Get Mystery Box with random crypto!

ጌታ ሆይ እንዴት @BiniGirmachew መዝሙር ፫ 1)አቤቱ፥የሚያስጨንቁኝ | ከ

ጌታ ሆይ እንዴት

@BiniGirmachew

መዝሙር ፫



1)አቤቱ፥የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።

2)ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።

3)አንተ ግን አቤቱ፥መጠጊያዬ ነህ፥ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።

4)በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፥ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።

5)እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፣እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።

6)ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።

7)ተነሥ፥አቤቱ አምላኬ ሆይ፥አድነኝ፤አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።

8)ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው



ዊት በዚህ መዝሙሩ ላይ "እንዴት ነህ ይህ ይሆናል?"እያለ አምላኩን ሲወቅስ እናነባለን። #በቅሬታ ድምፀትም "አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ...!" ይላል።

"...ይቀጥልናም ብዙ ሰዎች ነፍሴን አምላክሽ አያድንሽም አልዋት" ሲል እናገኘዋለን። #ይህ የእርዳታ ተማጽኖም ይመስላል። "ተነስ አቤቱ አምላኬ ሆይ፣አድነኝም፣"የሚል ተማፅኖ በውስ ጡ እናገኝበታለን። "...ከከበቡኝ ከአእላፍ ህዝብ አልፈራም፣"በማለቱም እምነት የዚህ መዝሙር ዋነኛ አካል ሆኖ ቀርቧል።


ዳዊት በፀሎቱ መካከልም ስለመንፈሳዊ ልምምዱ ይገልጣል። "በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፣ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።"ይህ የመዝሙር ክፍል በእርግጥም ካስተዋልነው በእግዚአብሔር ላይ ያለን ፅኑዕ እምነትንና መተማመንንም እናገኝበታለን።ዳዊት "ማዳን የእግዚአብሔር ነው፣በረከትህም በህዝብህ ላይ ነው"ማለቱም መተማመኑን ያሳያል። "አድነኝ፣አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፣የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።"በማለትም የአምላኩን ክንድ ከትውስታ ማህደሩ ያስታውሳል።


ምንም እንኳን ዳዊት መዝሙሩን በአቤቱታ፣ወቀሰና ቅሬታ ቢጀምርም፣የሚያሳርገው ግን በውዳሴና በፈንጠዝያ ስሜት ነው። #በዚህም አምላክ ያደረገለትን በጎ ነገራት ያስታውሰናል።

ይህ መዝሙር በተለይ ለማንኛውም የተጨነቀና በመከራ ውስጥ ላሉት ሁሉ የተስማማ ሆኖ እናገኘዋለን። መዝሙሩ መንፈሳዊ ጦርነትና ፈተና ለገጠማቸው፣ጠላቶቻቸውም በዙሪያቸው ከበው ላስጨነቋቸው ሁሉ የተገባ መዝሙር ነው።ይህም ብቻ አይደለም፣መዝሙሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ፣ሞትና ትንሳኤ የሚተነብይልንም ጭምር ነው።

ከዚህ ቀጥሎ መዝሙሩን ከሰብአዊ ፍጥረታት ነፍስና መንፈሳዊነት ጋር በማዛመድ አንጓ አንድምታውን ለመተንተን እንሞክራለን


+++

"ጌታዬ ሆይ፣እንዴት? ምንኛ የሚያስጨንቁኝ በዙ?ስለምንስ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ መጣ?አንተ አምላኬ እያለህ ይህ ምንኛ ሊሆንብኝ ቻለ?ሲል አምላኩን ይወቅሳል።


#ለሰዎች_ይህን_መሰሉን_ጥያቄ_አንስተን #ስለምን_በእኛ_ላይ_መሰል_ቸልተኝነት እንዳሳዩ ብንጠይቃቸው ብዙውን ጊዜ ምላቻቸው ቁጣና ንዴት ነው የሚሆነው፣ነገር ግን በአንፃሩ አምላካችንን "ለምን?" የሚል ጥያቄ በጠየቅነው ቁጥር በተከፈተ ልቡና ነው ጥያቄያችንን የሚያስተናግደው።


ብዙዎች ዳዊትን ከበው በዙሪያው አስጨንቀውታል።ነገር ግን ሲዘብትባቸውና ሲወቅሳቸው አንመለትም።ይልቁኑም የገዛ ፈጣሪውን ይወቅሰዋል እንጂ።


አቤቱ ጌታዬ ሆይ ስለምን ይህን መከራ ተጋፍጥሁ? #አስጨናቂዎቼስ ምንኛ በዙ?

ሁሉ
ቢሆኑ በእጅህ አይደሉምን?

ኃይል
አምላክስ አይደለህምን? #ጥበቃህና ክብካቤህ በእኔ ዘንድ ሳለ ስለምን እንዲስጨንቁኝ ፍቃድህ ሆነ?ይላል ዳዊት።


ይቀጥላል

@KeAbawandebet
@KeAbawandebet
@KeAbawandebet