Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-30 16:34:13
ቻይና እና ብራዚል የአሜሪካ ዶላር መጠቀምን ለማቆም ወሰኑ

በዓለም በኢኮኖሚዋ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቻይና እና በላቲን አሜሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ብራዚል የአሜሪካ ዶላርን እንደ መገበያያ ላለመጠቀም ተስማሙ፡፡

ሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጣቸውን ከዶላር ነጻ በማድረግ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያዬት መወሰናቸው የአሜሪካ ዶላር አቅም እንዲዳከም እና ተፅዕኖም እንዲቀንስ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ቻይና ባለፈው ዓመት በሁለትዮሽ ንግድ ሪከርድ 150 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የብራዚል ትልቋ የንግድ አጋር ሆና እንደነበርም የሲጂቲኤን ዘገባ አስታውሷል፡፡

በተመሳሳይ ኬንያ ከሳውዲ አረቢያ ነዳጅ ለመግዛት የአሜሪካ ዶላር ሳይሆን የኬኒያ ሽልንግ ለመጠቀም መስማማቷ ይታወሳል፡፡

@EthioipaNews
2.9K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 22:44:37
ቻይና ቲክ ቶክን በመጠቀም ልትሰልል እንደምትችል አሜሪካ ተናገረች

ባለፈው ሳምንት የቲክ ቶክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለአምስት ሰአት በፈጀው የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጪዎች ጥያቄ ላይ ቻይና በጣም ተወዳጅ የሆነውንና በከፊል በቻይና መንግስት ባለቤትነት ስር በተያዘው መተግበሪያ አሜሪካውያንን ለመሰለል ልትጠቀም እንደምትችል ዋሽንግተን ተናግራለች። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት አለም አቀፍ ኢንተርኔትን በብቃት የተቆጣጠሩ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዴት እንደሚጠቀሙ ግን የምክር ቤቱ አባል የጠቀሱት ነገር የለም።

ዩናይትድ ስቴትስ ከ150 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን አጭር የቪዲዮ መተግበሪያ ለማገድ ስታስብ፣ የሕግ አውጭ አካላት እንደ ጎግል፣ ሜታ እና አፕል ያሉ ኩባንያዎች በባህር ማዶ የሚገኙ የአሜሪካ ነዋሪ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ያልተገደበ የስለላ ሥራ እንዲያመቻቹ እያደረጉ መሆኑ ግን ተጠቁሟል።የኮንግረሱ አባል የሆነችውን አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ-ኮርትዝ ጨምሮ ተጠቃሚዎች በቲክቶክ ላይ የህግ አውጭዎች ብሔራዊ እገዳን ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ አደባባይ በመውጣት ተቃውመዋል።

ከአሜሪካ በተጨማሪ ቲክ ቶክን ለማገድ ካናዳ፣ብሪታኒያ ፣ፈረንሳይ ፣የአውሮጳ ህብረትና የኒውዝላንድ የምክር ቤት አባላት የደህንነት ስጋት ደቅኖብናል በሚል እየተንቀሳቀሱ ይገኛል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@EthioipaNews
1.2K views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 09:48:14
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ስብሰባውን እያካሄደ ነው!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እስካሁንም ከኦነግ ከሸኔ፣ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ዜጎች፣ አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሸጥ ከመቸገሩ ጋር በተያያዘ፣ ወደ አዲስ አበባ ምርት እንዳይገባ ከመከልከሉ ጋር፣ ከክልሎች የርስ በርስ መናበብ አለመቻል፣ የሱዳን ወታደሮች ወረው የያዙትን የኢትዮጵያ መሬትና ያወደሟቸውን ንብረቶች የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል።አሁንም የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው።

@EthioipaNews
2.1K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:44:38
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15 ይካሄዳል!!

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15 ድረስ በበይነ-መረብ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል። የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑም ተጠቁሟል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ባሉ ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ይሆናልም ብለዋል።

@EthioipaNews
3.7K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 13:04:15
አዲስ አበባ

የትግራይ ክልል ግዚያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ

----ምሽቱን በአዲስ አበባ----
@EthioipaNews
2.2K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 10:31:59 ጠቅላይ ሚንስትሩ ለፓርላማ ማብራሪያ ሊሰጡ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች፤ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ መሆኑ ታውቋል፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ መጋቢት 19፤ 2015 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎችን የሚሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚያዳምጥ እና የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ያስገቡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

ከአንድ ወር ዕረፍት በኋላ የተመለሱት የፓርላማ አባላቱ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 9፤ 2015 በተወካዮች ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በነበራቸው ስልጠና ይኸው እንደተነገራቸው ምንጮቹ ገልጸዋል።ይህንኑ ያረጋገጡት አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፓርላማ አባል፤ “ ‘በአስቸኳይ አስገቡ’ ብለው ባለፈው ቅዳሜ ነገሩን። ቀን ላይ ነግረውን፤ ‘እስከ ማታ ድረስ’ አሉን” ሲሉ ለጥያቄ ማቅረቢያ የተሰጠው አጭር ጊዜ እንደነበር አስታውሰዋል።

የፓርላማ አባሉ አክለውም፤ “ብዙዎቻችን ‘አይሆንም፤ ተረጋግተን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርብ አይነት ጥያቄ በአግባቡ ማዘጋጀት አለብን’ ስንል እስከ እሁድ አመሻሽ ድረስ አቅርቡ ተባለ” ሲሉ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ ቀን እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል።በዚህ አካሄድ እስከ ባለፈው ሳምንት እሁድ አመሻሽ ድረስ፤ የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አስገብተው ማጠናቀቃቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

በነገው ዕለት በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል፤ “የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ ይኖራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቁመዋል። “ወደ አዲስ አበባ አትገቡም እየተባለ ወደ አማራ ክልል የሚመለሱ ሰዎች” ጉዳይን የተመለከቱ ጥያቄዎችም፤ በነገው የፓርላማ ስብሰባ ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል ምንጮች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

[Ethiopia Insider]
@EthioipaNews
3.0K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 13:30:20
ወልቂጤ ዝም ጭር ብላለች።

@EthioipaNews
4.4K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 15:15:48
ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ አግኝተው ከተመረጡ በኃላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ርዕሰ መስተዳደር አድርገው እንደሾሟቸው ትላንት የጠ/ሚ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

@EthioipaNews
3.4K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 13:12:49
ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ተሸካሚ የውሃ ውስጥ ድሮን ሙከራ አደረገች!!

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላን (ድሮን) ሙከራ ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ የዜና ጣቢያ ገለጸ፡፡

የውሃ ውስጥ ድሮኑ ከ80 እስከ 150 ሜትር ባለ ጥልቀት ውስጥ በውሃ ውስጥ ከ59 ሰአታት በላይ ከተጓዘ በኋላ በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ መፈንዳቱን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል። ድሮኑ በውሃ ውስጥ ከተተኮሰ በኋላ “የራዲዮአክቲቭ ማዕበል” ሊያስነሳ የሚችል መሆኑንም ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ይህንን ሙከራ በበላይነት የመሩ ሲሆን አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ “የሰሜን ኮሪያ ያልተገደበ የኒውክሌር ጦርነትን የመከላከል አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እየተጠናከረ መሆኑን እንዲገነዘቡ” ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ፖሲዶን ከተሰኙት የሩሲያ የውሃ ውስጥ ተተኳሾች ጋር እንደሚመሳሰሉ የተነገረላቸው የሰሜን ኮሪያ የቅርብ ጊዜ መሳሪያዎች የባሕር ላይ ማዕበል በማስነሳት በአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተሞችን ሊያወድሙ ይችላሉም ነው የተባለው።

“ሚስጥራዊው መሳሪያ” ማክሰኞ ከደቡብ ሃምጊዮንግ ግዛት ወጣ ብሎ በሚገኘው ውሃ ውስጥ መቀመጡም ነው የተነገረው።

“ሃኤይል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የጦር መሳሪያ የጠላት መርከቦችን እና ወደቦችን በከፍተኛ የራዲዮአክቲቭ ሞገድ ለማጥቃት ታስቦ የተነደፈ መሆኑንም ተሰምቷል፡፡

አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ የጋራ ልምምዳቸውን ባለፈው ረቡዕ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በኮሪያ ልሳነ ምድር ዳግም ውጥረት መንገሱ ይነገራል። ይሁንና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል÷ ሰሜን ኮሪያ በግዴለሽነት ለምታደርገው ትንኮሳ ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ተደምጠዋል።

@EthioipaNews
3.7K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 16:25:38
የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወሰነ

የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መተመኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ በሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት እግድ የተጣለባቸውን ዜጎች በቅዱሱ ጉዞ አላሳትፍም ብሏል፡፡

ቀድሞ በፌደራል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ብቻ ይሰጥ የነበረው የምዝገባ አገልግሎት በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ወደ ሐጃጁ በማቅረብ ምዝገባውን በ16 ጣቢያዎች በየአካባቢው እንደሚከናወን ተገልጿል።

በመግለጫው የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል መቅረብ ይኖርበታል የተባለ ሲሆን ማንኛዉም ተመዝጋቢ የሚከተሉትንን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል ፦

1. የታደስ የነዋሪነት መታወቂያ/ መንጃ ፈቃድ
2. የጉዞ ሰነድ (ፖስፖርት ) የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ9 ወራት በላይ የቀረው መሆን ይኖርበታል፡፡
3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ
4. የኮቪድ ክትባት የወሠደበት ማስረጃ እንዲሁም የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ (ቢጫ ካርድ) ማቅረብ ይጠበቅበታል።
5. እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የሚችሉ ወይም አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተዉና ክፍያ ከፍለው ሊያግዛቸው የሚችል ሰው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

@EthioipaNews
3.0K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ