የጥምቀት በዓል የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት (Emergency Medical Service at Epiphany) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የድንገተኛ ሕክምና ክፍል በአደባባይ በዓላት ላይ የምናደርገውን የሕክምና አገልግሎት በመቀጠል ዘንድሮም የጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጀት ላይ ይገኛል። ይህ አገልግሎት የሚሰጠው ከከተራ እለት ጀምሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱት 3 ቦታዎች እና ሰዓታት ሲሆን የሚመቻችሁን ቦታ እና ሰዓት ቅጹን በመሙላት እስከ ጥር 3 (January 11) ድረስ ባለው ጊዜ እንድታሳውቁን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። 1. ጃን ሜዳ፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00 2. አበበ ቢቂላ ስታዲየም፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00 3. ጎንደር ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር፦ ከተራ ከሰዓት በኋላ 9፡00 - ከምሽቱ 2፡00 ፤ የጥምቀት ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 - 6:00 ለዚህ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው፦ Specialties needed for our Emergency Medical service at Celebration of Epiphany:- Emergency Physician General Practitioners Internal Medicine Pediatrics Nursing Pharmacists Orthopedics Health Officers Public Health professionals ጤና ባለሙያዎች ቅጹን ለመሙላት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfXvAjlOO0thRvvX33vt5TO1EVYWUwjT0pMcSRkIKkltJETZA/viewform?usp=pp_url አገልግሎታችንን ለመደገፍ የምትሹ በሚከተሉት አማራጮች መለገስ ትችላላችሁ፦ አሐዱ ባንክ፡ 0004857810101 ንግድ ባንክ፡ 1000355318021 ዳሽን ባንክ፡ 0472399237011 ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ: 3359501002471 ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 7000036276989 አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:: 013081005174100 በግብዐት ማገዝ የምትሹ በስልክ ቁጥር 0913726877 ይደውሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም! EOTMA for all by all! https://t.me/KeAbawandebet 110 viewsedited 05:34