Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የቴሌግራም ቻናል አርማ keabawandebet — ከ
የሰርጥ አድራሻ: @keabawandebet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው እሮብ እና ቅዳሜ ብቻ ይጠብቁን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-09 06:38:55
በሳምንት 10 ብር ምዕመናን እሄ ቤተክርስቲያን በእናንተ እረዳታ እያጠራቀምን እዚህ ላይ አድርሰናል በዚህ 6 ወር ውስጥ ምን ሥራን የሚለውን አቀርባለሁ

ወደ ትልቁወ ቻይና በመቀላቀል ምዕመናን እንድትተባበር ስል በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21

ለማንኛውም ጥያቄ @Begood16 ላይ መጠየቅ ይቻላል
1.1K views03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 15:43:45
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት


የፊታችን ቅዳሜ ጳጉሜ 5 ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን

አዲሱ ህንፃ ላይ ያዘጋጀነውን የጥበብ ድግስ ታድመው በአበባዬሽ ዝማሬ ችቦውን ይለኩሱ። ይምጡ አዲሱን አመት በጥበብ ይቀበሉ!!


ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
1.4K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 19:55:51 #አዲስ ዓመት


ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
 
#ዘመን መለወጫ

ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ እንዲል፡፡
በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 7፥1/ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡
 
#ዕንቁጣጣሽ

ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም ወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡
 
#ቅዱስ ዮሐንስ

ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡
 
በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡


@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
470 views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 12:00:53 ሰላም ከሀገር ወጣ ብሄ ነበር አሁን መጥቼአለሁ እግዚአብሔር ይመስገን

እንኳን አደረሰን
293 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:42:42 ሰላም ለገጠር ቤተክርስቲያን በሳምንት 10 ብር ምመናን

ከእዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ በመውጣት እዚህ ላይ ይቀላቀሉ

ምክንያቱም 1 የቴሌግራም ቻናል የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል የተሻለ በመሆኑን ሰላመኩበት እሄ የቴሌግራፍ ቻናል ላይ በመቀላቀል የተሻለ ሥራ ከእግዚአብሔር ጋር እንሰራለን

https://t.me/yeemariyaam21
https://t.me/yeemariyaam21

ከ50ሺ በላይ ምመናን አለበት
2.0K viewsedited  08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:11:22
ዘበዓለ ደብረ ታቦር ሥርዓተ ማኅሌት

ምንጭ - የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
2.8K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:30:06 ጌታ ሆይ እንዴት

@BiniGirmachew

መዝሙር ፫



1)አቤቱ፥የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።

2)ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።

3)አንተ ግን አቤቱ፥መጠጊያዬ ነህ፥ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።

4)በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፥ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።

5)እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፣እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።

6)ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።

7)ተነሥ፥አቤቱ አምላኬ ሆይ፥አድነኝ፤አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።

8)ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው



ዊት በዚህ መዝሙሩ ላይ "እንዴት ነህ ይህ ይሆናል?"እያለ አምላኩን ሲወቅስ እናነባለን። #በቅሬታ ድምፀትም "አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ...!" ይላል።

"...ይቀጥልናም ብዙ ሰዎች ነፍሴን አምላክሽ አያድንሽም አልዋት" ሲል እናገኘዋለን። #ይህ የእርዳታ ተማጽኖም ይመስላል። "ተነስ አቤቱ አምላኬ ሆይ፣አድነኝም፣"የሚል ተማፅኖ በውስ ጡ እናገኝበታለን። "...ከከበቡኝ ከአእላፍ ህዝብ አልፈራም፣"በማለቱም እምነት የዚህ መዝሙር ዋነኛ አካል ሆኖ ቀርቧል።


ዳዊት በፀሎቱ መካከልም ስለመንፈሳዊ ልምምዱ ይገልጣል። "በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፣ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።"ይህ የመዝሙር ክፍል በእርግጥም ካስተዋልነው በእግዚአብሔር ላይ ያለን ፅኑዕ እምነትንና መተማመንንም እናገኝበታለን።ዳዊት "ማዳን የእግዚአብሔር ነው፣በረከትህም በህዝብህ ላይ ነው"ማለቱም መተማመኑን ያሳያል። "አድነኝ፣አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፣የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።"በማለትም የአምላኩን ክንድ ከትውስታ ማህደሩ ያስታውሳል።


ምንም እንኳን ዳዊት መዝሙሩን በአቤቱታ፣ወቀሰና ቅሬታ ቢጀምርም፣የሚያሳርገው ግን በውዳሴና በፈንጠዝያ ስሜት ነው። #በዚህም አምላክ ያደረገለትን በጎ ነገራት ያስታውሰናል።

ይህ መዝሙር በተለይ ለማንኛውም የተጨነቀና በመከራ ውስጥ ላሉት ሁሉ የተስማማ ሆኖ እናገኘዋለን። መዝሙሩ መንፈሳዊ ጦርነትና ፈተና ለገጠማቸው፣ጠላቶቻቸውም በዙሪያቸው ከበው ላስጨነቋቸው ሁሉ የተገባ መዝሙር ነው።ይህም ብቻ አይደለም፣መዝሙሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ፣ሞትና ትንሳኤ የሚተነብይልንም ጭምር ነው።

ከዚህ ቀጥሎ መዝሙሩን ከሰብአዊ ፍጥረታት ነፍስና መንፈሳዊነት ጋር በማዛመድ አንጓ አንድምታውን ለመተንተን እንሞክራለን


+++

"ጌታዬ ሆይ፣እንዴት? ምንኛ የሚያስጨንቁኝ በዙ?ስለምንስ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ መጣ?አንተ አምላኬ እያለህ ይህ ምንኛ ሊሆንብኝ ቻለ?ሲል አምላኩን ይወቅሳል።


#ለሰዎች_ይህን_መሰሉን_ጥያቄ_አንስተን #ስለምን_በእኛ_ላይ_መሰል_ቸልተኝነት እንዳሳዩ ብንጠይቃቸው ብዙውን ጊዜ ምላቻቸው ቁጣና ንዴት ነው የሚሆነው፣ነገር ግን በአንፃሩ አምላካችንን "ለምን?" የሚል ጥያቄ በጠየቅነው ቁጥር በተከፈተ ልቡና ነው ጥያቄያችንን የሚያስተናግደው።


ብዙዎች ዳዊትን ከበው በዙሪያው አስጨንቀውታል።ነገር ግን ሲዘብትባቸውና ሲወቅሳቸው አንመለትም።ይልቁኑም የገዛ ፈጣሪውን ይወቅሰዋል እንጂ።


አቤቱ ጌታዬ ሆይ ስለምን ይህን መከራ ተጋፍጥሁ? #አስጨናቂዎቼስ ምንኛ በዙ?

ሁሉ
ቢሆኑ በእጅህ አይደሉምን?

ኃይል
አምላክስ አይደለህምን? #ጥበቃህና ክብካቤህ በእኔ ዘንድ ሳለ ስለምን እንዲስጨንቁኝ ፍቃድህ ሆነ?ይላል ዳዊት።


ይቀጥላል

@KeAbawandebet
@KeAbawandebet
@KeAbawandebet
15.3K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 12:32:30
የኦሴ ቴርዜዛ ቅዱስ ሚካኤል ቤቴ ክርስትያን ኣካውንት ቁጥር 1000215500962 የኢትጵያ ንግድ ባንክ
3.9K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 08:00:31
3.4K views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:58:16 ​​​ SUPPORT ON YOUTUBE

https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
3.0K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ