Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የሰርጥ አድራሻ: @keabawandebet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው እሮብ እና ቅዳሜ ብቻ ይጠብቁን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-01-07 08:29:31
499 views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 19:38:27
489 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 19:38:17 የወላይታ ሀገረስብከት በፋንጎ ሌሜ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያ ከጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶች ጥቃት እንዲጠብቃቸው የህግ ከለላ መንግስት እንዲሰጣቸው ተማጸነ።
***

ስለፋንጎ ሌሜ ቀበሌ #ኦርቶዶክሳውያን እንጸልይላቸው!

በወላይታ ሀገረስብከት ሁምቦ ወረዳ ፋንጎ ሌሜ ቀበሌ በምትገኘው የአቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስትያን እና በቀበሌው በሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናንን ላይ ከታህሳስ 25 ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት እና ዛቻ በተደራጁ ጽንፈኛ የፕሮቴስታንት ተከታዮች እየደረሰ ይገኛል።

እስከአሁን የሞተ ምዕመን ባይገኝም ከ10 በላይ ምዕመናንን ላይ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ የአካል ጉዳት ደርሶባችዋል።

በአከባቢው የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንን በቁጥር ጥቂት ስለሆኑ ጥቃቱን ፈርተው ከቤታቸው ተሸሽገው በሰቀቀን ላይ ይገኛሉ።

የወላይት ሀገረስብከትም በአከባቢው ባሉ የምዕመናንን ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ በመሆኑ የተነሳ መንግስት የህግ ከለላ በቀን እና በማታ ለምዕመናንን እንዲያደርግ ተማጽኗል።
482 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 20:54:37 ወር በገባ በ27  የሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ወርኃዊ በዓሉ ይከበራል ።

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ

በ8ኛው ሺህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለሚመጣው ደገኛ ንጉሥ

ስለ ሀገራችን የኢትዮጵያ ትንሣኤና ደጉ ዘመን

በስምንተኛው ሺህ ዘመን በዓለም ስለሚሆነው

ስለመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ሌሎችንም .....
በመናገር  የሚታወቀው ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር  ነው።

በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ  ‹‹ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ፤

በ8ኛው ሺህ ዘመን በሀገራችን በኢትዮጵያና

በግብፅ እንዲሁም

በቁስጥንጥንያና

በሮም ወደፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር

በግልጽ የተናገረው "ትንቢቱና ሙሉው ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር"

"ከታላቁና ከሙሉው

1ኛ የ12 ወር ፤

2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤

3ኛ ሰማዕቱ ሚናስ ያደረገው ተአምር ፤

4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ ከተካተቱበት "
ከገድለ ቅዱስ ሚናስ"ጋር  ታትሞ›› ይገኛል ፡፡

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር  ሚያዝያ 27 ቀን በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ ከጥቂት ዘመናት በኋላ እግዚአብሔር

በኢትዮጵያ ሀገር ክርስቶስን የሚወድ ቅዱስ ሰው ያነግሣል፡፡አረማውያንም በእርሱ እጅ ይደመሰሳሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ግብፅ ሀገር ሄዶ አረማውያንና መንግሥታቸውን ሁሉ ያጠፋል፡፡ እግዚአብሔር በቍስጥንጥንያ እርሱን የሚወድ ስሙ

" ትውልደ አንበሳ"የተባለ ሰው ያነግሳል፡፡

ከኢትዮጵያ ንጉሥ ጋር ይገናኝ ዘንድ ይመጣል፡፡ በግብፅ መሀል ቦታ ላይ ይገናኛሉ፡፡ ከእርሱ ጋርም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳትና የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ይገናኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ንጉሥ ሠራዊቱን በደቡብ በኩል ትቶ የቍስጥንጥንያም ንጉሥ ሠራዊቱን በሰሜን በኩል ትቶ ሁለቱ ነገሥታትና ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ተገናኝተው እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ፤

ሊቃነ ጳጳሳቶቹ በመንበራቸው ላይ ተቀምጠው ነገሥታቱን ‹በየመንበራችሁ ላይ ተቀመጡ› ይሏቸዋል፡፡

የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ‹የእኛ ሃይማኖት ትበልጣለች› ይላል፡፡

የእስክንድሪያውም ሊቀ ጳጳሳት ‹እግዚአብሔር የሰጠኝን ቃል እኔ እነግራችኋለሁ› ይላል፡፡

ሁለቱ ነገሥታትም ‹አባታችን በል ንገረን› ይሉታል፡፡ ‹የአባ ሲኖዳ ወደምትሆን ወደዚህች ታላቅ ቤተክርስቲያን ገብተን በአንዲት ታቦት ላይ እኔ እቀድሳለሁ፣

ይህ ባልደረባዬ ሊቀ ጳጳሳት በአንዲቷ ታቦት ላይ ይቀድስ፤ ሁሉም ሕዝብ ሠራዊቶቻችሁም መጥተው ይመልከቱ› ይላል፡፡ ‹መንፈስ ቅዱስ እያያችሁት ከሁለታችን በአንዱ ቁርባን ላይ ከወረደ በዚያ ሃይማኖት ሁላችን እንሂድ፣ ሃይማኖቷም ትታወቃለች ቀንታለችና› ይላቸዋል፡፡

ሁለቱ ነገሥታት ‹እሺ በዚህ ቃል ተስማምተናል፣ የእግዚአብሔር ምክር ናትና› ይሉታል፡፡ ያን ጊዜ ሁለቱ ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ካህናቶቻቸውም፣ ሕዝቡም ወደዚህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ፡፡

ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳትም በሁለቱ ታቦታት ላይ ይቀድሳሉ፡፡ በዚያ ያሉ ሁሉ እያዩ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል ከብርሃን ጋር የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳሳት በቀደሰው ቍርባን ላይ ይወርዳል፡፡

ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ንጉሥ ይደሰታል፣ የእርሱም ሊቀ ጳጳሳት ነውና፡፡ በእግዚአብሔር ፊትም የእርሱ የሃይማኖት ሕግ የተወደደ ይሆናል፡፡ የሮም ንጉሥ ግን ........(የበለጠ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመውን ገድለ ፊቅጦርን ያንብቡት)

የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፊቅጦር ረድኤት በረከቱ ይዋልብን ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

ምንጭ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመው
1ኛ የ12 ወር ፤

2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤

3ኛ ሰማዕቱ ያደረገው ተአምር ፤

4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ የተካተቱበት "

ሙሉውና ታላቁ ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር "
474 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 20:54:37
ገድለ_ቅዱስ_ሚናስ_ወገድለ_ፊቅጦር
በመምህር ሳሙኤል ደርሴ
ዋና አከፋፋይ
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር

ለኅብረቱ አባላት 250ብር ሳያልቅባችሁ ቀድማችሁ ለፍስሃ
@tsionfish እዘዙት።

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ማርያም_ዋናውበር_ሽዋዳቦ_ፊትለፊት_ካሉት_መነጽር_ቤቶችውስጥ_ለበለጠ_መረጃ_0912044752_0966214181_ይደውሉ
378 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 17:52:13
በወላይታ ሀገረ ስብከት በሁምቦ ወረዳ ቤተ ክህነት ፋንጎ ሎሜ ቀበሌ በደምባ ሎሜ መንደር በሚገኘው በአቡነ ዜና ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያኑ ምእመናን ላይ ታኅሣሥ 25/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አከባቢ በተደራጁና በታጠቁ ጥቃት አድራሾች አሰቃቂ ጥቃት ደረሰ።

በጥቃቱ ሁለት ምእመናን ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ10 በላይ ምእመናን ላይ መጠነኛ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ጥቃት ያደረሱት አካላት ከወራት በፊት ሲዘጋጁ እንደነበሩ እና ተከታታይ የግድያ ሙከራ በማድረግ "የቤተ ክርስቲያን ደጆቿን እናዘጋለን" በማለት ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርሱ የነበሩ መሆናቸውን ምእመናን ገልጸዋል።


ብዙ በደሎች እየደረሰ እደሆነ አውቃለሁ ቢሆንም ዝም የምለው አውርተን መረጃ ሰተን ከወሬ ያለፈ ነገር ሲደረግ አላየሁም ለዛም ነው ዝም ማለትን የመረጥኩት

እንጂህ የሚደረጉት ነገሮች ያስጠላሉ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት ከማድረግ ውጪህ መፈቴ የለም

https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
299 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 16:53:54 በተለይ ጥዋት እና ማታ መንፈስ የሚድስ ስብከት እዚህ ቻናል መስማት ወይም ማንበብ ይችላሉ

https://t.me/Orthodox_sibket/31
https://t.me/Orthodox_sibket/31
https://t.me/Orthodox_sibket/31
400 viewsedited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 16:47:02
ሙሉ በሙሉ ተዘርፋ ለነበረው ቤተክርስትያን ያስተባበርነውን ከ200ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወደ አጥቢያዋ አድርሰናል።
***

እግዚአብሔር ይመስገን !

በደቡብ ኢትዮጽያ ጉማይዴ ለዘመናት በቆዬው የእርስ በእርስ ግጭት የቤቾ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን ሙሉ በሙሉ መዘረፏ ይታወቃል።

የተዘረፈው ንብረት ይተካ ዘንድ ከማህበራዊ ሚዲያ ወዳጆቻችን ያስተባበርነውን ቁሳቁሶችን ትላንት ወደ አጥቢያዋ አድርሰናል።

አሁን ላይ በተሻለ መልኩ የሠላም አየር በስፍራው እየነፈሰ ስለሆነ፣ከህዝቡ ጋር ተሶዶ የነበረችውን የቅድስት ኪዳነምህረት ታቦተ ህግ ወደ ስፍራው ከህዝቡ ጋር ስለተመለሰች ቅድስት ቤተክርስትያን ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሳለች።

ለለገሳችሁልን እግዚአብሔር ይስጥልን !

ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን

https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
https://t.me/KeAbawandebet
413 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 16:29:22
#ለሚዲያ
435 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 08:34:53 የጥምቀት በዓል የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት (Emergency Medical Service at Epiphany)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የድንገተኛ ሕክምና ክፍል በአደባባይ በዓላት ላይ የምናደርገውን የሕክምና አገልግሎት በመቀጠል ዘንድሮም የጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጀት ላይ ይገኛል። ይህ አገልግሎት የሚሰጠው ከከተራ እለት ጀምሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱት 3 ቦታዎች እና ሰዓታት ሲሆን የሚመቻችሁን ቦታ እና ሰዓት ቅጹን በመሙላት እስከ ጥር 3 (January 11) ድረስ ባለው ጊዜ እንድታሳውቁን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

1. ጃን ሜዳ፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00
2. አበበ ቢቂላ ስታዲየም፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00
3. ጎንደር ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 - 6:00

ለዚህ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
Specialties needed for our Emergency Medical service at Celebration of Epiphany:-

Emergency Physician
General Practitioners
Internal Medicine
Pediatrics
Nursing
Pharmacists
Orthopedics
Health Officers
Public Health professionals

ጤና ባለሙያዎች ቅጹን ለመሙላት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfXvAjlOO0thRvvX33vt5TO1EVYWUwjT0pMcSRkIKkltJETZA/viewform?usp=pp_url

አገልግሎታችንን ለመደገፍ የምትሹ በሚከተሉት አማራጮች መለገስ ትችላላችሁ፦

አሐዱ ባንክ፡ 0004857810101
ንግድ ባንክ፡ 1000355318021
ዳሽን ባንክ፡ 0472399237011
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ: 3359501002471
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 7000036276989
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 013081005174100

በግብዐት ማገዝ የምትሹ በስልክ ቁጥር 0913726877 ይደውሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!

EOTMA for all by all!

https://t.me/KeAbawandebet
110 viewsedited  05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ