Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-02 09:17:05
''አድዋ የነፃነት ሳይሆን የድል ቀናችን ነው''

አድዋ ማለት አባቶቻችን በሀይማኖት እና ዘር ሳይከፋፈሉ ለሀገር አንድነት ከጫፍ እስከጫፍ ተነስተው ጣሊያንን አሸንፋዋል ውድ ህይወታቸውን መስዕዋት አድርገዋል ይህ ትልቅ ዋጋ ያለው የድል ቀን የሱጠበት ነው አድዋ

ይህን የድል ቀን ባይኖር ሀይማኖታችን ማንነታችን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ቀለማችን ጠፍቶ ውብ እና ድንቅ የሆኑ ባህሎቻችን ጠፍተው ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሆኑት እንሆን ነበር ባህል,ቋንቋ እንዲሁ ሀይማኖት የቆየው በአባቶቻችን ነው

1888 ታላቁ ድል የተገኘበት ቀን ነው

እነሱ ደማቸውን አፍሰው የሰጡንን የድል ቀን እንደ በሬ ቅርጫ አንከፋፍለው የጋራ ነገር ሁሌም የማረ ነው ድሉ የመላው ኢትዮጵያዊያን ነው!

   ክብር ለጀግኖች ለአባቶቻችን
@EthioipaNews
3.8K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:15:26
አዲስ አበባ ሚኒሊክ አደባባይ የአድዋን የድል በዓለ ለማክበር የተሰባሰቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአድማ በታኝ ተበትነዋል።

@EthioipaNews
3.5K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 17:50:26
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና በ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳስታወቁት፤ሚኒስቴሩ የሥራ ገበያውን እና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን እንዳዘጋጀም ነው የጠቆሙት፡፡

በዚህም መሰረት ከቴክኒክና ሙያ ውጪ ባሉ ማዕከላት የሚስተናገዱትን ሳይጨምር በሥልጠና ዘመኑ 608,666 የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሯ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፤ በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች ግን የሚስተናገዱት በ 2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል፡፡

የ2015 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ላይ ተያይዟል።

@EthioipaNews
4.6K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 17:50:26
የዛሬ ሶስት ከደምቤ ዶሎ ዩንቨርስቲ ታግተው ደብዛቸው የጠፋ  17 ተማሪዎችን የሚያስታውስ   በሴቶችና  በህፃናት  ጥቃት  ላይ ማዕከል ተመሰረተ

"ህዳር 25  የሴቶች  እና  የህፃናት ጥቃት  መብት ጥበቃ እና  የማህበራዊ  የተሃድሶ  ማዕከል "የተባለው  አዲሱ ተቋም  በጋዜጠኛ መዓዛ  መሀመድና  በአጋሮቿ የተመሰረተ ነው።
ህዳር 25  2012 ዓ.ም   ከአማራ ክልል የመጡ 17 ሰባት ተማሪዎች  ከደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ  ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ   ታግተው አሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ይታወቃል።

ዛሬ ምስረታውን  አስመልክቶ  በነበረው  ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ  የማዕከሉ የቦርድ ሰብሳቢ  መዓዛ  መሀመድ እንደተናገረችው "  በጦርነትና በተለያየ ግጭት  ሴቶችና ህፃናት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከደረሰባቸውም ህጋዊ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ  " እንደሚሰራ ተናግረዋል።

@EthioipaNews
4.2K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:02:31
ቅዱስ ፓትርያርኩ መቐለ ገቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት በሰላም መቐለ ገብተዋል።ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው መቐለ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

[Ethio FM]
@EthioipaNews
4.4K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:00:19
"በኢትዮጵያ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 3.99 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል"- ኦቻ

የተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) የሰብዓዊ ምላሽ እቅድ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 3.99 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

ይኽም በተፈጥሯዊ እንዲሁም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ 20 ሚሊዮን ዜጎችን ለመድረስ ያለመ ነው።

የሰብዓዊ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው 20 ሚሊዮን ዜጎች 4.6 ሚሊዮኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሲሆኑ፤ 13 ሚሊዮኑ 5 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች በማለፉ በድርቅ የተጎዱ መሆናቸውን ጠቅሷል።

በድርቁ ምክንያት አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር በሆኑ አከባቢዎች በተለይም ምስራቃዊ እንዲሁም ደቡባዊው የሀገሪቱ ክፍል የምግብ ዋስትና እጦት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት መዳከም ለበሽታና ወረርሽኝ ተጋላጭነትን ከፍ አድርጓል።

የኦሮሚያ እንዲሁም የሶማሌ ክልሎች ከድርቁም በተጨማሪ በግጭት ጭምር ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸውን ሪፖርቱ ይጠቅሳል። እንደ ኦቻ እቅድ በ 2023 ቅድሚያ የተሰጣቸው ሥራዎች የአፋጣኝ የህይወት አድን ተግባራት ማከናወን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ደህንነቱ በተጠበቀ እና ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ እንዲቀርብ ማስቻል እና የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራዎችን መደገፍ ናቸው።

@EthioipaNews
4.6K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 17:24:23 የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳለፈ!

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት ስብሰባ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳልፏል።

የአሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ኑሮ እና ተጠቃሚነት በመሠረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ሰፊ መሠረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሠራሮችን በመዘርጋት ሲሠራ መቆየቱን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውሷል።

ባለፉት ዓመታት ውስጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የዕድገት ደረጃ መሠረት በርካታ ከተሞችን በመመሥረት ሰፋፊ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በተደረበት የዕድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ሕዝቡን እና ክልሉን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ሕገ-ወጥነትን በመቆጣጠር በከተሞች ውስጥ እየታዩ ያሉ ውስብስብ ሁኔታዎችን ለማስተዳደር ያለውን አደረጃጀት እየፈተሹ እና እያሻሻሉ መሄድ አስፈላጊ ነው ብሏል የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ።

በመሆኑም ከተሞቹ ያላቸውን መልካም ዕድል ወደ አንድ በማምጣት አብረው እንዲለሙ እና የጋራ ዓላማ እንዲኖራቸው፣ በአንድ ፕላን በመተዳር ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲኖራቸው፣ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት ኖሯቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ሙያን ለማስፋፋት፣ የቢዝነስ አስተሳሰብን ለማዳበር እና የአገልግሎትን ለማሻሻል የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሁለት እና ከዚያ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ ለማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለአስተዳደር በሚያመች መንገድ የከተሞቹ አደረጃጀት እንደሚከተለው ተከናውኗል።

1. ቢሾፍቱ ከተማ፦ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ዲሬ በመቀላቀል በ3 ክፍለ ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

2. ሻሸመኔ ከተማ፦ የሻሸመኔ ከተማ እና የቢሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክፍለ ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

3. አዳማ ከተማ፦ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክፍለ ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

4. ሮቤ ከተማ፦ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክፍለ ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

5. ማያ ከተማ፦ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክፍለ ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

6. ባቱ ከተማ፦ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመልማት ዕድል ያላቸው ከተሞቻን በተሟላ መንገድ በመጠቀም ሁለንተናዊ የሆነ ልማት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች እና ወረዳዎችን ልማት እንዲያፋጥኑ ለማድረግ እና የአመራርን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግሥት እንዲሆን ተወስኗል።

1. መቱ ከተማ
2. አጋሮ ከተማ
3. ቡሌ ሆራ ከተማ
4. ነጆ ከተማ
5. ሰንዳፋ በኬ ከተማ
6. ሸኖ ከተማ
7. ሞያሌ ከተማ
8. ዶዶላ ከተማ
9. ሻኪሶ ከተማ

በተመሳሳይ መልኩ የከተሞች የማስፈፀም አቅማቸው ተሻሽለው ፈጣን እና ከእንግልት የፀዳ አገልግሎት በሙሉ አቅም እንዲሰጥ እና ሁሉአቀፍ የሆነ ልማት እንዲመዘገብ ለማድረግ እንደ አጠቃላይ እየተደረገ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የከተሞችን ዕድገት መሠረት በማድረግ የከተሞችን ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።

1. አዳማ፣ ሻሻመኔ እና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ
2. የሮቤ ከተማ እና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ
3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌ እና ሻኪሶ ከተሞች፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።

በሌላ መልኩ ለረጅም ጊዜ ሲነሳ የቆየውን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት ለማስመዝገብ፣ በድንበር አካባቢ ያለውን ሕገ ወጥነትን ለመቅረፍ፣ በድንበር አካባቢ ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚከሰተውን የሰላም ሁኔታን ለመፍታት እንዲሁም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ ውጤታማ የሆነ አደረጃጃት እና አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የምሥራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።

በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምሥራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-

• ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
• ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
• እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል።

በአዲሱ አደረጃጀት የምሥራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

በልላ በኩል ለማኅበረሰቡ ተደራሽ የሆነ አደረጃጀት ለመፍጠር የመሬት ስፋት፣ የፀጥታ ችግር፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እና ፈጣን ልማት ጥያቄን ለማረጋገጥ የመደ ወላቡ ወረዳ የነበረ በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳ እና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ እና የጭናክሰን ወረዳ የነበረ በሁለት ወረዳ ማለትም የጭናክሰን ወረዳ እና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ መወሰኑን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@EthioipaNews
3.0K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 14:46:06
ቴዲ አፍሮ በቦረና ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል የ1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) ብር ድጋፍ አድርጓል።

ዓድዋ 127 ለቦረና በሚል መሪ ሐሳብ ጉዞ ዓድዋ ከኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ጋር በመሆን በድርቅ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጠው የቦረና ሕዝብ በአስቸኳይ ድጋፍ እንያደርግ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዚህ ዘመቻ የመጀመሪያውን 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር በመለገስ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ታውቋል።

”በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መሪነት መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዓድዋ ላይ ወራሪን ድባቅ በመምታቱ በዓለም የነጻነት መድብል ውስጥ ኢትዮጵያ የታሪክ ማማ ላይ መስፈር ችላለች። 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ኹሉ በትብብር እና በአንድነት በመቆም የአያቶቻችንን አደራ መጠበቅ ይገባናል።” ሲልም መረጃውን ያጋራው ያሬድ ሹመቴ ገልጿል።

@EthioipaNews
3.7K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 14:44:24 መንግሥት ለአርሶ አደሩ የስንዴ መሸጫ ዋጋ አስገዳጅ ተመን አወጣ!

መንግሥት አርሶ አደሩ የስንዴ ምርቱን በመንግሥት ለሚተዳደሩ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በተተመነላቸው ዝቅተኛ ዋጋ እንዳቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በአማራ ክልል አንድ ኩንታል ስንዴ 3 ሺሕ 200 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን አዲስ ማለዳ የክልሉ ግብርና ቢሮ አረጋግጣለች፡፡

ቢሮው የክልሉ የስንዴ ግዥ አስተባባሪ ግብረ ኃይል በወሰነው ውሳኔ መሰረት፣ በገበያው ላይ የስንዴ ምርት መግዣ ዋጋ ከ3 ሺሕ 800 ብር እስከ 4 ሺሕ ብር የደረሰ መሆኑን ገልጾ፣ ለዋጋ ንረቱ ዋነኛ ምክንያት የስንዴ ነጋዴዎችና የዱቄት ፋብሪካ ነጋዴዎች የሚያደርጉት ግብይት ነው ብሏል፡፡

ክልሉ ለዋጋ ንረቱ ያስቀራል ያለውን ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን፤ በዚህም በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል የስንዴ ግዥ እስከሚጠናቀቅ እነዚህ አካላት ግብይት እንዲያቆሙ ቁጥጥር እንዲደረግበት ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

አርሶ አደሩ የስንዴ ምርቱን በወጣለት ዋጋ መሰረት ለኅብረት ሥራ እንዳቀርብ ውሳኔ የተላለፈው በፌደራል መንግሥት ደረጃ መሆኑም ተሰምቷል፡፡ መንግሥት የአርሶ አደሩን የትርፍ ህዳግ ጨምሮ አንድ ኩንታል ስንዴ በ3 ሺሕ 200 ብር እንዲገዛ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡

ይህ ውሳኔ በሌሎች ክልሎችም የተላለፈ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሩ አንድ ኩንታል ስንዴ በ3 ሺሕ 500 ብር ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡ ክልሉ ከአርሶ አደሩ በተመነው ዋጋ የገዛውን ስንዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ለውጭ ገበያ አቀርበዋለሁ ላለው የስንዴ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል፡፡

በወቅታዊ የስንዴ መግዣ ዋጋ እና ውሳኔው ተመጣጣኝ ባለመሆኑ የመሰረታዊ ሕብረት ሥራ ማኅበራት እና ዩኒየኖች የተቀመጠላቸውን አምስት በመቶ የትርፍ ህዳግ ጨምሮ ኩንታል በ3 ሺሕ 350 ብር ግዥ ይፈጽማሉ ተብሏል፡፡

የፌደራል መንግሥት ክልሎች ከአርሶ አደሩ በተቆረጠ ዋጋ ስንዴ እንዲገዙ የፋይናንስ አቅርቦት ያቀረበ ሲሆን፣ ለአማራ ክልል ስንዴ መግዣ ብቻ ገንዘብ ሚኒስቴር 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መላኩ ተሰምቷል፡፡

አርሶ አደሩ መንግሥት ያቀረበውን የዋጋ ተመን ላይ ቅሬታ እንዳለው፣ አዲስ ማለዳ ካነጋገረቻቸው አርሶ አደሮች ሰምታለች፡፡ ምንም እንኳን እንደየአካባቢው ቢለያይም መንግሥት የገበያ ዋጋ ከመተመኑ በፊት አንድ ኩንታል ስንዴ በነጻ ገበያ ከ4 ሺሕ እስከ 5 ሺሕ ብር ተሸጧል፡፡

አርሶ አደሩ ያመረተውን ስንዴ ለገበያ አቅርቦ እራሱ በወሰነው ዋጋ ነጻ በሆነ ሕጋዊ ገበያ መሸጥ እንዳይችል የመንግሥት ዋጋ ተመን ይከለክላል፡፡ መንግሥት ይህን የገበያ ገደብ የጣለው በተመነው ዋጋ ከአርሶ አደሩ ስንዴ ሰብስቦ ስንዴ ለውጭ ገበያ አቀርባለሁ ያለውን እቅዱን ለማሳካት መሆኑ ተሰምቷል፡፡

መንግሥት እንዳስታቀው ከኢትዮጵያ ፍጆታ የሚተርፍ የስንዴ ምርት ስላለ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎች ከመንግሥትን ሀሳብ በተቃራኒ፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተረጅ ሆኖ የውጭ ረጅዎችን እጅ በሚጠብቅበት ሁኔታና ብዙዎች በተራቡበት ሁኔታ ከፍጆታ ተርፎ ለውጭ ገበያ መቅረቡን አይቀበሉም፡፡

[Addis Maleda]
@EthioipaNews
3.4K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 12:21:09
የአድዋ ዜሮ ኪ.ሜ ፕሮጀክት ግንባታ 78.2% ደርሷል ተባለ።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ክፍት እንደሚሆን የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ የአድዋ ታሪካዊ ዳራን ከጅማሬው የሚዳስስና የፓን አፍሪካን መንፈስ የተላበሰ እንደሆነ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የግንባታ አስተዳደር ዳይሬክተር ዳዊት ጥበቡ(ኢ/ር) ተናግረዋል።

አብዛኛው የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጪ የሚገባ በመሆኑና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት በሎጀስቲክስ ዘርፉ ላይ ባደረሰው ተጽዕኖ የግንባታ ሥራው ሊጓተት እንደቻለም አስረድተዋል።ከቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር ችግሩ መቀረፉንም አብራርተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን

@EthioipaNews
3.9K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ