Get Mystery Box with random crypto!

የወላይታ ሀገረስብከት በፋንጎ ሌሜ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያ ከጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶች ጥቃት እንዲ | ከ

የወላይታ ሀገረስብከት በፋንጎ ሌሜ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያ ከጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶች ጥቃት እንዲጠብቃቸው የህግ ከለላ መንግስት እንዲሰጣቸው ተማጸነ።
***

ስለፋንጎ ሌሜ ቀበሌ #ኦርቶዶክሳውያን እንጸልይላቸው!

በወላይታ ሀገረስብከት ሁምቦ ወረዳ ፋንጎ ሌሜ ቀበሌ በምትገኘው የአቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስትያን እና በቀበሌው በሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናንን ላይ ከታህሳስ 25 ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት እና ዛቻ በተደራጁ ጽንፈኛ የፕሮቴስታንት ተከታዮች እየደረሰ ይገኛል።

እስከአሁን የሞተ ምዕመን ባይገኝም ከ10 በላይ ምዕመናንን ላይ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ የአካል ጉዳት ደርሶባችዋል።

በአከባቢው የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንን በቁጥር ጥቂት ስለሆኑ ጥቃቱን ፈርተው ከቤታቸው ተሸሽገው በሰቀቀን ላይ ይገኛሉ።

የወላይት ሀገረስብከትም በአከባቢው ባሉ የምዕመናንን ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ በመሆኑ የተነሳ መንግስት የህግ ከለላ በቀን እና በማታ ለምዕመናንን እንዲያደርግ ተማጽኗል።