዩ ዳዊት፡- “ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” ብሏል ። መዝ. 15 ፡ 2 ። በራስ ጽድቅ መተማመን ባለፈው ያንን አልፌዋለሁ ብሎ አሁን ግን አልወድቅም በሚል ስሜት መዘናጋትም ነው ። በራስ ጽድቅ መተማመን ማለት ሌሎች ላይ መፍረድና እኔ እሻላለሁ ብሎ ማሰብ ነው ።

አባ እንጦንስ ሁለተኛው ምክሩ፡- “ስላለፈው ድርጊትህ አትቆጭ” የሚል ነው። ባለፈው ድርጊትና በተናዘዙበት ስህተት መቆጨት ራስን እየመረዙ መኖር ነው ። “እንዴት እኔ ይህን አደርጋለሁ ?” ማለትም መመጻደቅ ነው ። ሌሎች የሚሠሩትን ስህተት ካልሠራን እግዚአብሔር ስለረዳን እንጂ የማይሠራ ሥጋ ስለተሸከምን አይደለም ። “ባለፈ ክረምት ቤት አይሠራም” እንደሚባል ባለፈው ዘመን መቆጨት ያለውን ዘመን ማቃጠል ነው ። እግዚአብሔር ይቅርታ እንዳደረገልን ካመንን ከኅሊናችን ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልገንም ። “የአንድ ግብ መድረሻ ለሌላ መነሻ ነው” ይባላል ። ንስሐም የኃጢአት መጨረሻ የጽድቅ መነሻ ነው ። ስለ ክፉ አድራጎት መጸጸት በራሱ በጎነት ነው ። እየተጸጸቱ መኖር ግን በእግዚአብሔር አለማመን ነው ። የሚመለስ ሰው እንጂ የማይበድል ሰው አይደለንም ።

“ምላስህንና ሆድህን ተቆጣጠር” ሦስተኛው ታላቅ ምክር ነው ። ምላስ ባለቤቱን አስሮ የማስቀመጥ አቅም አለው ። ሕይወትና ሞትም በአንደበት ላይ ነው ። የምንጓዘው ወደ ተናገርነው ነው ። ስለዚህ ምላስን መቆጣጠር ይገባል ። ሆድን መቆጣጠርም ለመንፈሳዊና ለሥጋዊ ጤንነት ወሳኝ ነው ። ተገኘ ተብሎ መብላት ፣ እንደ ዔሳው ለምግብ ጎምዥቶ ብኵርናን መሸጥ አይገባም ። ፍላጎት ገደብ ከሌለው በምድር በሰማይ ከርታታና የማይረካ ሰው ያደርገናል ። መቆጣጠር በጥንቃቄ መኖርን የሚያመለክት ነው ። ጠቢቡ፡- “ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል” ይላል ። ምሳሌ 2፡11 ።

ጌታ ሆይ ፣ በአንደበቴ ሳይሆን በልቤ የታዘብኩት እንኳ ፈተና ሁኖ ይመጣብኛል ። አለሁ ስል ይበልጥ አልኖርም ። ስምል ፣ ስገዘት የበለጠ እወድቃለሁ ። አምላኬ ትላንት የዛሬውን ሕይወቴን እንዲያውክ ፈቅጄለታለሁ ። በአንደበቴ ላይም ገና ባለሥልጣን አልሆንሁም ። እባክህን ጌጠኛውን የጽድቅ መጎናጸፊያ አልብሰኝ ።

በዘላለማዊ ክብርህ አሜን ።

ለተጨማሪ ትምህርቶች Add ማድረግ ይቻላል

https://t.me/KeAbawandebet
280 viewsedited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 20:50:26 እውነት ነው የምላችሁ አንብብ እና የሰላም እንቅልፍ ተኙው

አስታዋሽ አምላኬ ሆይ

የሥነልቦና ባለሞያ Bini Girmachew  እንደፃፈው

      በተደነቀ ዝምታ  የምትኖር አስታዋሽ ፈጣሪ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ በዝምታህ ውስጥ መልስ አለህና አከብርሃለሁ፡፡

እንደማይሰማ ዝም ብትልም፣ እንደማይሰጥ ብትዘገይም፣ እንደማይገደው ብታልፍም ዓላማ አለህና ተመስገን፡፡ የቀኑን ምልክት በማየት አለባበሴን ባስተካክልም፣ የዘመኑ ምልክት ግን ሳይገባኝ በአንደበቴ ጠፍቻለሁና አድነኝ፡፡ ዓለም ስትንጫጫ ዝም ማለትን አስተምረኝ፡፡
    
     እውነት ስናገር ሰዎች ይከፋቸዋል፣ ሐሰት ስናገር ፍቅርህ ያዝንብኛል፡፡ እባክህ የአንተ ወገንተኛ አድርገኝ፡፡ ያንተ ወገን በሁለት ወገን እንደተሳለው ቃልህ ለማንም አይመችም፡፡

መተማመን በጠፋበትና ቋንቋ  በተደባለቀበት ዘመን የልቤና የአንደበቴ ጠባቂ ሁን፡፡ በሰነፎች ዘመን ጠቢብ አድርገኝ፡፡

ውዴ ሆይ፡ የሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ንግግር እንዳያናግረኝ እባክህ ተቆጣጠረኝ፡፡

     ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ ከሚሉ ግትሮች ጠብቀኝ፣ እኔም ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ በሚል የሕይወት ጠንቅ ውስጥ እንዳልገባ ያዘኝ፡፡

ሥጋዬን አላምነውምና መንፈስህ ይምራኝ፡፡ የገዛ ፍቅሬ እንጂ ሌሎችን መጥላት ከማንም ጋር እንዳያፋቅረኝ ተጠንቀቅልኝ፡፡ ያምራል ብዬ ከተናገርኩት ይከፋል ብዬ የተውኩት እንደሚሻል አሳየኝ፡፡

ዘላለም የሚጸናው የአሁኑ ሳይሆን ያንተ ሥርዓት መሆኑን ግለጥልኝ፡፡ ለስሜቴ የሚስማማኝን እየመረጥኩ ቃልህን እንዳልታዘዝ እማጸንሃለሁ፡፡

     ተስፋህ ተስፋ ያደረኳቸውን ነገሮች ሁሉ ይውረሰው፡፡ ሰዎች እንዲያምኑኝና ፍትሐዊ ነው እንዲሉኝ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፡፡

አንተ ትበቃኛለህና ልቤን በጥላህ አኑረው፡፡ በማስፈልግበት ሰዓት እንዳልተኛ እርዳኝ፡፡ ሰው ሁሉ የመፍራት ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሲፈራ እኔን በዓለት ላይ አቁመኝ፡፡

ሰዎች ሲያዘምሙ ሳይ ነቢይ እንዳልሆን ጠብ ቀኝ፡፡ ካንተም ይልቅ ቸር እንዳልሆንኩ አስረ ዳኝ፡፡ እገሌ በደለ እንጂ እኔ በደልኩ የማይልን አገርና ትውልድ ፈውስ፡፡ የመካሰስ ወራትን በይቅር  ነፋስ ለውጥ፡፡

     በአገራችን ሁሉም ሊቅ ነውና የሚማር መንፈስን ስጠኝ፡፡ የሰዎች ርእስ ያልሆኑትን የተረሱትን አንተ አስታውስ፡፡

ኃያላን ሲጣሉ እኛ እንዳንደቅ አውጣን፡፡ በደግ ቀን ያልጸለዩት በክፉ ቀን አይረዳምና በጸሎት አትጋኝ፡፡

አስቤ እንድናገር ሊቃውንት ነግረውኛል፡፡ ነገር ግን አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ለሰውዬው የምትናገረውን እንድናገር እርዳኝ፡፡

የጥያቄዎች ሁሉ መልስ «አምላኬ በእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?» የሚለው መሆኑን አብራልኝ፡፡

ጣዕም ባለው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።

የማይሾሙህ ንጉሤ

     ከከበሩት በላይ ከብረህ የምትኖር የማይ ሾሙህ ንጉሤ፣ የማያበድሩህ ብልጥግናዬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ ዓመታት ዘመናት ብዙ ወዳጆቼን ሲለውጡ እኔም በብዙዎች ስለወጥ አንተ ግን ያው አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ፡፡

ልብስ የሸፈነውን ጓዳዬን፣ ጥርስ የሸፈነውን ልቤን ላንተ እገልጣለሁ፡፡ ልትረዳኝ አቅምና ፈቃድ ላለህ ላንተ መሸነፌን አወራለሁ፡፡ አንተ እንደ ሰው አልፎ ሂያጅ አይደለህምና እመካብሃለሁ፡፡

     ሰው ሁሉ ራሱንና አካባቢውን በሚያ ዳምጥበት ዘመን ቃሌ አይሰማምና እባክህ አንተ ስማኝ፡፡

ፍቅርና መልካምነት የራቀኝ የትዝታ ሰው ሆኛለሁና ዘመኔን እንደ ቀድሞው አድስ፡፡ ሰው በተሰለቻቸበት ዘመን የማይጠገብ ፍቅር ስጠኝ፡፡ ክፉን በክፉ ሳልመልስ በመልካም ማሸነፍን አድለኝ፡፡

     በፀፀት የትላንትናውን፣ በንዴት የዛሬን ከመመልከት በእምነት የወደፊቱን እንዳይ እባክህ እርዳኝ፡፡ በማየው ተወስኛለሁና የተስፋ አገሬን አጉላልኝ፡፡

ሰው በሰው ሆኖ ሲጠቃቀም እኔ ግን ካንተ በቀር የምጠራው የለምና ድረስልኝ፡፡ ሰዎችን በፍጹም ልቤ እንድወዳቸው እርዳኝ፡፡ ሰዎችም እኔን በመውደድ እንዳይፈተኑ አግዛቸው፡፡ ቃላት ቆርጣሚ አማርኛ ሰንጣቂ ከመሆን እውነት ቀማሽ አድርገኝ፡፡ ሰዎች ቋንቋን ያዳምጣሉ፣ አንተ ግን አሳቤን ተረዳልኝ፡፡

ሁሉም ወደ ራሱ አሳብ ሲያዘነብል እኔን ግን በአሳብህ ማርከኝ፡፡ ባልንጀርነትና ትዳር ባቢሎን ሲሆን ለእኔ ግን ቋንቋዬ ሁንልኝ፡፡ የሰው አንደበት ያቆስላል፣ የሚያዩት የሚሰሙት አያስደስትምና ለእኔስ ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል፡፡

     ንጹሕ ምንጭ እንደሚደፈርስ የብዙ በጎ ሰዎች አእምሮ ደፍርሷልና እባክህ አድነኝ፡፡

ከልብ የሚያመልኩህ ሳይበላሹብህ ውሰዳቸው፡፡ የሃይማኖት ቃላችንን ማንም ሊሰማው ጠልቷልና ደግ ዘመን አምጣልን፡፡ ራሴን በቃልህ እንጂ በደከመው ወንድሜ እንዳልመዝን እርዳኝ፡፡ በሚያስጠጋው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።
በምስጋና ተውበህ

     በክብር ደምቀህ፣ በምስጋና ተውበህ፣ በአእላፋት ተከበህ፣ በኪሩቤል ጀርባ ነግሠህ የምትኖር የማትወሰን፣ ለሁሉ ወሰን የሰጠኸው አምላኬ  ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡

ለዚህ ሁሉ ፍጥረተ ዓለም ምክንያቱ አንተ ነህ፣ አንተ ግን ምክንያት ሳትሻ ትኖራለህና አከብርሃለሁ፡፡

     እንደ ወደድኸኝ ልወድህ አልችልም፣ እንዴት እንደወደድከኝ እንኳ የፍቅርህን ልክ ማወቅ ተስኖኛልና እባክህ አግዘኝ፡፡

ባምነው መንግሥተ ሰማያት እገባለሁ፣ ብክደው ገሀነመ እሳት እወርዳለሁ ብዬ ሳይሆን ወዶኛል ሞቶልኛል ብዬ እንድከተልህ እርዳኝ፡፡

አቅሜን አላውቅምና በፍቅር አቅሜን አሳውቀኝ፡፡ በመሰበር መማር አይረሳም፣ እኔን ግን በመውደድህ አስተምረኝ፡፡

ሰው ሁሉ  ለመከራው አያቅድም፡፡ መከራ ግን በሰው ላይ ያቅዳልና ይሆናል ብዬ መጠበቅንም አስተምረኝ፡፡

የምወዳቸው ያለ ችግር እንዲሆኑ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፣ አይሳካምና፡፡ ለማንም ካንተ በላይ ደግ እንዳልሆንኩ አሳውቀኝ፡፡ የማልፍበትን የኑሮ ገጽ  ሁሉ «ይህም ሕይወት ነው» እንድል አሰልጥነኝ፡፡

ፀጥታ ረብሻ ሲሆን አጽናኝ፡፡ ማንም እንዳይደርስብኝ የከለልኩት የፀጥታ ሰዓቴን ለተጨነቁት ማዋልን አድለኝ፡፡

ራስን በማዳመጥ ሳይሆን ሌሎችን በመርዳት ያለውን ደስታ ግለጥልኝ፡፡

የማላደርገውን እንዳልናገር፣ የተናገርኩትን እንድፈጽም፣ ከሁሉ በላይ ተስፋ ሰጪ ሰው እንድሆን እለምንሃለሁ፡፡ ሰውን የሚያህል ፍጡር በማይፈጸም «እሽ» እንደ ዶሮ እንዳላባርር ማስተዋል ስጠኝ፡፡

«አይሆንም» በጊዜው ጥሩ መልስ መሆኑንም ግለጥልኝ፡፡

ጌታዬ ሆይ ምንም ባስቸግርህ ለፍላጎቴ አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡ ከሚያፀፅት ሕሊና አድነኝ፡፡

ሥጋዬ የበላይ ሆኖብኛልና አንተ ግዛኝ፡፡ ላንተ ከመገዛት ውጪ ሌላ አሳብ የለኝም፡፡ ለመታዘዝ ግን ፍላጎት እንጂ አቅም የለኝምና ጸጋህንና የጸጋ ስጦታህን ላክልኝ፡፡

አውቄህ እንዳላወቀህ ከመሆን አድነኝ፡፡ ለዚህ የእንግድነት ኑሮ እንዳልረሳህ ከራሴ ጠብቀኝ፡፡ ምናልባት ነገ ብትመጣ ከነኃጢአቴ እንዳታገኘኝ ነጩን ሸማህን አልብሰኝ፡፡

ወደ ፍጡራን ብጠጋም ጽድቃቸው ለራሳቸውም አልበቃቸውም፣ አንተው በሚተርፈው ጽድቅህ አጽድቀኝ፡፡

በማይታበለው እውነትህ ለዘላለሙ አሜን፡፡


Bini Girmachew ( ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን) 

YouTube ሰብስክራይብ ለማድረግ ይሄን ሊንክ

ይጠቀሙ!!

  
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w

@Bini_Girmachewbot @BiniGirmachew


የነገ ሰው ይበለን
454 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 23:30:17
እንኳን አደረሰን
137 views20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 06:51:36
በጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ነዉ ያለዉ

የኬንቼው ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የንግድ ባንክ
አካውንት   ➯

1000261754987

ሁላችሁም እኅት ወንድሞች የተጀመረውን ቤተክርስቲያን ከፍጻሜ እናደርስ ዘንድ እናት ቤተክርስቲያን እኛን ልጆቿን ትጠይቃለች።

ለተጨማሪ መረጃ  ዲያቆን በሀይሉ  በማለት መደውል  በተጨማሪም እቃ መግዛት የምትችሉ  ለሱ መስጠት ትችላላችሁ

091 070 8770
4.8K views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 06:36:07
ዛሬ የነቢያት ፃም (የገና ፃም) ተጀምራል።

በዚህ ፃም ሰለተራቡ፣ስለ ተጠሙ፣ ስለታረዙና ስለተሰደዱ ሰዎች ስለሃገራችንም
ሰላም አበክረን የምናስብበት ወቅት ነው።

ለጥቂት ደቂቃ በዚህ ህይወት ያሉትን ወገኖች እናስባቸው መልካም የፃም ወራት
ይሁንላችሁ የንስሀ ፍሬ የምናፈራበት ለስጋ እና ደሙ የምንበቃበት ያድርግልን አሜን

@KeAbawandebet
@KeAbawandebet
@KeAbawandebet
395 viewsedited  03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ