Get Mystery Box with random crypto!

100 የእርድ ሰንጋዎች ከአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ሰን | EthioipaNews

100 የእርድ ሰንጋዎች

ከአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ሰንጋዎችን በሰሜን ማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር ድጋፍ አደረገ።

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ለሦስተኛ ጊዜ የከፈተውን ወረራ ለመመከት በሚደረገው ርብርብ የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ በአምስቱ ግንባሮች ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን በሰሜን ማይጠብሪ ተከዜ ግንባር የአሸባሪውን የሕወሓት 3ኛ ዙር ወረራ እየተከላከለ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር 100 የእርድ ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርጓል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአማራ ባለሐብቶች 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውን የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ የሎጀስቲክ አስተባባሪ የኾኑት አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን ተናግረዋል። ባለሀብቱ ጥምር ጦሩን ለማገዝ ሙሉ ፈቃደኛ መኾናቸውን ገልጸው በቀጣይም የአልባሳት፣ የፍራሽና የጫማ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን ጠቁመዋል። የአማራ ባለሀብቶች ወቅታዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊትም ለጥምር ጦሩ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደቆየ አንስተዋል አቶ ሙሉጌታ።

የግንባሩ ጥምር የሎጀስቲክ ኮሚቴ ለተደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምሥጋናቸውን አቅርበው ፥ሌሎች ኢትዮጵያዊያን የተለመደውን ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥምር ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

Via @Addis_Mereja
@EthioipaNews