2022-09-04 21:53:47
ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ተጨማሪ ውሳኔ!!
የደሴ ከተማ አስተዳደር ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በከተማው ልዩ ልዩ ክልከላዎችን በማስቀመጥ የተቀመጡ ህጎችን እያስተገበረ ይገኛል።
እነዚህ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪ ከነሀሴ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተጨማሪ ክልከላዎችን ያስቀመጥን መሆኑ ታውቆ ህዝቡ ተባባሪ እንድሆን እንጠይቃለን።
1ኛ- የመከላከያ አባል ሳይሆን የመከላከያን የደንብ ልብስ መልበስ ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሳይሆን የልዩ ኃይሉን የደንብ ልብስ ለብሶ በከተማው ውስጥ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። የመከላከያም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይል አባል ሳይሆን የደንብ ልብሱን ለብሶ ሲንቀሳቀስ የተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ።
2ኛ- ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅር ውጭ ተፈናቃይ በመሆን የመጥታችሁ በከተማው በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው ፡፡
3ኛ- ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የጥምር ጦሩን ስም ማጠልሸት ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ የተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ።
ለዚህም የከተማው ማህበረሰብ አሉባልታዎችን በተለያዩ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገጥ ወይም ጥላቻ ለማሳደር የሚሰሩ ኃይሎችን ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
4ኛ- ፀጉረ ልውጥ የሆነ ሰው በምናገኝበት ሰአት ማህበረሰባችን በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል።
5ኛ- በከተማችን የሚገኝ ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት።
6ኛ- ማንኛውም አካል ከመንግስት አደረጃጀት ውጭ ለጦርነቱ በሚል ገንዘብ መሰብሰብ ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ አካል ሊኖር አይገባም ። ሆኖም መንግስት ወጣቱንም ፣ ባለሀብቱን ፣ መንግስት ሰራተኞችና አመራሮችን ወዘተ በማሳተፍ የራሱን የመንግስት አደረጃጀት ተጠቅሞ ለጥምር ጦሩ የሎጅስቲክ ድጋፍ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ በህጋዊ ደረሰኝ ከህዝቡ እየሰበሰበ ጥምር ጦሩ ውስጥ እየተሳተፈ ለሚገኝ ማንኛውም ኃይል ይጠቀምበት ዘንድ ያስረክባል።
7ኛ- በማንኛውም ሰዓት ታርጋ ቁጥር የሌለው ተሽከርካሪ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር ውሎ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ።
የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
Via @Addis_Mereja
@
EthioipaNews
11.6K viewsedited 18:53