ቻይና ቲክ ቶክን በመጠቀም ልትሰልል እንደምትችል አሜሪካ ተናገረች ባለፈው ሳምንት የቲክ ቶክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለአምስት ሰአት በፈጀው የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጪዎች ጥያቄ ላይ ቻይና በጣም ተወዳጅ የሆነውንና በከፊል በቻይና መንግስት ባለቤትነት ስር በተያዘው መተግበሪያ አሜሪካውያንን ለመሰለል ልትጠቀም እንደምትችል ዋሽንግተን ተናግራለች። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት አለም አቀፍ ኢንተርኔትን በብቃት የተቆጣጠሩ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዴት እንደሚጠቀሙ ግን የምክር ቤቱ አባል የጠቀሱት ነገር የለም። ዩናይትድ ስቴትስ ከ150 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን አጭር የቪዲዮ መተግበሪያ ለማገድ ስታስብ፣ የሕግ አውጭ አካላት እንደ ጎግል፣ ሜታ እና አፕል ያሉ ኩባንያዎች በባህር ማዶ የሚገኙ የአሜሪካ ነዋሪ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ያልተገደበ የስለላ ሥራ እንዲያመቻቹ እያደረጉ መሆኑ ግን ተጠቁሟል።የኮንግረሱ አባል የሆነችውን አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ-ኮርትዝ ጨምሮ ተጠቃሚዎች በቲክቶክ ላይ የህግ አውጭዎች ብሔራዊ እገዳን ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ አደባባይ በመውጣት ተቃውመዋል። ከአሜሪካ በተጨማሪ ቲክ ቶክን ለማገድ ካናዳ፣ብሪታኒያ ፣ፈረንሳይ ፣የአውሮጳ ህብረትና የኒውዝላንድ የምክር ቤት አባላት የደህንነት ስጋት ደቅኖብናል በሚል እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። Via:- ዳጉ ጆርናል @EthioipaNews 1.2K views19:44