Get Mystery Box with random crypto!

ኤፍቢአይ በዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት ከ11 ሺህ በላይ ሚስጢራዊ መረጃዎች ማግኘቱን ገለጸ በአሜ | EthioipaNews

ኤፍቢአይ በዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት ከ11 ሺህ በላይ ሚስጢራዊ መረጃዎች ማግኘቱን ገለጸ

በአሜሪካ ህግ መሰሩት ፕሬዝዳንቶች የስልጣን ህጋቸውን ሲጨርሱ ብሄራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ እና ይዘው እንዳይሄዱ ይከለክላል።

ተሰናባች ፕሬዝዳንቶች ይሄንን ህግ ከጣሱ ከባድ ቅጣት የሚጠብቃቸው ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሄንን ህግ ጥሰው ጠቃሚ ብሄራዊ መረጃዎችን ወደ ቤታቸው እንደወሰዱ ይጠረጠራሉ።

የሀገሪቱ የምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ህግ ጥሰዋል በሚል ጠርጥሯቸው ከሰሞኑ ምርመራውን ጀምሯል።

ባሳለፍነው ሳምንት በፍሎሪዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ ከ11 ሺህ በላይ የአሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አግኝቻለሁ ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ የኤፍቢአይን ክስ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን ክስተቱ ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ እንዳልሳተፍ የሚደረግ ተንኮል ነው ብለዋል።

በኤፍቢአይ ምርመራ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከፕሬዝዳንት ውድድር ሊታገዱ ይችላሉም ተብሏል።

Via:- Al Ain
Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews