Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-15 13:10:03
የአሜሪካ ድሮን ከሩሲያ የጦር ጀት ጋር ተጋጭቶ ወደቀ!

የሩሲያ የጦር ጀቶች ከአሜሪካ የቅኝት ሰው አልባ በራሪ (ድሮን) ጋር ተጋጭቶ ጥቁር ባሕር ውስጥ መውደቋን አሜሪካ የገለጸች ሲሆን፣ ድርጊቱንም ኃላፊት የጎደለው ነው ብላለች።አሜሪካ ድሮኑ በዓለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ በመደበኛ የቅኝት በረራ ላይ እንዳለ ሁለት የሩሲያ ተዋጊ ጀቶች ሊጠልፉት እንደሞከሩ ገልጻለች።

ክስተቱ በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት ሩሲያ እና አሜሪካ ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ የተፈጠረውን ስጋት አጉልቶታል።ሆኖም ሩሲያ ተዋጊ ጀቶቹ ከድሮኗ ጋር ምንም አይነት ግኙነት አልነበራችወም ብላለች።የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ድሮኑ በራሱ ምክንያት መውደቁን ጠቁሟል።

“ኤምኪው 9 የተባሉት የጦር አውሮፕላናችን በዓለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ጊዜ በሩሲያ የጦር አውሮፕላን ተጠልፎ ተመቷል። በውጤቱም ድሮኑ ተከስክሶ ወድሟል” ሲል የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ኤስዩ 27 የተባሉት የጦር ጀቶች ድሮኑን ከመግጨታቸው በፊት “ኃላፊነት በጎደለው መንገድ፣ ከአካባቢ ጥበቃ አንጻር ባልተገባ እና ሙያዊ ባልሆነ መንገድ” በተደጋጋሚ ነዳጅ ሲያፈሱ ነበር ብሏል።ድርጊቱን በመቃወም አሜሪካ በዋሽንግተን የሚገኙትን የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭን ለማብራሪያ ጠርታለች።

[BBC]
@EthioipaNews
4.9K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 08:44:26
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ!

ብሊንከን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በይፋዊ ጉብኝታቸውም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።በሰሜን ኢትዮጰያ የነበረውን ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

[EBC]
@EthioipaNews
4.9K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 19:01:25
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱን ጦር ለእውነተኛ ጦርነት ዝግጅት እንዲያደርግ ትእዛዝ አስተላለፉ!!

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጦራቸው ለ'እውነተኛ ጦርነት ልምምድ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል ።

መሪው ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱ ጦር የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እና ሙከራዎች አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታውን ኬ.ሲ.ኤን.ኤ ዘግቧል።የሀገሪቱ የከባድ መሰሳሪያ ዩኒት ለሁለት ከፍተኛ ተልእኮዎች መዘጋጀት እንዳለበትም ነው መሪው በመልእክታቸው ያስታወቁት።

የመጀመሪያው ተልእኮ ጦርነትን ቀድሞ ተከላክሎ ማስቀረት ሲሆን፤ ሁለተኛው ተልእኮ ደግሞ ጦርነት ውስጥ የበላይት ለመውሰድ እንደሆነም አስታውቀዋል ነው የተባለው።ሰሜን ኮሪያ እያደረገች ያለውን የሚሳዔል ሙከራዎች አጠናክራ ቀጥላች የተባለ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሐሙስ የአጭር ርቀት የባላስቲክ ኪሳዔሎችን ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች።

ሰሜን ኮሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋሽንግተን አጋሮቿ እያደረጉት ያለውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የቀጠናውን ሁኔታ ወደ “ቀይ መስመር” እንደወሰደው በተለያዩ ጊዜያት ስትናገር መቆየቷ ይታወሳል። በኮሪያ ልሳነ ምድር ለተፈጠረው ውጥረት አሜሪካን ተጠያቂ የምታደርገው ሰሜን ኮሪያ ከአሁን በኋላ የሚደረግ ማንኛውም የዋሽንግተን ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥረውም አሳስባለች።

@EthioipaNews
2.6K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 15:18:11
ባጃጆች እንዳይሰሩ መታገዳቸው በርካታ ችግሮችን እንዳስከተለ ተነገረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድንገት በከተማዋ ውስጥ የባጃጅ ትራንስፖርትን ላልተወሰነ ጊዜ በማገዱ ምክንያት ችግሮች ማጋጠማቸውን ለአዲስ ማለዳ ቃላቸውን የሰጡ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡

የባጃጅ ትራንስፖርት መታገዱን ተከትሎ አዲስ ማለዳ ቅኝት ባደረገችባቸው ባጃጆች ይንቀሳቀሱባቸው በነበሩ የጉዞ መስመሮች የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር መኖሩን ተመልክታለች፡፡

በዚህም የተጓዦች ረዥም ሰልፎች የተስተዋሉ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ፍላጎቱን ለማሟላት በጋማ እንስሳት የሚንቀሳቀሱ ጋሪዎች ጥቅም ላይ የዋሉባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ተስተውሏል፡፡

የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አስተያየቱን ለአዲስ ማለዳ የሠጠ ወጣት፣ በከተማ አስተዳደሩ በድንገት የተወሰነው እግድ በሕይወቱ ላይ ስጋት እንደፈጠረበት ተናግሯል፡፡ 5 የቤተሰብ አባላቱን በሚሰራው ሥራ እንደሚያስተዳድር የተናገረው ወጣቱ፣ የገቢ ምንጬ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብሏል፡፡ የከፋ ችግር ከፊቴ ተደቅኖ ይታየኛል የከተማ አስተዳደሩ በውሳኔው ጫና የደረሰባቸውን የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶችን ጉዳይ መመልከት አለበት ሲልም ተናግሯል፡፡

“የከተማ አስተዳደሩ አካሂዳለሁ ያለውን ጥናት ባጃጆች በዚህ መልኩ ሳይታገዱ ማካሄድ ይችል ነበር።” ያሉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ደግሞ፣ ከከተማዋ የትራንስፖርት ችግር አንጻር ውሳኔው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው ብለዋል፡፡

አሰጣጥ ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩ በርካቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ መ

Via addismaleda
@EthioipaNews
3.0K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 22:14:04
በአዲስ አበባ በቀን ሰባት ጥንዶች የጋብቻ ፍቺ ይፈፅማ

ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ከ1ሺህ 300 በላይ የትዳር ፍቺዎች ተመዝግበዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ይህም በአማካኝ ሲሰላ በቀን ሰባት ጥንዶች በህጋዊ መልኩ ፍቺ ይፈፅማሉ ማለት ነው።

ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ የተመዘገበው የፍቺ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ተቀራራቢ ሲሆን፤ በ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 623 የፍቺ ምዝገባዎች መደረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 16 ሺህ 35 ፍቺዎች እንደተካሄዱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ቤቴልሔም እንደሚገልጹት መረጃዎቹ የሚያመላክቱት በመስሪያ ቤቱ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡትን ብቻ ነው።

እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ በተለያዩ ቦታዎች በህጋዊም ሆነ በባህላዊ መልኩ ፍቺ እና ጋብቻ ይከናወናል፤ ነገር ግን ወደ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መተው የሚመዘገቡት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ናቸው።

@EthioipaNews
2.5K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 21:32:46
ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የዓረብ ሊግ ያወጣውን መግለጫ አትቀበለውም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የዓረብ ሊግ ያወጣውን መግለጫ እንደማትቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሊጉ በትናንትናው ዕለት ለአንድ ወገን የወገነ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ጉዳዩን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚህም የሕዳሴ ግድቡን የግንባታ ሥራና የውሃ ሙሌትን የማስተዳደር ስራ ለሚመለከታቸው ለተፋሰሱ የአፍሪካ ሀገራት ሊተው እንደሚገባ አንስቷል፡፡

ስለግድቡ ጉዳይ የሚመለከታቸው የተፋሰሱ ሀገራት እንዳሉ ለማስታወስ አንፈልግም ያለው መግለጫው ሊጉ መሰረታዊውን ዓለም አቀፍ ህግ ባላከበረ መልኩ የአንድ ሀገር ቃል አቀባይ ሆኖ እያገለገለ ነው ብሏል፡፡የአፍሪካ ህብረትም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህን በመከተል ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅን ለማቀራረብ የሦስትየሽ ድርድር ሲያመቻች መቆየቱን ጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጫማሪም ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዙሪያ በራስ ወዳድነት በምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ድርድሩን ማዘግየቷን መግለጫው አመላክቷል፡፡ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት በፅኑ እንደሚደግፍ ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም መንግስት በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተፈረመውን የስምምነት አዋጅ በመከተል የግድቡን ግንባታና ውሃ ሙሌት የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@EthioipaNews
2.6K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 08:56:11
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ተከለከለ

ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃክ አገልግሎት መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ "የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ እገኛለው" ብሏል።

የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

@EthioipaNews
2.8K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 08:50:27
ዛሬ ማርች 8 ነው።

ዛሬ ማርች 8 የሴቶች ቀን ነው።ለመሆኑ ዕለቱ ለምን ይከበራል?

• ከ3 ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ተደፍራለች (UN)
• በአለማችን ዕድሜቸው ከ15 እስከ 44 የሆኑ ሴቶች ከካንሰር፣ ከጦርነት፣ ከመኪና አደጋና የወባ በሽታ ይልቅ አስገድዶ የመደፈር ስጋት ያሳስባቸዋል (UN)
• 603 ሚሊዮን ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ወንጀል ባልሆነባቸው አገራት ውስጥ ይኖራሉ (UN)
• በአሁኑ ወቅት በአለማችን 700 ሚሊዮን ያህል ሴቶች ዕድሜያቸው 18 ዓመት በታች ሆነው ያገቡ ሲሆን 250 ሚሊዮን ሴቶች ደግሞ ዕድሜያቸው 15 ዓመት በታች ሆነው ያገቡ ናቸው (UNICEF)
• በየአመቱ በአለም ላይ ከ600-800 ሺህ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውሮች ይካሄዳሉ፡፡ ከሚካሄደው የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ከአምስት አራቱ ሴቶች ነው፡፡ (Trafficking.org)
• በየአመቱ 62 ሚሊዮን ሴቶች የትምህርት ዕድል አያገኙም (Makers)
• የአለማችን116 ሚሊዮን ሴት ተማሪዎች (25 በመቶ ያህሉን የሴት ተማሪዎችን ቁጥር ይዛል) አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አያጠናቅቁም፡፡
• በአለማች ለሴቶች የሚከፈለው ክፍያ ከወንዶች አንጻር ከ60-75 በመቶ ያነሰ ነው (PBS)
• 155 አገራት ሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚገድብ ህጎች ሲኖራቸው 100 አገራት ደግሞ ሴቶች የሚሰሩትን የስራ አይነት ገድበዋል (The Guardian)
• በየደቂቃው አንድ እናት በወሊድ ምክንያት ትሞታለች (UN)
• በአለማች 200 ሚሊዮን ሴቶች በግዳጅ ይገረዛሉ (World Health Organization)

@EthioipaNews
2.8K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 23:32:53
አዲሱ የዓባይ ድልድይ ግንባታ 94 በመቶ ተጠናቀቀ።

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት 94 በመቶ መጠናቀቁ ተሰምቷል። የድልድዩ ተሸካሚ ምሰሶዎችና ከመሬት በታች የቋሚ ተሸካሚ መሰረቶች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የድልድዩ 760 ሜትር ርዝማኔ ካለው "ግራይደር" ውስጥ 380 ሜትሩ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።

በተጨማሪም ለድልድዩ የሚያስፈልጉ 8 ቋሚ ተሸካሚ ምሰሶዎች ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቃቸውና የቀሩት በቅርቡ ለመጨረስ እየተሰራ ነው፡፡ ግንባታውን እየተከናወነ የሚገኘው በቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ተቋራጭ ሲሆን መንግስት ለግንባታው 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት መድቧል።

በ2011 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከሚጀመርበት ጊዜ ጀምሮ ለ100 ዓመታት እንዲያገለግል ተደርጎ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል። የድልድዩ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ ስድስት መኪኖችን ማሳለፍ የሚያስችል ሲሆን የፊታችን ሰኔ 2015 ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@EthioipaNews
482 views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 09:50:38
ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተነገረ

ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል። ኢንተርኔት ከተዘጋ ዛሬ 28ኛ ቀኑን ይዟል።

Via - capital
@EthioipaNews
3.7K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ