Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 61

2022-09-07 19:54:10
ኦነግ ሸኔ በአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃት ማድረሱ ተነገረ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው እና መንግስት “ሸኔ” እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በአርጆ ዴደሳ ስኳር ፋብሪካ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ።

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በምሥራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘውን ፋብሪካ ለሰዓታት ተቆጣጥሮ ከቆየ በኋላ ንብረት ማውደሙን እና ዘረፋ መፈጸሙን የስኳር ኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ታጣቂው ቡድን ስድስት የአርጆ ደዴሳ ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ተሽከርካሪዎችንም ያቃጠለ ሲሆን የሠራተኞችን ሞባይልና ጫማ እንዲሁም ቁጥራቸ የማይታወቅ የድርጅቱን ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ዘርፈዋል ነው የተባለው። የቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገፃቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት በስኳር ፋብሪካው እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ በቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ የመንግሥት ኃይሎች አካባቢውን ጥለው ወደ ደቡብ ሸሽተዋል ሲሉም አስታውቀው ነበር።

@Addis_Mereja
@EthioipaNews
3.6K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:08:34
ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች ካልተነሱ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገለጸች!!

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል።
 
ጦርነቱ በዓለም ዲፕሎማሲ ላይ የተለያዩ መፋለሶችን ያስከተለ ሲሆን ሀገራት ከትብብር ይልቅ ጎራ ለይተው እንዲሰለፉ እያደረገም ይገኛል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ በተለያየ መንገድ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል።

ሩሲያም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ስትሆን ማዕቀቡ ለአውሮፓ ሀገራት የምታቀርበውን ጋዝ ሽያጭ እክል አስከትሏል። ይሄንን ተከትሎም 40 በመቶ ለሚሆኑ የአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ ስታቀርብ የነበረችው ሩሲያ በማዕቀቡ ምክንያት ለአውሮፓውያን ነዳጅ መላክ አለመቻሏን በተደጋጋሚ ገልጻለች።

በነዳጅ ዕጥረት እየተፈተነ ያለው የአውሮፓ ህብረትም በሩሲያ ላይ የጣለውን ማእቀብ እስከማላላት ቢደርስም በሩሲያ ላይ የተጣሉት ሁሉም ማዕቀቦች እስካልተነሱ ድረስ ሩሲያ ምንም አይነት ነዳጅ እንደማትልክ ራሺያ ቱዴይ ዘግቧል።

Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
1.0K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 09:51:59
አሳዛኝ ዜና

የህወሓት ቡድን አንድ እናትና አራት ልጆቿን ጨምሮ 25 ንጹሃንን ረሸነ!!

አሸባሪው የትህነግ ቡድን አባላት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወለህ የመጠለያ ጣቢያ ገብተው 25 ንጹሀንን በግፍ ረሽነዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው አንዲት እናት ከአራት ልጆቿ ጋር በግፍ መረሸኗም ታውቋል። ከጥቃቱ የተረፉ የዐይን እማኞች እንደገለጹት÷ አሸባሪ ቡድኑ በመጠለያ ጣቢያው ያላደረሰው ግፍ የለም፤ ፍጹም እንዳንነሳ አድርጎን ነው የሄደው ብለዋል፡፡

በግፍ ከተገደሉ 25 ንጹሀን መካል አብዛኞች ሕጻናትና ሴቶች ሲሆኑ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ጭምር በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የዋግኽምራ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው አረመኔው ህወሓት ከዚህ ቀደም ከ90 ሺህ በላይ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፡፡

ዛሬም ይህን እኩይ ተግባር አዝሎ የመጣው ትህነግ በመጠለያ ጣቢያ ገብቶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። በእርዳታ የተሰጣቸውን የዕለት ጉርስ ጭምር የዘረፈው የሽብር ቡድኑ÷ የመጠለያ ጣቢያውን ቁሳቁስ ጭምር ማውደሙንም ነው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች የተናገሩት።

via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
2.6K viewsedited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 23:56:17
100 የእርድ ሰንጋዎች

ከአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ሰንጋዎችን በሰሜን ማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር ድጋፍ አደረገ።

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ለሦስተኛ ጊዜ የከፈተውን ወረራ ለመመከት በሚደረገው ርብርብ የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ በአምስቱ ግንባሮች ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን በሰሜን ማይጠብሪ ተከዜ ግንባር የአሸባሪውን የሕወሓት 3ኛ ዙር ወረራ እየተከላከለ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር 100 የእርድ ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርጓል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአማራ ባለሐብቶች 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውን የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ የሎጀስቲክ አስተባባሪ የኾኑት አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን ተናግረዋል። ባለሀብቱ ጥምር ጦሩን ለማገዝ ሙሉ ፈቃደኛ መኾናቸውን ገልጸው በቀጣይም የአልባሳት፣ የፍራሽና የጫማ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን ጠቁመዋል። የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊትም ለጥምር ጦሩ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደቆየ አንስተዋል አቶ ሙሉጌታ።

የግንባሩ ጥምር የሎጀስቲክ ኮሚቴ ለተደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምሥጋናቸውን አቅርበው ፥ሌሎች ኢትዮጵያዊያን የተለመደውን ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥምር ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
4.9K views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:13:42
#ሰበር የድል ዜና

በማይጠብሪ ግንባር በ4 የወራሪው ቡድን አዋጊዎች የሚመራ ሃይል በጥምር ጦሩ ተቀጥቅጦ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።

በተደረገው ዘመቻ ወራሪው ሃይል ይዞአቸው በቆዩ ቦታዎችና ምሽጎች ውስጥ በርካታ ቁጥር ያለው ለሰብአዊ እርዳታ በሚል ወደ ትግራይ ሲገባ የነበረ ዱቄት፣ ሀይል ሰጪ ብስኩት፣ መድሀኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች ተገኝተዋል።

ጥምር ሃይሉ አሁንም በወራሪው ሃይል ላይ ክንዱን እያሳረፈ ግስጋሴውን የቀጠለ ሲሆን ህዝቡ ደጀንነቱን በየአከባቢው እያሳየ ይገኛል።

via @Addis_Mereja
 @EthioipaNews
6.4K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:54:49
አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው!!

ሰልፉ “በአገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት እየተከናወነ ይገኛል። ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለው የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ዲሲ ግብረ ኃይል ገልጿል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ያለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመከባበርና በሁለትዮሽ የጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ እንዲሆን የሚያሳስቡ መልዕክቶች በሰልፈኞቹ ተላልፈዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል ሰልፉን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።

via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
6.9K viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:02:54 ኤፍቢአይ በዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት ከ11 ሺህ በላይ ሚስጢራዊ መረጃዎች ማግኘቱን ገለጸ

በአሜሪካ ህግ መሰሩት ፕሬዝዳንቶች የስልጣን ህጋቸውን ሲጨርሱ ብሄራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ እና ይዘው እንዳይሄዱ ይከለክላል።

ተሰናባች ፕሬዝዳንቶች ይሄንን ህግ ከጣሱ ከባድ ቅጣት የሚጠብቃቸው ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሄንን ህግ ጥሰው ጠቃሚ ብሄራዊ መረጃዎችን ወደ ቤታቸው እንደወሰዱ ይጠረጠራሉ።

የሀገሪቱ የምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ህግ ጥሰዋል በሚል ጠርጥሯቸው ከሰሞኑ ምርመራውን ጀምሯል።

ባሳለፍነው ሳምንት በፍሎሪዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አግኝቻለሁ ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ የኤፍቢአይን ክስ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን ክስተቱ ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ እንዳልሳተፍ የሚደረግ ተንኮል ነው ብለዋል።

በኤፍቢአይ ምርመራ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከፕሬዝዳንት ውድድር ሊታገዱ ይችላሉም ተብሏል።

Via:- Al Ain
Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
7.9K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 23:08:54
አዲአርቃይ ላይ በወገን ጦር የተሰበሩ የዋሻ ምሽጎች!!

ጠላት አንድ ዓመት ከሁለት ወር በላይ ተቆጣጥሮት የነበረውን አዲአርቃይ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት እና ጥምር ጦሩ በትናንትናው ምሽት ነፃ ወጣለች።

በአሁን ወቅት መከላከያ ሰራዊት ወደ ማይፀብሪ እየተጠጋ መሆኑ ታውቋል።

Via
@Addis_Mereja
@EthioipaNews
9.5K viewsedited  20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:01:03
ትምህርት ሚኒስቴር!

የመውጫ ፈተና ለግል እና ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጋራ መመዘኛ መሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የመውጫ ፈተና የሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ እና ዋነኛው የጋራ መወዳደሪያ መስፈርት ነው።

የመውጫ ፈተናን ውጤት መሰረት በማድረግም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እርስ በርሳቸው እንደሚወዳደሩ ሚኒስትር ደኤታው አመልክተዋል።

በመሆኑም ጥሩ ውጤት ሊገኝ የሚችለው ጥሩ ሂደት ሲኖር በመሆኑ ተቋማቱ ተማሪዎች ለውጤት እንዲበቁ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ፋንታ አስገንዝበዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደሩ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻዎች እንደሚሳተፉበትና በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በማእከል እንደሚዘጋጅ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ተማሪዎች ለምረቃ መብቃትና የትምህርት ማስረጃዎቻቸውንም መውሰድ የሚችሉት የመውጫ ፈተናውን ካለፉ በኋለ መሆኑን ጠቁመው፣ በፈተናው ያላለፉ ተማሪዎችም ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ደግመው መፈተን የሚችሉበት አሰራር እንደሚኖር አስታውቀዋል። የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለሚያደርጉት ዝግጅትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።

Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews
9.1K viewsedited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:46:50
ስራተኛዋ ህፃኑን ፍሪጅ ውስጥ ጨምራው በህይወት ተገኘ!!

ሰራተኛዋ በፍሪጅ ውስጥ የዘጋችበት ህፃን ከነ ህይወቱ መገኘቱ ፖሊስ ገለፀ።

በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ቀበሌ 05 ቡዳ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስተሰራ የነበረች አንዲት ሴት በሞግዚትነት የምታሳድገዉን የ11ወር ህፃን በፍሪጅ ውስጥ ከታው መገኘቱን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር አበበች ሸዋረጋ አስታውቀዋል ።

ህፃኑ በፍሪጅ ውስጥ እንደተዘጋበት የታወቀው የህፃኑ አክስት ወደ ቤት ስትገባ ህፃኑ የታለ ብላ ሰራተኛዋን ስትጠይቅ ሻወር ቤት ነው ብላ ትመልሳለች አክስት፣ ተጠራጥራ ሻወር ቤት ገብታ ስትመለከት የለም መጨረሻ አክስት የታፈነ ድምፅ ትሰማለች ፍሪጅ ስትከፍት ህፃኑ በቲማቲም ማስቀመጫ ፖላስቲክ ውስጥ ተቀምጦ ፍሪጅ ውስጥ ተዘግቶበት እንደተገኘ ኮማንደር አበበች ምርመራው ያመለክታል ብለዋል።

ሀላፊዋ እንደገለፁት የህፃኑ እናትና አባት ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አሳዳጊዋ ሰራተኛ ህፃኑ ሁል ግዜ ፍሪጅ እየከፈተ በማስቸገሩ ለማስፈራራት ብላ ፍሪጅ ውስጥ ከታው እንደነበር በወቅቱ ለደረሰችው የህፃኑ አክስት ለምን እንዲህ እንዳደረገች ስትጠይቃት መናገሯን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት እንደምትገኝና ህፃኑ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። ቤተሰብ ህፃኑ ለ2 ሰአት በፍሪጅ ውስጥ ተቀምጦ እንደነበረ ግምታቸውን ይናገራሉ በማለት ኮማንደር አበበች አክለው ገልፀዋል።

Via ሀረሪ ክልል ፖሊስ መምሪያ
Via
@Addis_Mereja
@EthioipaNews
8.9K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ