Get Mystery Box with random crypto!

ወር በገባ በ27  የሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ወርኃዊ በዓሉ ይከበራል ። ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በሰማ | ከ

ወር በገባ በ27  የሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ወርኃዊ በዓሉ ይከበራል ።

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ

በ8ኛው ሺህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለሚመጣው ደገኛ ንጉሥ

ስለ ሀገራችን የኢትዮጵያ ትንሣኤና ደጉ ዘመን

በስምንተኛው ሺህ ዘመን በዓለም ስለሚሆነው

ስለመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ሌሎችንም .....
በመናገር  የሚታወቀው ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር  ነው።

በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ  ‹‹ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ፤

በ8ኛው ሺህ ዘመን በሀገራችን በኢትዮጵያና

በግብፅ እንዲሁም

በቁስጥንጥንያና

በሮም ወደፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር

በግልጽ የተናገረው "ትንቢቱና ሙሉው ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር"

"ከታላቁና ከሙሉው

1ኛ የ12 ወር ፤

2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤

3ኛ ሰማዕቱ ሚናስ ያደረገው ተአምር ፤

4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ ከተካተቱበት "
ከገድለ ቅዱስ ሚናስ"ጋር  ታትሞ›› ይገኛል ፡፡

ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር  ሚያዝያ 27 ቀን በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ ከጥቂት ዘመናት በኋላ እግዚአብሔር

በኢትዮጵያ ሀገር ክርስቶስን የሚወድ ቅዱስ ሰው ያነግሣል፡፡አረማውያንም በእርሱ እጅ ይደመሰሳሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ግብፅ ሀገር ሄዶ አረማውያንና መንግሥታቸውን ሁሉ ያጠፋል፡፡ እግዚአብሔር በቍስጥንጥንያ እርሱን የሚወድ ስሙ

" ትውልደ አንበሳ"የተባለ ሰው ያነግሳል፡፡

ከኢትዮጵያ ንጉሥ ጋር ይገናኝ ዘንድ ይመጣል፡፡ በግብፅ መሀል ቦታ ላይ ይገናኛሉ፡፡ ከእርሱ ጋርም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳትና የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ይገናኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ንጉሥ ሠራዊቱን በደቡብ በኩል ትቶ የቍስጥንጥንያም ንጉሥ ሠራዊቱን በሰሜን በኩል ትቶ ሁለቱ ነገሥታትና ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ተገናኝተው እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ፤

ሊቃነ ጳጳሳቶቹ በመንበራቸው ላይ ተቀምጠው ነገሥታቱን ‹በየመንበራችሁ ላይ ተቀመጡ› ይሏቸዋል፡፡

የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ‹የእኛ ሃይማኖት ትበልጣለች› ይላል፡፡

የእስክንድሪያውም ሊቀ ጳጳሳት ‹እግዚአብሔር የሰጠኝን ቃል እኔ እነግራችኋለሁ› ይላል፡፡

ሁለቱ ነገሥታትም ‹አባታችን በል ንገረን› ይሉታል፡፡ ‹የአባ ሲኖዳ ወደምትሆን ወደዚህች ታላቅ ቤተክርስቲያን ገብተን በአንዲት ታቦት ላይ እኔ እቀድሳለሁ፣

ይህ ባልደረባዬ ሊቀ ጳጳሳት በአንዲቷ ታቦት ላይ ይቀድስ፤ ሁሉም ሕዝብ ሠራዊቶቻችሁም መጥተው ይመልከቱ› ይላል፡፡ ‹መንፈስ ቅዱስ እያያችሁት ከሁለታችን በአንዱ ቁርባን ላይ ከወረደ በዚያ ሃይማኖት ሁላችን እንሂድ፣ ሃይማኖቷም ትታወቃለች ቀንታለችና› ይላቸዋል፡፡

ሁለቱ ነገሥታት ‹እሺ በዚህ ቃል ተስማምተናል፣ የእግዚአብሔር ምክር ናትና› ይሉታል፡፡ ያን ጊዜ ሁለቱ ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ካህናቶቻቸውም፣ ሕዝቡም ወደዚህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ፡፡

ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳትም በሁለቱ ታቦታት ላይ ይቀድሳሉ፡፡ በዚያ ያሉ ሁሉ እያዩ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል ከብርሃን ጋር የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳሳት በቀደሰው ቍርባን ላይ ይወርዳል፡፡

ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ንጉሥ ይደሰታል፣ የእርሱም ሊቀ ጳጳሳት ነውና፡፡ በእግዚአብሔር ፊትም የእርሱ የሃይማኖት ሕግ የተወደደ ይሆናል፡፡ የሮም ንጉሥ ግን ........(የበለጠ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመውን ገድለ ፊቅጦርን ያንብቡት)

የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፊቅጦር ረድኤት በረከቱ ይዋልብን ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

ምንጭ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመው
1ኛ የ12 ወር ፤

2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤

3ኛ ሰማዕቱ ያደረገው ተአምር ፤

4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ የተካተቱበት "

ሙሉውና ታላቁ ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር "