Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-23 22:24:30
በቦረና ዞን የተረጂዎች ቁጥር ከ604 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለጸ

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ማሊቻ ሎጄ (ዶ/ር) ድርቁ በቦረና ብቻ ሳይሆን ሁለቱን የጉጂ ዞኖች ጨምሮ በ10 ዞኖች የተከሰተ መሆኑን ጠቅሰው ቦረና ግን ቆላማነቱ ከሌሎቹ አካባቢዎች ከፍተኛ በመሆኑ የጉዳቱ መጠንም በዚያው መጠን ሊጨምር ችሏል ነው ያሉት።

በድርቁ ወደ ተጎዳው የቦረና ዞን ሄደው ያለውን ሁኔታ መመልከታቸውን የገለጹት ምክትል ሃላፊው በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ አጦት ሰውነታቸው እንደተጎዳ መታዘባቸውን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቦታው ድረስ ተገኝተው በአካባቢው ከሚገኙ ሰዎች ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

እንደ ክልሉ በሁለት ወቅቶች ማለትም በየካቲት እና ሰኔ የድርቁ ሁኔታ ያለበትን ለማወቅ ጥናት ይካሄዳል ያሉት ምክትል ሃላፊው በዚሁ መሠረት ዘንድሮም ድርቁ መቀጠሉ ሰለተረጋገጠ ክልሉ ዕቅዶችን አውጥቶ በየደረጃው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

በአራት ዙሮች ተከፍሎም ዕርዳታ እየተሰጠ እንደሚገኝ እና ለቦረና ብቻ እስከ ሦስተኛ ዙር በክልሉ እና ፌዴራል መንግሥት ትብብር ለ375u ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ማቅረብ መቻሉን ጠቅሰው በአራተኛው ዞር የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ የተረጂዎች ቁጥር 604 ሺህ እንደ ደረሰም ገልጸዋል።

@EthioipaNews
5.4K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 21:07:11
በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ኦሮሚኛ ቋንቋ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተሰጠ መሆኑን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ፣ ኦሮሚኟ ቋንቋ የሚያስተምሩ 2 ሺህ 600 አስተማሪዎችን ለመቅጠር አስቤያለሁ ማለቱን ዘገባው አመልክቷል። የከተማ አስተዳደሩ፣ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች ኦሮሚኛ ቋንቋ ሁለተኛ ቋንቋ ሆኖ እንዲሰጥ በቅርቡ መወሰኑ ይታወሳል። ትምህርቱ የሚሰጠው፣ ከሦስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ሲሆን፣ በከተማዋ ካሉት 786 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ባሁኑ ወቅት ትምህርቱ በ624 ትምህርቱ እንደተጀመረ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ መናገሩን ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@EthioipaNews
5.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 21:26:31
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በሱ ሳዶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት

አትሌት በሱ ሳዶ ከሁለት ወንድሞቿ እና ከሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ባለቤቷን በመግደሏ፣ ድርጊቱን መፈጸሟ በመረጋገጡና እሷም የእምነት ክህደት ቃላን በመስጠቷና ባሏን እንደገደለችው በማረጋገጧ በሷና በአንደኛው ወንድሟ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የ27 ዓመቷ አትሌት በሱ ሳዶ እና ባለቤቷ ተሻለ ታምሩ የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ አባል ነበሩ።

በሱ ባለቤቷ “እንዳይሳካልን በቤተሰቤ፣ በእናቴ፣ በወንድሞቼ እና በእኔ ላይ ያስጠነቁላል” በሚል ይህንን ወንጀል እንደፈጸመች ቃሏን በሰጠችበት ወቅት መናገሯን ቢቢሲ አስነብቧል ።

በጥንዶቹ መካከልም ከገንዘብ ጋር በተያያዘ አለመግባባት እንደነበር ተከሳሿ በሰጠችው የእምነት የክህደት ቃል ላይ መስፈሩን ተገልጿል።

ከዚህ ግድያ በፊት ይህች አትሌት ሟችን እንደምታስገድለው ትዝትበት እንደነበር ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ወቅት እንደ ደረሰበት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ግን የዚያኑ ዕለት ሌሊት ስለጠፉ እስካሁን ድረስ ያሉበት እንዳልታወቀ እና በፖሊስ እየተፈለጉ መሆናቸው ተገልጿል። የትዳር አጋሮቹ በቆይታቸው ልጅ ባይኖራቸውም የተለያየ ንብረት ማፍራታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

@EthioipaNews
2.2K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 19:22:52
በመቀሌ የሚገኘው የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ ዳግም ስራ መጀመሩን አስታወቀ

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የሚገኘው የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ ምርት ካቋረጠ ከሁለት አመታት በኋላ ዳግም ስራ መጀመሩን አስታዉቋል።

የለስላሳ መጠጥ ፋብሪካዉ ፤ ከተፈረመዉና ተግባራዊ መደረግ ከተጀመረዉ የሰላም ስምምነት በኋላ በተያዘዉ ሳምንት ዳግም ስራ መጀመሩን የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብዙነህ ፎሌ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ብዙነህ ገለፃ ፤ በቅርንጫፉ ከዚህ ቀደም የነበሩ ሁሉም ሰራተኞች ወደስራቸዉ ተመልሰዋል። በዚህም ከ 4 መቶ በላይ የሆኑ ሰራተኞች ካሳለፍነዉ ሰኞ እለት ጀምሮ ዳግም በስራ ገበታቸዉ ላይ ለመሆን በቅተዋል ብለዋል።

ተቋሙ ስራ ባቋረጠባቸዉ አመታት ያጋጠመዉን ኪሳራ በሚመለከት ጥናት የሚካሄድና ወደፊት የሚገለጽ መሆኑን አቶ ብዙነህ አክለዋል። የተጀመረዉም የሰላም ሂደት ላለፉት ሁለት አመታት ከስራ እና ከደሞዝ ዉጪ የነበሩ ሰዎችን ዳግም ወደቀደመ ህይወታቸው የሚመልሳቸዉ መሆኑን የማርኬቲንግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ከሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በኋላ መነቃቃቶች እየታዩ መሆኑን ብስራት ራዲዮ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

Via:- ዳጉ_ጆርናል
@EthioipaNews
3.2K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 15:54:31
"ዜጎችን በአገራቸው ባይተዋርና ስደተኛ የሚያደርግ ነዉ"

በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ተገለፀ!!

በቅርቡ በተመሰረተውና ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው በተባለው ሸገር ከተማ ስር በተካተቱ ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሱሉልታ እና ገላን በተባሉ አከባቢዎች ዜጎች ለአመታት የኖሩባቸው መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በሳምንት ውስጥ መፍረሳቸን የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአመታት ያፈሩት ሃብትና ንብረት በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አፈርነት ከመቀየሩም ባለፈ ያልተገቡ ድብደባና ማዋከቦች እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል።መድረሻ ያጡ ዜጎችም በመስጊድ፣ በቤተክርስቲያን እና በሜዳ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው የሚገልጹት።

በአዲስአበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ከሰብዓዊነት ባፈለገጠ መልኩ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ተናግረዋል።

“ሲሆን አገራት ለዜጎቻቸው ቤት ሰርተው ይሠጣሉ” የሚሉት ዋና የህዝብ ዕንባ ጠባቂው ዜጎች ጥሪታቸውን አሟጠው የሠሩትን ቤት ያለበቂ ካሳና መጠለያ በማናለብኝነት ማፍረስ ከመንግስት የሚጠበቅ ተግባር አለመሆኑን ተናግረዋል።

እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ዜጎችን በአገራቸው ባይተዋርና ስደተኛ የሚያደርግ ነዉ ብለዋል። በሂደቱም ከገበሬ የተገዙና ካርታ ከሌላቸው ውጪ ካርታ ያላቸውን ህጋዊ ቤቶች ጭምር እየፈረሱ መሆናቸው ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

ሼር ያድርጉ!
@EthioipaNews
78 views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 14:38:38
የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1ዓመት ከ8ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ፋስት መረጃ ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሮ ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር አቅርቦ የአቃቢ ህግን ማስረጃዎች ባለማስተባበሉ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል ፡፡

ሼር ያድርጉ!
@EthioipaNews
1.1K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 12:20:15
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ቅሬታ ቀረበበት
የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ወራሾች “ፍቅር እስከ መቃብር”ን በተመለከተ ለኢቢሲ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ።

የ“ፍቅር እስከ መቃብር” ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ወራሾች፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) መጽሐፉን ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ቀይሮ “የማስተላለፍ መብት የለውም” ሲሉ ለተቋሙ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል።

ወራሾቹ ለኢቢሲ በላኩት ደብዳቤ የመፅሃፉ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ በህይወት በነበሩበት ወቅት “ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፍን “በፊልም እና ቲያትር መልክ ተሰርቶ ለገበያ እንዲቀርብ” ስምምነት ፈጽመው የነበረው “ሜጋ ማስታወቂያ ኢንተርፕራይዝ” ከተባለ  ድርጅት ነው ብለዋል።

ሆኖም ሜጋ ከዓመታት በኋላ “ከስሞ በመዘጋቱ በመጽሐፉ ላይ የባለቤትነት መብት ያለን እኛ ወራሾቹ ብቻ ነን ያሉ ሲሆን የመጽሐፍ የመብት ባለቤትነት ወደ ኮርፖሬሽኑ የተላለፈበት አግባብ "የኛ ህጋዊ እውቅና የሌለው ነው” በማለት የቅሬታ ደብዳቤ አስገብተዋል።

ይህ ደብዳቤ እንደደረሰው የገለጸው ኮርፖሬሽኑ፤ በጉዳዩ ላይ የተቋሙ አመራሮች ውይይት ካደረጉ በኋላ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

Via:- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@EthioipaNews
2.2K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 10:20:06
ፑቲን ከአሜሪካ ጋር የነበራቸውን የኒውክሌር ስምምነት ማቋረጣቸውን አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በተመለከተ የነበራትን ስምምነት ማክበር አይጠበቅባትም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ ባደረጉት ረጅም ንግግር፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ኪየቭ ያደረጉትን ያልተጠበቀ ጉብኝት ጨምሮ በበርካታ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ማብራራያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ጦርነቱ የተቀሰቀሰው እና የተስፋፋው "አሜሪካ እና አጋሮቿ የኃይል ጥማት ስላለባቸው ነው" በማለት ምዕራባውያኑን ወቅሰዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይድን በዚህ ሰዓት  ከኔቶ ምስራቃዊ  አጋሮች ጋር ለመመካከር ፖላንድ ይገኛሉ።
የአልጀዚራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ቢያንስ 8ሺህ ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡

@EthioipaNews
2.8K views07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 00:36:34
በቦረና የተከሰተው ድርቅ አስከፊ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በሺ የሚቆጠሩ እንሰሳት ረግፏል። በመቶ ሺ ሰዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ።

@EthioipaNews
3.7K views21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:01:22
መምህር ምህረተአብን ጨምሮ ሌሎችም በእነ ፌቨን ክስ ስር የተካተቱት እንዲሁም ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከተማ በዛሬው እለት ከእስር ተፈተዋል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን በቤተ ክርስቲያኗ በመምህርነት የሚያገለግሉ ሰባኬ ወንጌላውያንን ጨምሮ የማኅበራት ተወካዮችን እንዲሁም የችግሩን እውነታ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚናገሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል።

ለአብነትም በእስር ላይ ከሚገኙት መካከል መምህር ምሕረተአብ አሰፋ፣ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪ ፌቨን ዘሪሁን እና ሌሎችም መታሰራቸው ይታወሳል። በተጨማሪም ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ (ጋዜጠኛ እና ደራሲ) በጸጥታ ኃይሎች ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።

በዛሬው እለትም መምህር ምህረተአብን ጨምሮ ሌሎችም በእነ ፌቨን ክስ ስር የተካተቱት እንዲሁም ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከተማ ከእስር ተፈተዋል።

@EthioipaNews
1.7K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ