Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-06 13:04:18
መቄዶንያ ለሚሰራው አዲሱ ህንፃ በር እና መስኮት ማስገጠሚያ ድጋፍ እየተሰባሰበ ይገኛል!

መቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እያስገነባ ለሚገኘው አዲሱ ህንጻ በር እና መስኮት ማስገጠሚያ ድጋፍ እየተሰባሰበ ይገኛል።

በአጠቃላይ የሚገጠሙት በሮች ቁጥር 888 እንዲሁም የመስኮቶቹ ደግሞ 739 ሲሆን የአንድ በር ዋጋ 106ሺህ ብር እንዲሁም የአንድ መስኮት ዋጋ 80ሺህ ብር ነው።

ለበር እና መስኮት ማስገጠሚያ ድጋፉ በተለያዩ አማራጮች እየተደረገ ሲሆን፤ ድጋፍ ለማድረግ -

• በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ፣ በዳሸን ባንክ፣ በአቢሲንያ ባንክ እና በአባይ ባንክ - ለሁሉም በተመሳሳይ የሂሳብ ቁጥር 8161 ላይ

• ጎ ፈንድ ሚ (GoFundMe) - Mekedonia Charity Homes

• Cash App: 240-840-6256

• Zelle: 240-840-6256

• WEGEN FUND : https://www.wegenfund.com/causes/

መቄዶንያ በማዕከሉ ላሉ ሰዎች ሁሉንም መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም ምግብ፣ አልባሳት፣ መጠለያ፣ ንፅህና መጠበቂያ፣ ህክምና፣ ትምህርት እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን በመስጠት የአረጋዊያንን እና የአእምሮ እክል ያለባቸውን ህይወት በመርዳት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል።

@EthioipaNews
3.3K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 13:04:18 መከላከያ የሕወሓት ታጣቂዎችን ከዋግ ኽምራ ሊያስወጣ መሆኑ ተሰማ

በፌደራል መንግስትና ሕወሓት መካከል ከተፈረመው የሰላም ስምምነት በኋላም፣ በሕወሓት ቁጥጥር ሥር የነበሩት የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ኹለት ወረዳዎች በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ያሉት ወረዳዎች ጻግብጂና አበርገሌ ሲሆኑ፣ በአካባቢዎቹ ከ67 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የኹለቱ ወረዳ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በችግር ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለከፍተኛ ችግር መዳገራቸውን ተከትሎ ወደ ቀየያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ለማድረግ እየጣርኩ ነው ያለው የዋግ ሕምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ መከላከያ ሰራዊት በአጭር ቀናት ውስጥ አካባቢዎቹን ነጻ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ምኅረት ታምሩ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ መከላከያ ሰራዊት ኹለቱን ወረዳዎች በአጭር ቀናት ውስጥ ከሕወሓት ነጻ በማውጣት የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እንደሚሰራ ለዞኑ አስታውቋል፡፡

በዚህም መከላከያ ሰራዊት ለዞኑ የጸጥታ ማረጋገጫ እስኪሰጥ ድረስ እየተጠበቀ ነው ያሉት ምኅረት፣ ሰራዊቱ በምን አይነት ሁኔታ ወረዳዎቹን እንደሚቆጣጠር አናውቅም ብለዋል፡፡

ይህንኑ መሰረት በማድረግም ጽ/ቤታቸው ከ15 መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር ተፈናቃዮችን ወደየቀያቸው መመለስ ስለሚቻልበትና መልሰው ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ሀሙስ የካቲት 23 በሰቆጣ እንደተወያዩ ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ጽ/ቤቱ መከላከያ ሰራዊት የሚሰጠውን የጸጥታ ማረጋገጫ ተከትሎ የሚያደርጋቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ለመጀመር ከየካቲት 28 ጀምሮ የሚጠቀምበት የክንውን እቅድ ያወጣ ሲሆን፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ዕለታዊ እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ 250 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተነግሯል፡፡

በዚህም መሰረት መንግሥታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ማበርከት የሚችሉትን ካሳወቁ በኋላ ለአማራ ክልል አደጋ መከላልና የምግብ ዋስትና ቢሮ ሪፖርት ይደረጋል ያሉት ምኅረት፣ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ብለዋል፡፡

የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም ከወረዳዎቹ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን፣ ተፈናቃዮች ወደየቀያቸው ከተመለሱ በኋላ የሚኖረውን መልሶ ማቋቋም በተመለከለት የእርዳታ ድርጅቶች እቅዳቸውን እንደሚያቀርቡ ተሰምቷል፡፡

ተፈናቃዮች በአብዛኛው በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ በመሆኑ መጪውን የእርሻ ጊዜ እንዲጠቀሙ ለማድረግ በቅርብ ቀናት ውስጥ መከላከያ ሰራዊት ሕወሓትን ከወረዳዎቹ የማስወጣት ሥራውን እንደሚያጠናቅቅ ያላቸውን ተስፋ የተናገሩት ምኅረት፣ 67 ሺሕ ለሚሆኑት ተፈናቃዮች አሁንም በቂ እርዳታ እየቀረበላቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ሕወሓት የኹለቱ ወረዳዎች አካል የሆኑ 21 ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙ እና ማኅበረሰቡ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያገኝበት ሁኔታ እንዳልነበር ሲገለጽ ነበር፡፡

Via :- አዲስ ማለዳ
@EthioipaNews
3.0K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 18:13:53 በጦርነቱ ምክንያት ትግራይ የሚገኘው የሼባ ቆዳ ፍብሪካ ሙሉ በሙሉ ወድሟል

ከአራት አመት በፊት የትግራይ ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት 2.9 ቢሊዮን ብር ሀብት የነበረው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ንብረትነት የነበረው ሼባ ቆዳ ፍብሪካ መውደሙን ሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ ዛሬ አስነብቧል።

ሼባ በትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ ውስጥ ከሚገኙት 16 ኢንተርፕራይዞች አንዱ ነበር።

በ2004 ዓ.ም ድርጅቱ በ93 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን መቀመጫውንም በውቅሮ ከተማ ነበር። ከትግራይ ክልል መቀሌ 45 ኪሎ ሜትር የሚርቀው ፋብሪካ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ቢያንስ 1,200 ሰዎች ቀጥሮ ያሰራ ነበር።

@EthioipaNews
2.5K viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 18:13:53
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹን እያንገላታ ነው

ባንኩ ዛሬ የአፕሊኬሽን ስርዓቱ ባለመስራቱ ምክንያት ደንበኞች ከፍተኛ ችግር ገጥሞናል ብለዋል።

በተለይሜ አፕሊኬሽኑን በመጠቀም ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ደንበኞቹ ለግልም ለሆነ ለድርጅት አስቸጋሪ ሆኖብናል ብለዋል።

የተለያዩ ክፍያዎችን በዚህ በንግድ ባንክ አፕሊኬሽን ይፈፅሙ የነበሩ ደንበኞች ከጠዋት ጀምሮ ሊያሰራልን አልቻለም ብለዋል።

@EthioipaNews
2.5K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 13:48:42
አዋሽ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

አዋሽ ባንክ ባለፈው ዓመትም በቦረና እና ጉጂ ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 60 ሚሊየን ብር መለገሱን ከባንኩ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል። ባንኩ ከዚህ ቀደም በምዕራብ ኦሮሚያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎችና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ቤት ለፈረሰባቸው ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሷል።

@EthioipaNews
3.3K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:35:30
ነዳጅ

መንግሥት የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ እንዲሆን መወሰኑን የመንግሥት ትራንስፖርት ሚንስቴርና ንግድ ሚንስቴር ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከሐምሌ 2014 ዓ፣ም ጀምሮ በ"ቴሌ ብር" ክፍያ የሚፈጽሙት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ብቻ ናቸው። ሆኖም ሁሉም ተሽከርካሪዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ እንዲጀምሩ እንደተወሰነ ሚንስቴሮቹ መናገራቸውን ዘገባዎች ጠቅሰዋል።

መንግሥት ሌሎች የኤሌክትሪክ ክፍያ አማራጮችን ለመተግበር እንዳሰበም በመግለጫው ላይ ተገልጧል ሲል ዋዜማ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

@EthioipaNews
4.0K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 19:07:43
በዓድዋ በዓል ላይ የጸጥታ ኃይሎች በፈጸሙት ድርጊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተፈጠረውን ችግር አስመለክቶ ባወጣው መግለጫ፣ የጸጥታ ኃይሎች ከገደብ ያለፈ ድርጊት ፈጽመዋል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ፣ በበዓሉ ላይ አላስፈላጊ ኃይል የተጠቀሙ እና ከመጠን ያለፈ እርምጃ ወሰዱ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎ፣ በሕግ ተጠያቂ ከመሆናቸው በተጨማሪ በሕግ አስከባሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው ብሏል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር) በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣  የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተወሰደው እርምጃ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ቢንስ አንድ ሰው መገደሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሊም ኮሚሽነሩ አክለዋል፡፡ በምኒልክ አደባባይ የዓድን ድል ለማክበር፣ እንዲሁም በአቅራቢያው በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን  ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር የተሰበሰበው ሕዝባዊ  በኃይል መበተኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ እና የኹሉንም ሰው ሰብአዊ መብቶች ማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነቱ የሆነው፣ የጸጥታ ኃይል የሚወስዳቸው አላስፈላጊ እና ከመጠን ያለፉ እርምጃዎች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

@EthioipaNews
2.6K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 13:41:04
የዜና ጥቆማ

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን
ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን
ለኦሲኤን ቴሌቪዥን
ለአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን
ለባላገሩ ቴሌቪዥን
ለናሁ ቴሌቪዥን
ለአሻም ቴሌቪዥን
ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን
ለሀገሬ ቴሌቪዥን
ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
ለET ART ሚዲያ
ለንቁ ሚዲያ
ባላችሁበት

ጉዳዩ፡- የዜና ሽፋንን ይመለከታል

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በዛሬው ዕለት የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት መግለጫ የሚሰጥ በመሆኑ ከላይ የተጠቀሳችሁ የሚዲያዎች ብቻ በሰዓቱ ተገኝታችሁ መግለጫውን በመቅረጽና በመዘገብ የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ የተጋበዛችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
@EthioipaNews
948 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 11:28:59
3.5K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 11:28:58
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጥቅም ላይ ያዋላቸው ቀላል እና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በትርዒት ላይ

@EthioipaNews
3.5K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ