Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት ክፍል | ከ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት

ክፍል ሁለት

ነገር ግን ነገሥታት ሰማያዊውን የክብር አምላክ ሊያመልኩ መጡ፤ ወታደሮች የኃይል አዛዥ የሆነውን እርሱን ሊያገለግሉት መጡ፤ ሴቶች ከሰው የተወለደው ኀዘናቸውን ወደ ደስታ እንዲቀይርላቸው ሊያዩት መጡ።

ደናግላን የድንግልን ልጅ ሊያዩ መጡ ። ምክንያቱም የጡትን ምንጭ እንደሚፈስ ወንዝ የሚያደረገውን የጡትና የወተት ፈጣሪ ከድንግል እናቱ የልጆችን ምግብ ተመግቧልና ።

ሕፃናት ከሕፃናት አፍ ምስጋናን ለመቀበል ሕፃን የሆነውን ለማየት መጡ።

ጨቅላዎች በሄሮድስ ክፋት ምክንያት ምስክር የሆነውን ጨቅላ ሊያዩት መጡ ።

ወንዶች ሰው የሆነውንና የባሮችንም ኀዘን ያጠፋውን ለማየት መጡ።

እረኞቹ ለበጎቹ ብሎ ሕይወቱን የሚሰጠውን መልካም እረኛ ለማየት መጡ።

ካህናት በመልከ ጸዴቅ ሥርዓት ሊቀ ካህን የሆነውን ለማየት መጡ።

ባርያዎች ባርነትን በነጻነት ሊያከብር ፣ የባሪያን መልክ[2] የያዘውን ለማየት መጡ።

ዓሣ አጥማጆች ከዓሣ አጥማጆች መሐል የሰው አጥማጅ የሚያደርገውን እርሱን ሊያዩት መጡ።

ቀራጮቹ ከቀራጮች መሐል ወንጌላዊውን የሾመውን ለማየት መጡ።

ዘማውያን ለዘማዊቷ ዕንባ እግሩን የሚሰጠውን ለማየት መጡ።

ግልጽ አድርጌ እንዲህ ብዬ ልናገር ሁሉም ኃጢአተኞች የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔርን በግ ለማየት መጡ።

ሰብዓ ሰገል አብረው ሆነው፣ እረኞች እያመሰገኑ፣ ቀራጮች መልካሙን ዜና እየተናገሩ፣ ዘማውያን ሽቱ ይዘው፣ ሳምራውያን የሕይወትን ምንጭ እየተጠሙ፣ ከነናዊቷ ሴት ጥርጥር በሌለበት እምነት የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔርን በግ ሊያዩ መጡ።

ሁሉም ሰው እየፈነጠዘ ስለሆነ እኔም መፈንጠዝና ማሸብሸብ በዓሉን ማክበርና መደሰት እፈልጋለሁ።

ነገር ግን እኔ የምዘምረው ክራር በመምታት ፣ ጸናጽል በመጸንጸል ፣ ዋሽንት በመንፋት ወይም ችቦ በመለኮስ አይደለም ።

እኔ ግን በዝማሬ መሳሪያዎች ፈንታ የክርስቶስን መጠቅለያ ጨርቅ በመልበስ እንጂ።

ይህ ተስፋዬ ነው፣ ሕይወቴ፣ ድኅነቴ፣ ክራሬና ዋሽንቴ ነው።

ስለዚህ እነዚህን ለብሼ እመጣለሁ በዚህም በእነርሱ ኃይል የቃላትን ኃይል ተቀብዬ ከመላእክቱ ጋር አብሬ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን” እያልኩ ከእረኞቹ ጋር ደግሞ “ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” (ሉቃ 2፥14) እላለሁ።

ይቀጥላል

https://t.me/KeAbawandebet