Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የሰርጥ አድራሻ: @keabawandebet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው እሮብ እና ቅዳሜ ብቻ ይጠብቁን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-08-07 23:15:22 ጻዲቁ ዮሴፍ እጅግ ከባድ የሆነ ውጪያዊ ውጊያ ከጲጥፋራ ሚስት ቢገጥመውም አልወደቀም።

እርሱ ኃጢአትን በልቡ ውስጥ ስላልተቀበለው ፈተናውንም አልተቀበለውም። ስለሆነም ጥቃቱን ሊቋቋም ችሏል።

እያስተዋልን

ዲያብሎስ አሳቦችን ያቀርብልሃል እንጅ ተቀብለህ ተግባራዊ እንድታደርጋቸው አያስገድድህም።

እናም ለስህተት ሌላ ሰው ተጠያቂ አታድርግ መጀመሪያ እራስን ይቅርታ ጠይቀህ ከዛም በነገሮች የተረበሹትን ይቅርታ መጠየቅ በመቀጠል አምላክህን ይቅርታ መጠየቅ

መልካም የፍልሰታ ፆም

ስልክ +251927707000

#ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን

#ቴሌግራም

https://t.me/BiniGirmachew
https://t.me/BiniGirmachew
https://t.me/BiniGirmachew

SUPPORT ON YOUTUBE

https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w

tiktok

tiktok.com/@bini_girmachew
tiktok.com/@bini_girmachew

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
2.7K views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 10:59:58 በቃ እንዲሕ ያለውን የነጠረ ቃል ሳስታውስ ነው ፍልሰታ ማለት ለእኔ ምን ማለት እንደሆነች የምረዳው….. ከዛፎቹ …..ከመጠለያው …..ከአስቀዳሹ…… ከፅናው….. ከዲያቆኑ….. ከካሕኑ ከልብሰ ተክሕኖው ….. ከሚሯሯጡት ሕፃናት ….. ከሁላ ሁሉ በላይ የድንግል ማርያም ምስጋና የፍልሰታ ጾም ውበት ነው፡፡


የቁርባን ስዓት (ድርገት) ሲደርስ ከሰንበት ትምሕርተ ቤት አዳራሽ በሰልፍ ስንወጣ…. በተወሰነ ርቀት ሰልፋችንን ጠብቀን እንድንጓዝ የሚደርጉን የመዘምራን ዩኒፎርም የለበሱት ትዝ ይሉኛል። ቆርበን ስወጣ በወንዶች እና በሴቶች በር የተቆራረሰ ዳቦ ለምለም እንጀራ ይዘው ለሁሉም ቆራቢ የሚሰጡት እናቶች ዛሬ ድረስ ትዝታዬ ናቸው ። አንዳንድ ጊዜ በልጅነት ዘመን ሳንቆርብ እንደቆረብን መስለን አፋችንን በነጠላ ሸፍነን ዳቦ እንቀበል ነበር። በሴቶች በር ተቀብለን ከሆነ በወንዶች በር ለመቀበል የምንሰጠው ምክንያት ገራሚ ነበረ

"ጫማዬ በዛኛው በር ነው"

"እናቴ በዛ እየጠበቀችኝ ነው"

ከቆረብን በኋላ ካሕኑ የሚያነቡት ንባብ

ይህንን የማርያምን የምስጋና ቃል እንደሰማችሁ የሕፃናትን ይልቁንም አጥንትን የሚያለመልመውን የመላእክት ምስጋና እንደዚሁ ያሰማችሁ። የእሳት ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት የካሕናት አለቆች ወደ አሉበት ያግባችሁ ። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ይሄንን መርሳት መቼም አይሆንለትም። መቼም ቢሆን አይረሳም ። በልጅነት ልቦናችን ላይ የታተመ የተቀረፀ የትላንትናችን የትዝታ ማህደር ነው።

አድንኑ አርዕስቲክሙ ሲባል የልጅነት ልቦናችን እና እግራችን ወደ ቤት ለመሮጥ ይዘጋጃል። ሥርዓተ ቅዳሴው ማለቁን እንረዳለን። ዳዊት ድፍዳ ፀበል ይዞ ከቤተ መቅደስ ከወጣ ።

በቃ ቅዳሴው አልቋል ማለት ነው ጃንጥላዎች ከታጠፉ ምንጣፎች ከተሰበሰቡ ነጠላዎች በሰስ ፌስታል ውስጥ ከተከተቱ. በቃ ቅዳሴው አልቋል ማለት ነው። ዛሬም ቢሆን ከዓመታት በኋላ ዳዊት ድፍዳ ለአንዳንድ ምዕመናን ጸበል መስጠቱን አላቆመም ። አድንኑ ሲባል ሁሉም ነጠላውን ያጥፋል።

"በስላም ግቡ ወደ ቤታችሁ ግቡ" ከተባለ በኋላ ድምፅ ማጉያውን ተቀብለው የሚዘምሩትመ ዘማሪዎች ትላንትም ነበሩ….. ዛሬም አሉ ።

ትላንትና ከቅዳሴው መጠናቀቅ በኋላ በአባ ክፍለዮሐንስ (የከተማው እንጦንስ) ቤት ገብተን እግር ስመን የፍልሰታን በረከት እንቀበል ነበር። ባቄላና ንፍሮ አንዳንዴም አነባበሮ እንቀበላለን ። ንቦቹ እንዳይነድፉን ፊታችንነ በነጠላ እንሸፍናለን። ጋሽ አድማሱም ጋር እንሄድ ነበረ። ትዝታችን እዚህ ጋር ነው የተሰበረው። አባ ክፍሌ እና ጋሽ አድማሱ በአካለ ሥጋ ከእኛ ጋር የሉም።

በፍልሰታ ፆም የማይገኙት የየት ሰፈር ልጆች ናቸው?

የሁሉም ሰፈር ልጆች ይገኛሉ፡፡

ስለምንቆርብ ነው ገላችንን በደንብ የምንታጠበው ። ስለቆረብን ነው ኳስ እንዳንጫወት የተከለከልነው። ስለቆረብን ነው ከቤት እንዳንወጣ የተደረግነው ። ወላጆቻችን ከወትሮ በተለየ እቤት ውስጥ የተንከባከቡን ስለቆረብን ነው ።

በክረምት የሚሰጠው የሰንበት ትምህርት ቤቱ ኮርስ ነው ። ከፍልስታ ፆም መግባት ጋር ልዩ ድባብ ነበራቸው። ዛሬም አላቸው…. የምድብ አስልጣኞች የሚያፅፉን ፅሑፍ ሁሉም በፍልሰታ ወቅት ልጅነቴ ብዬ በምጠራው ሀዲድ ላይ የተሳፈሩ የሃይማኖት ቤት ትዝታ ናቸው፡፡

ማታ ሲመሽ

ሰዓታት ዘሌሊት ከመቆሙ በፊት ወደ መቅደስ ግቡ የሚለው ደወል እስኪደወል ድረስ የአዳራሹ ወንበር ገጥመን እንተኛ ነበር። ዲያቆናት ውዳሴ ማርያም ዜማ ያደርሳሉ ። ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ደወል ሲደወል የቤተመቅደሱ መብራት ሲበራ ሁሉም ከተኛበት ተነስቶ ተናጽቶ ወደ ቤተመቅደስ ይገባል። ፀሎቱን ሳያደርስ ማንም ከማንም ጋር አያወራም….. የሰዓታቱ ቦታ አራት ማዕዘን ቅርፅ አለው…… የአበባ ምንጣፍ ይነጠፍበታል…… አሳዳሪው ካሕን ካባቸውን ለብሰው በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን ብለው ይጀምራሉ፡፡ በግራና በቀኝ ካሕናት ፣ መነኮሳት ፣ መሪጌታዎች ፣ ቀሳውስቶች ፣ ቀኝ ጌታዎች ፣ ግራ ጌታዎች ፣ ዲያቆናት ፣ መፀሐፈ ሰዓታት ይዘው የሚከታተሉት ብቻ ብዙውን ነገር ያየሁት በልጅነት አዕምሮዬ በዛች ውብ ቤተ መቅደስ ነው፡፡

አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሰዳዴሆሙ ለአጋንንት እምየማንነ ወእምፀጋምነ እምዛቲ መካን ይርሃቁ እምኔነ ለእለ ይፀብዕዎ ለነፍስነ ይባላል…… አባ ልብሰወርቅ ሰዓታት ቋሚውን ቆንጆ ሽቶ ሲቀቡ።

ኃይል ባለው ድምፅ እንባ በሞላው ፀሎት ሁሉም ሰዓታት አድራሾች የእመቤታችን ስዕለ አድህኖ እየተመለከቱ ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኢሳያስ ሲሉ…….. ተረኛው ሲቀበል….. ዲያቆኑ ምስባክ ሲሰብክ….. ካሕኑ ወንጌል ሲያነቡ ያ ሁሉ የልጅነት ልቦናዬ ላይ የታተሙ ፊደሎች ናቸው ….. ዲያቆናቱ ኩሎሙን ሲቀሽሩት…… አባ ኃይለስላሴ ነዓ ነዓ ነዓ ጊዮርጊስ እንዘ ትፄአን በፈረስ ሲባል እንዴት ነበር መቋሚያውን የሚዘምሙት….. ትባርኮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ነዓ ጊዮርጊስ ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ ወነዓ ፍቁር ዘልዳ ንጉስ ዘሐረፀከ ዱዲያኖስ ወወገረከ ደብረ ይድራስ። አባ ኃይለስላሴ በአካለ ሥጋ ከእኛ ጋር አይደሉም ። በረከታቸው ይደርብን።

ደሞ ሊነጋጋ ሲል…… አባ ልብሰወርቅ ተዓምሪሃ ለእግዕዝትነ ማርያም ሲሉ….. ተዓምረ ቂርቆስ ……ተዓምረ ኢየሱስ ተከታትለው ሲነበቡ….. ዕሴብሕ ፀጋኪ ሲባል…….እንዴት ደስ ይላል….. የደብሩ የመጽሐፍ መምሕር የኔታ ብርሃኑ ውዳሴ ማርያም አንድምታውን ሲተረጉሙት፡፡

"አዕምሮውን ልቦናውን ሳይብን አሳድሪብን " ሲሉ፡፡

እንዴት መሰላችሁ የሚናፍቀው። የፍልሰታ ፆም ብዙ ነገር ነው።

ነሐሴ 16 ታቦተ ሕጉ ሕዝቡን እየባረከ ዑደት ሲያደርግ። የሰንበት ትምሕርት ቤት ተማሪዎች "ሞትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ሲሉ" እነዚህና መሰል ትዝታዎች ዛሬን ብቻ ነገም አብሮን ይኖራል።

የፍልሰታን ፆም እንኳን ደኽና መጣሽ እንበላት፡፡

ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን!
17.1K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 10:59:58 ፍልሰታ
×

|

መቼም ቢሆን የልጅነት ዘመኔን ከሚያስታውሱኝ የቤተክርስቲያን ወቅቶች መካከል የፍልሰታ የፆም ወቅት አንዱ ነው። በዚሕ የፆም ወቅት ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀዳደደ ነጠላ አጣፍቼ ወደ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ለማስቀደስ የሄድኩት።

ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን ከራሴ ቁመት ጋር አነፃጽሬ የተገረምኩት። ትልቀቱ ግዝፈቱ የገረመኝ። የቤተክርስቲያኑ ግንብ ላይ ያሉት ጠጠሮች ። የቆሙት አስራ ሁለቱ የቤተክርስቲያን ምሰሶዎች….. ብቻ ሁሉንም ማወቅ የቻልኩት በዛን የልጅነቴ ጊዜዬ ነው ፡፡

ነጠላዬን አላስተካከልኩም

"ወዴት ነው የምትሄደው? "

" ስንት ሰዓት ነው የምትመጣው? " አልተባልኩም። ብቻ ነጠላዬን አጣፍቼ ወደ ቤተክርስቲያን ራሴን ችዬ ከሰፈሬ ልጆች ጋር የሄድኩት በፍልሰታ የፆም ወቅት ነው፡፡

ቤተክርስቲያኑ እንደኔ ያሉትን ብዙ ሕፃናት የማስተናገድ አቅም ነበረው። ብዙ ነን። በጣም ብዙ።

አንዱ ዣንጥላ ይዞ ይሯሯጣል ….

አንዳንዱ ሹሌ ይጫወታል…..

ሌላው ምንጣፍ ይጎትታል….. በዘረጋነው ምንጣፍ ላይ ተርታውን ዓውደ ምሕረቱ ላይ እንተኛ ነበር፡፡ (ካደኩ በኋላ ነው እንዲያ የምንተኛው የአተኛኘት ዓይነት አስመራ ድርድር መባሉን ያወኩት)። የደብሩ ዲያቆናት ከመቅደሱ ወደ ቤተልሔም ለአገልግሎት ሲፋጠኑ ….ውር ውር ሲሉ የልጅነት አዕምሮዬ ላይ ተከትቦ ቀርቷል። መቅደስ ውስጥ የጉልላቱን ርቀት እያየሁ ይደንቀኝ ነበር። መንግስተ ሰማያት ማለት ያ ይመስለኝ ነበር ። ያኔ ነው የመቅደሱ ፍቅር የጣለኝ፡፡

ካሕናቱ ፍሕሙን በጧፍ ሲያቀጣጥሉ ። የዕጣኑ መዓዛ በንፋስ እተገፋ ያለንበት ድረስ መጥቶ ሲያውደን። የቤተክርስቲያኑ ጠባቂ ንቦች አንዳንድ ጊዜ ለመደበቅ የማይመች ቦታ ሲነድፉን በእብጠቱ ጓደኞቻችን እየሳቁ ያስኮርፉን ነበረ ። ከንፈራችን አፍንጫችን ቅንድባችን የተነደፈ ዕለት የሚኖረው እብጠት እኛኑ ራሱ ያስገርመን ነበረ። ደሞ በ
ሌላ ጊዜ እንዳይነድፉን በነጠላችን ስንሸፋፈን ትዝ ይለኛል፡፡

በቃ ደስ የሚል ትዝታ አለ አይደለ ….ፍልሰታ ለእኔ እንደዛ

የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ሁላችንንም ሰብስበው አዳራሽ ውስጥ ቁርባን እስኪጀመር ድረስ አስገብተው የሚነግሩን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች። መሳጭ የሆኑት የእነ አብርሃም ታሪክ አጣፍጠው የሚነግሩን የተረት አባቶች ። ያኔ አዳራሹ መቀመጫ ወንበር አልነበረውምና ምንጣፍ ተነጥፎልን ነበር የምንቀመጠው። ብዙዎቻችን ለመቀመጥ እንጋፋለን ።

ሥርዓተ ቅዳሴ ሲጀመር ይሰማናል።

"አሐዱ አብ ቅዱስ ..." ሲባል ሁላችንም እንድንነሳ ይደረጋል። አቤት የነበረ ፍቅር። ቶሎ ለመነሳት ያለን እሽቅድድም። ለመነሳት አንዱን ስንደገፍ…. ሌላኛው እኛን ሲደገፈን…. የነበረው መልካምነት ደስ ይል ነበር። የሰንበት ትምህርት ቤቱ መድረክ ለልጅነታችን አዕምሮ ይገዝፍብን ነበር። እየተቀባበሉ የሚያቀርቡልን መነባንብ ….. የምድብ ማቴዎስ የሕጻናት ክፍል ተማሪዎች እየተቀባበሉ የሚዘምሩልን መዝሙር…. አዝማቹ ሲጠፋቸው ለማረም ስንሞክር የምነፈጥረው ረብሻና ጩኽት። አቤት እንዴት ደስ ይል ነበር። አዳራሽ በተራ ነበር የምንገባው…… ዛሬ ወንዶች ከገቡ ነገ ደግሞ ሴቶች ይገባሉ፡፡ በዛ ድራማና መነባንብ ተስበን ብዙዎቻችንን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ሆነን ቀርተናል።

ጥሬ የሚለቅሙት ነጫጭ እርግቦች አውደ ምህረቱ ላይ የተበተነላቸውን የድፎ ዳቦ ፍርፋሪ….. የእንጀራ ቁራሽ…. የጥሬ ብትን ሲመገቡ ቆመን እናያቸው ነበር።

ስንት ነበሩ ርግቦቹ?

አንድ ጨቅላ ሕጻን ልጅ እየሮጠ ወደ ተሰበሰቡት እርግቦች መሰስ ብሎ ሲሄድ እየተበታተኑ ወደ የአቅጣጫው ሲሄዱ። በየዛፎቹ ላይ ሲንጠላጠሉ። እናቶች ሕፃኑን ልጅ ይዘውት ሲሄዱ። የተበታተኑት እርግቦች መልሰው ሲሰበሰቡ። ከሕ
ንፃ ቤተክርስቲያኑ መስኮት ላይ ….. ከደውሉ ላይ…… ከዛፎች ላይ ….ድጋሚ ተሰብስበው ጥሬ ሲለቅሙ ያለው ድባብ መቼም የማይረሳ ትዝታ ነው፡፡

ሕፃንነት ነውና ጊቢው ዙርያ እንሮጣለን…. አንዱን ጓደኛችንን እናባራለን፡፡

በሌላ ቀን ደሞ

ካህናቶች ወደ ቤተልሔም ወርደው መሶበ ወርቅ ዲያቆኑ ተሸክሞ ሲመለስ የዲያቆኑን ቃጭል ተከትሎ የሚደወለው ትልቁ ደወል ። ሕዝበ ክርስቲያኑ መሬት ወድቆ ሲሳለም።

"እምነ በሃ ቅድስት ቤተክርስቲያን አረፋቲሃ "ሲሉ። ሁለቱ ድምፅ ማጉዎች ሲያስገመግሙ ሲያስተጋቡ ።

"ሃሌ ሉያ እመቦ ብዕሲ ምዕመናን ዘቦአ ቤተክርስቲያን " ሲባል እንረጋጋለን። ወላጆች ልጆቻቸው እንዳይቀሰፉ በማለት በእጆቻቸው ይጣራሉ፡፡

በፍልሰታ ፆም የማላየው የዣንጥላ አይነት የለም። ጥቁር ቢጫ አረንጓዴ ቀይ...

የማልመለከተው የሰው ዓይነት የለም አጭር ወፍራም ሽማግል ወጣት ቀጫጫውን ...ወዘተ

ያላየሁት መቀመጫ ዱካ በርጩማ ያላየሁት ምንጣፍ የለም። ከቤተክርሰቲያኑ ዋናው በር በስተግራ የመባዕ መሸጫውን….. ክርስትና ቤቱን ….. የሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽን ይዞ….. የደብሩ አስተዳደር ያለበትን…. የአባታችን የአባ ክፍለ ዮሐንስ ዘወልደማርም መኖሪያ ቤት በሙሉ መጠለያ ስምንትን ጨምሮ እስከ ቤተልሔሙ ድረስ[ከቤተልሄም በመለስ] ሴቶች ይቆማሉ።

ጥንታዊያን የተሰኙ ዲያቆናት መሪጌታዎች መነኮሳት ቀሳውስት የቤተልሔሙን አጸድ ይመርጣሉ። ወጣቶችም አይጠፉም ። መጠለያዎቹ ግጥም ብለው ይሞላሉ ። ደወሉም ላይ የሚወጣ አይጠፋም። በቤት መኪና …. በላዳ ታክሲ ጭምር መጥተው የሚያስቀድሱም አሉ። ብቻ ሁሉም እግሩ በመራውና ይመቸኛል ባለው ቦታ ለማስቀደስ ይቆማል ።

"ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ " ሲባል ሁሉም ቀጥ ብሎ ይቆማል ። የቤተክርስቲያኑ በሮች በጥበቃዎቹ ይዘጋል። እጆች ይዘረጋሉ።

"አሐዱ" ሲባል ጥበቃው እየተራመደ ከሆነ ይቆማል። አንዳንዱ ያለቅሳል ሌላው በፍርሃትና በተመስጦ በጌታ ፊት ሲቆም። የሚነደው ፍሕም ላይ የገባው ዕጣን ያለከልካይ ብቻውን ሲንቦለቦል። የካህናቱ ዜማ እንደ ንፁሕ ምንጭ ውሃ ኩልል ሲፈስ። የእጣኑ መዓዛ ጅረት ሆኖ ቤተክርስቲያኑን ሲዞር ለተመለከተው የሰማይ ሥርዓት በምድር እንደተሰራ የሚያመላክት አንዳች ኃይል አለው ፡፡

ሕፃናት ጃንጥላዎቻቸውን ዘርግተው የቤተክርስቲያኑን ግንብ ተደግፈው ይቀመጣሉ፡፡ በጊቢው ውስጥ የተገኙት ምዕመናን "ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት" የሚለውን የዲያቆኑ ትዕዛዝ ተከትለው "ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ" እያሉ በሕብረት ይሰግዳሉ።

ሁለት አንድ አይነት የሆኑ የካሕናት ዜማዎች ከቤተመቅደሱ አናት ላይ ይፈሳሉ። በልጅነቴ የሰማሁት ቅዳሴ ማርያም ዛሬምድረስ ይታወሰኛል። የእመብርሃን…. የወላዲተ አምላክ ቅዳሴ እኮ ነው ።

አኮቴተ ቊርባን ዘእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ ብህንሳ ። ሁላችንም ይህን የቅዳሴ አንቀጽ የሰማነው በልጅነታችን አእምሮ ነው። "

"...ጎሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ወአነ አየድሕ ቅዳሴሃ ለማርያም አኮ በአብዝኆ አላ በአውሕዶ" የቀዳስያኑ ድምጽ ባለ ግርማ ሞገስ ነበር (አሁንም ነው ድረስ ነው) ። ፍሬ ቅዳሴውን እየተቀባበሉት ሲደግሙት። አንድ ቀን በግዕዝ። በሌላኛው ቀን ደሞ በአማርኛ ንባቡን ሲዘልቁት። ዛሬም በአዕምሮዬ ትዝታ ሆኖ ቀርቷል፡፡

"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራዊን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንፅሕና በቅድስና በቤተመቅደስ ኖርሸ እንጂ….."

"ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥ የጠጣሽ አይደለሽም ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥ ነው እንጂ ….. "
13.6K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:21:14


❝እነሆም የስራ ዜና!❞
* ***

#ለሸፍቴ_ቅዱስ_ሩፋኤል_ህንጻ_ማሰሪያ_201000_ብር_ገቢሆነ!

በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን በኦይዳ ወረዳ በሸፍቴ ከተማ ለምትገኘው የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰሪያ ከዚህ ቀደም ህንጻው ተጀምሮ ከ10 ዓመታት በላይ ቆሞ ቀርቶ የነበረውን ለማሰራት እንቅስቃሴ ጀምሬ የተባረከው ወንድሜ ከአሜሪካን ሃገር ከኪሱ እና ደጋጎችን አስተባብሮ ከዚህ ቀደም 208,000 ብር ሌላም ጊዜ ከ100,000 ብር በላይ በድምሩ ከ310,000 ብር በላይ ልኮ ቆሞ ቀርቶ የነበረው የሩፋኤል ህንጻ መጀመሩ እና ትልቅ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አብስሬ ነበር። እነሆም ይሄው ወንድሜ ከሃገረ አሜሪካ 201,000 (ሁለት መቶ አንድ ሺህ) ብር ልኮልናል። እስከ አሁን ድረስ ለሸፍቴ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰሪያ የሚሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ስሙን እንድገልጽ በማይፈልገው ወንድሜ ከሃገረ አሜሪካ ሰጪነት ከ501,000 ብር በላይ ገንዘብ ገቢ ሆኗል።

እናንት የሸፍቴ ከተማ ነዋሪዎች፥ ይህ መቅደስ ሲያልቅ ለኦርቶዶክስ አማኙ ብቻ ሳይሆን ለሁላችሁ የከተማችሁ ድምቀት ነውና ህንጻውን ተባብራችሁ ከዳር እንድታደርሱት አደራ እላለሁ። ገንዘቡን ሳትሰስት የምትቸረን ወንድሜ ገንዘቡ በትክክል ለታለመለት አላማ እየዋለ ነውና ደስ ይበልህ። የአምላክን ቤት ለመስራት ገንዘብህን ለመስጠት እጅህ አልሰሰተምና ስስት የሌለው የአምላክ በረከት ቸርነት በቤትህ ይሁን እላለሁ። አምላክ ለፍጻሜው በሰላም ያድርሰን። እንድንጨርሰውም አቅሙን ይስጠን!

https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
3.7K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:18:00
እኔስ እዘምራለው ለሥላሴ እኔስ እዘምራለው ለሥላሴ
ፈጥሮኛልና በስጋ በነፍሴ እኔስ እዘምራለው ለሥላሴ


እንኳን ለቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረበአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የፃድቁ አባታችንን የአብርሀምን ቤት የጎበኙ ቅድስት ሥላሴ የእኛን ቤት ይጎብኙልን
1.7K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 09:19:03
3.8K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:55:10
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
አጠራቅመን አንድ የገጠር ቤተክርስቲያን እናድሳለን
2.8K views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:43:58
እግዚአብሔር ይስጥልን
3.2K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:05:56 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ

ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር

አለ"

ራእ. 22:11-12
3.6K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 08:42:10
5.0K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ