Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-21 11:52:30
የቱርክ እና ሶሪያ ድንበር በአዲስ ከባድ ርዕደ መሬት ተመታ፡፡

በቱርክ ሃታይ ግዛት በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 4 እና 5 ነጥብ 8 የተለካ አዲስ ርዕደ መሬት መከሰቱ ተሰምቷል።

እስካሁን በርዕደ መሬቱ ሳቢያ እስከ 5 ሰዎች ለህልፈት ሳይዳረጉ አልቀረም ነው የተባለው።

የአሁኑ አደጋ ከ45 ሺህ በላይ የቱርክ እና ሶሪያ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገው ከባድ ርዕደ መሬት ከተከሰተ ሁለት ሳምንታት በኋላ በድጋሚ የተከሰተ ነው።

የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት (አናዶሉ) እንደዘገበው በአዲሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በርካታ ሕንፃዎች ወድመዋል።

@EthioipaNews
3.7K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 10:30:59
አሜሪካ በቱርክ ለደረሰው ርዕደ መሬት እጇ አለበት የሚል ጥርጣሬ ተነሳ

ኃርፕ የተሰኘው የአሜሪካ ከርሰ ምድር ጥናት ማዕከል ለአደጋው መንስኤ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተጠርጥሯል።

ይህ ገዳይ የርዕደ መሬት አደጋ እንዴት ሊከሰት ቻለ አደጋው ሰው ሰራሽ ነው እና ሌሎችም መላ ምቶች የቀጠሉ ሲሆን ብዙዎች የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ ከአደጋው ጀርባ አለች ብለው እንደሚያስቡ ተገልጿል።

"ሀርፕ" የተሰኘው የአሜሪካ የከርሰ ምድር ጥናት ማዕከል በፈረንጆቹ 1990 በአሜሪካ ህግ አውጪ የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ዓላመውም የመሬትን ውጫዊ ስሪት ለማጥናት በሚል ነበር።

ተቋሙ ጥናቱን ሲያከናውን በከርሰ ምድር ውስጥ ያሉ ኤሌክትሮኖችን ለማሞቅ የራዲዮ ሞገዶችን እንደሚጠቀም ያስታወቀ ሲሆን በዚህ ጊዜ በመሬት የላይኛው ክፍል ላይ መጠነኛ መንቀጥቀጥ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል።

በቱርክ እና ሴሪያ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ እስካሁን ከ45,000 በላይ ዜጎች ሞተዋል።

Via:- Alain
@EthioipaNews
4.0K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 10:40:23
የኤሊክትሪክ ምክኒያት በደጀን ወረዳ የመድሐኔዓለም ቤተክርስቲያን የእሳት አደጋ አጋጥሞታል

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ በሰብሸንጎ ቀበሌ በቀን 12/06/2015 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በኤሊክትሪክ መብራት ምክንያት በተፈጠረ የእሳት አደጋ መድሐኔዓለም ቤተክርስቲያን የመቃጠል አደጋ ገጥሞታል ሲል የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን አስታዉቋል ፡፡ አደጋውን ለመከላከል ህዘብ የተረባረበ ቢሆንም በቀላሉ መከላከል አልተቻለም። በአደጋው እሳት ለማጥፋት ሲሞክር የነበረ የአንድ ሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡

@EthioipaNews
952 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:39:54
ሰበር መረጃ!!

ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል።

እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

@EthioipaNews
2.8K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 12:32:45
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባ ገብተዋል

ጉተሬዝ በነገው እለት በሚጀመረው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጉተሬዝ በነገው እለት በሚጀመረው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@EthioipaNews
2.3K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 15:09:30
የአልሸባብ ታጣቂዎች በሶማሊያ ኪስማዮ ከተማ አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት የጦር ሰፈሮችን መቆጣጠራቸው ተሰማ

በደቡባዊ የወደብ ከተማ ኪስማዮ አቅራቢያ በሚገኘው ባር ሳንጉኒ አካባቢ የአልሸባብ ተዋጊዎች ዛሬ ማለዳ ላይ ሁለት የሶማሊያ ጦር ሰፈር መቆጣጠራቸውን ከሶማሊያ የወጣው መረጃ ያሳያል።

የአልሸባብ ደጋፊ የሶማሌ ሜሞ የተባለው ራዲዮ እንደገለጸው በባር ሳንጉኒ የሚገኙት ሁለቱ ካምፖች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በሰለጠኑት የሶማሊያ ልዩ ሃይል ዳናብ እና የጁባላንድ ክልላዊ መንግስት የደርቪሽ ሃይሎች ተይዘው የነበሩ ናቸው።
የአልሸባብ ቃል አቀባይ ለራዲዮ ጣቢያው እንደገለፀው ታጣቂዎቹ የጦር ሰፈሮችን እና የባር ሳንጉኒ አካባቢን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋል።

እንደ ራዲዮው ዘገባ ከሆነ ጥቃቱ የጀመረው ታጣቂዎቹ ከመንግስት ሃይሎች ጋር ቀጥተኛ ውጊያ ከማድረጋቸው በፊት በመኪና በተጠመደ ቦምብ ነው። የመንግስት ባለስልጣናት እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም።

የሶማሊያ ባለሥልጣናት ትናንት እንዳስታወቁት በመካከለኛው የሙድዩድ ክልል ደቡባዊ አካባቢዎች የሀገሪቱ ጦር ከ75 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድሏል።

Via:- DW
@EthioipaNews
3.1K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 13:54:14
የሞዛምቢክ ፓስተር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም ሲሞክር ህይወቱ አለፈ

አንድ የሞዛምቢክ ፓስተር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀናት የጾመዉን ጾም ክብረወስን ለመጋራት ሲሞክር ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።በሞዛምቢክ ማዕከላዊ ማኒካ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሳንታ ትሪንዳድ ቤተ ክርስቲያን ፓስተር እና መስራች የሆኑት ፍራንሲስኮ ባራጃህ ረቡዕ እለት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

በከባድ ሁኔታ የጤና ችግር ዉስጥ ከወደቀ በኃላ ወደ ቤይራ ሆስፒታል ተወስዶ ሲታከም ቢቆይም ህይወቱ አልፏል።ከ25 ቀናት ጾም በኋላ መቆም፣ መታጠብና መራመድ እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ ክብደት ከድቶት እንደነበር መገለፁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

ከቀናት በኋላ፣ በዘመድ አዝማድና በአማኞች ግፊት፣ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ጤናው ለመመለስ የተደረገው ሙከራ ግን አልተሳካም።በቤተክርስቲያኑ አማኞች ዘንድ እና በጎረቤቶቹ ያሉ አማኞች በሁኔታዎች ለውጥ አልተገረሙም ፣ምክንያቱም ከቅርብ ቀናት ወዲህ የታየበት የሰውነት አካል ለዉጥ በህይወት ለመትረፍ አስፈሪ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

Via:- ዳጉ ጆርናል
@EthioipaNews
3.4K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 13:15:53
እንኳን ደስ አለን/አላቹ

አትሌት ለሜቻ የዳንኤል ኮመንን የ25 አመት ክብረ ወሰን በመስበር ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸንፏል።

አትሌት ለሜቻ ርቀቱን 7 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ከ81 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው። ክብረ ወሰኑ በኬንያዊው ዳንኤል ኮመን ለ25 አመታት ተይዞ የቆየ ነበር። ኮመን በ7 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ከ90 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነበር ክብረ ወሰኑን ይዞ የቆየው።

@EthioipaNews
3.4K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 22:12:51
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሙሉ ቃል።

@EthioipaNews
2.3K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:08:39
#ሰበር_ዜና!!

በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

@EthioipaNews
4.1K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ