Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት አዲስ | ከ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት

አዲስና እንግዳ የሆነ ምሥጢር ይታየኛል፤ እረኞቹ ባዶ የሆነ ድምፅ ሳይሆን የመላእክትን ዝማሬ ሲዘምሩ በጆሮዬ ይሰማኛል።

እግዚአብሔርን በምድር የሰውን ልጅ ደግሞ በሰማይ አይተዋልና መላእክት ይዘምራሉ፤ ሊቃነ መላእክት ያሸበሽባሉ፤ ኪሩቤል ይዘምራሉ፤ ሱራፌልም እያመሰገኑ ሁሉም በአንድነት በዓሉን እያከበሩ ነው።

ከፍ ያለው እርሱ በቀደመው ምክሩ ራሱን ዝቅ አደረገ ። ያ ዝቅ ብሎ የነበረው ሥጋ ደግሞ ለሰው ልጅ ባለው ፍቅር ምክንያት ከፍ አለ።

ዛሬ ቤተልሔም ሰማይ መስላለች ፣ በከዋክብት ፈንታ የመላእክትን ዝማሬ ተቀበለች፤ በፀሐይ ፈንታ ጻድቁን ሳትወስነው ያዘችው። እንዴት እንደሆነ አትጠይቁ ።

እግዚአብሔር ሲፈቅድ /ሲያዝ/ የተፈጥሮ ሕግ ይሻራል።

እርሱ ስለ ፈቀደ ስለ ወደደና ሥልጣን ስላለው ወረደ ፣ አዳነን ። ሁሉንም ነገር ደግሞ እግዚአብሔር ላይ እንዲመሠረት አደረገ ።

ዛሬ ከጥንት ጀምሮ የነበረው እርሱ ተወለደ ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበረውም ያልነበረውን ሆነ ።

እርሱ አምላክነቱ ሳይለቅ እግዚአብሔር ሳለ ሰው ሆነ ። እርሱ ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ አልተለየም።

በተመሳሳይ መልኩም እግዚአብሔር የሆነው ከሰውነት በማደግ አይደለም ።

ነገር ግን አካላዊ ቃል ሆኖ ሳለ መከራ ሊቀበል ስለማይችል ባሕርይው ሳይቀየር ሰው ሆነ።

ነገር ግን በአንድ መልኩ ተወልዶ ሳለ አይሁድ እንግዳ የሆነ ልደቱን አልተቀበሉም ።

ፈሪሳውያን ደግሞ አምላካዊ መጻሕፍትን አሳስተው ተረጎሙ፣ ጸሐፍትም ሕጉ ላይ ከተጻፈው በተቃራኒው ተናገሩ።

ሄሮድስ የተወለደውን ሕጻን ሊያከብረው ሳይሆን ሊገድለው በማሰብ ፈለገው።

ዛሬ ግን ሁሉም ነገር እነርሱን እንደሚቃረናቸው አዩ። መዝሙረኛው እንዲ

መዝሙረኛው እንዲህ ይላል፡- “ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም” (መዝ 78፥4)።

ነገሥታቱ በሰማያዊው ንጉሥ ተደንቀው ሊያዩት መጡ። እርሱ መላእክትንና ሊቃነ መላእክትን፣ ኃይላትን፣ ዙፋናትን፣ አጋእዝትን፣ ሥልጣናትን ሳያስከትል እንግዳ በሆነና ባልተለመደ መንገድ መጥቷል።

እርሱ መላእክቱን ከሥልጣኑ ውጭ ሳያደርጋቸው[1] በመሐላችን ሰው ሲሆንም አምላክነቱን ሳይተው ዘር ካልተዘራበት ማኅፀን ወጣ።

ይቀጥላል

https://t.me/KeAbawandebet