Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-19 11:20:06
በአዲስ አበባ ትላንት ምሽት በጣለዉ ከባድ ዝናብ አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር ጨምሮ አራት ሰዎችን ወሰደ

የአራቱ ሰዎች አስከሬን ፍለጋ ላይ ይገኛል

በአዲስ አበባ ትላንት ምሽት 12:05 ሰዓት የጣለው ከባድ ዝናብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታዉ ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ የነበረ መኖሪያ ቤት ዉስጥ የነበሩ የ3፣ የ13፣ የ15 ዓመት ታዳጊ ህፃናትን ጨምሮ የ46 ዓመት ሴት በጎርፉ መወሰዳቸውን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።

መረጃዉ የደረሰዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የዋናተኛ ቡድን የሟቾቹን አስከሬን በመፈለግ ላይ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የ46 ዓመቷ ሴት በጎርፍ  የተወሰዱት የ13 እና የ15 ታዳጊዎች ወላጅ እናት ሲሆኑ ከእነሁለት ልጆቻቸው በጎርፉ መወሰዳቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የ3 ዓመት ታዳጊ ህፃን ከሌላኛው ቤት ጎርፉ እንደወሰዳት ታውቋል።

@EthioipaNews
3.9K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 09:39:39
ለሚቀጥለው ዓመት የነዳጅ ፍጆታ ግዥ ለመፈጸም አራት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

ለ2016 በጀት ዓመት የነዳጅ ፍጆታ 212 ቢሊዮን ብር ወይም ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን፣ ግዥውን ለመፈጸምም የጨረታ ሒደት መጀመሩ ታውቋል።

የቀጣዩ ዓመት ነዳጅ ፍላጎት አራት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሆን፣ የዘንደሮ በጀት ዓመት አጠቃላይ የነዳጅ ፍላጎት ደግሞ 3.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነው። በመሆኑም የቀጣዩ ዓመት የነዳጅ ፍላጎት ከ2015 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር የ200‚000 ሜትሪክ ቶን ጭማሪ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አጠቃላይ የነዳጅ አቅርቦት በየዓመቱ በአማካይ በአሥር በመቶ የሚጨምር ቢሆንም የቀጣዩ በጀት ዓመት የነዳጅ አቅርቦት የአምስት በመቶ ብቻ ጭማሪ እንደሚኖረው መነገሩን ሪፖርተር ዘግቧል።

@EthioipaNews
3.8K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 13:05:24
በመተሃራ ከተማ የሸኔ ታጣቂዎች ፈፀሙበት በተባለው ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገድለዋል

ባሳለፍነው እሮብ ምሽት የሸኔ ታጣቂዎች በመተሃራ ከተማ በፈፀሙት ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ዳጉ ጆርናል ከመተሃራ ከተማ ምንጮቹ አረጋግጧል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ካጡ ዜጎች መካከል ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከአዳማ ከተማ ወደ መተሃራ ከተማ ያቀናው አገልጋይ ሳሙኤል እና አገልጋይ መስፍን ሽፈራው እንደሚገኙበት ዳጉ ጆርናል አረጋግጧል።

በጥቃቱ ሌሎች ስድስት የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደተገደሉ ተሰምቷል።በጥቃቱ ዙሪያ የከተማ አስተዳደሩ የሰጠው መግለጫ የለም።የአገልጋይ ሳሙኤል አስክሬን ወደ አዳማ ከተማ መምጣቱ ተሰምቶል።

@EthioipaNews
3.3K views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 07:07:09
ሰበር

አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳን የሽግግር መሪ (ፕሬዚዳንት) አድርጎ ሾሙዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፕሬዚዳንት ካልሆንኩ ብሎ ሞቼ እገኛለሁ ቢልም በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ጌታቸው ረዳ በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።

@EthioipaNews
5.0K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 16:34:21
በኢትዮጵያ የታሸገ ውሃ ታሪክ ቀዳሚው እና ለታሸገ ውሃ የወል ስም እስከመሆን የበቃው ሃይላንድ ውሃ በድጋሜ ገበያውን በይፋ መቀላቀሉን ተናገረ ።

ሃይላንድ ውሃ በግብር ምክንያት ከምርትም ከገበያም ጠፍቶ መቆየቱን ሰምተናል።ለምርቱ መቋረጥ ምክንያት ሆኖ የቆየው የግብሩ ጉዳይ ከሁለት ዓመት በፊት እልባት ማግኘቱን ኩባንያው ተናግሯል።ይሁን እንጂ ኩባንያው ከዓመት በላይ በተለያየ ምክንያት ምርት ሳይጀምር ቆይታል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ሃይላድ ውሃ በእህት ኩባንያው አስኩ ኃ/የተ/የግ ኩባንያ እየተመረተ በሩብ፣ በግማሽ፣በአንድ፣በአንድ ተኩል እና ሁለት ሊትር ለገበያ እየቀረበ ይገኛል ተብሏል።በቀን እስከ 60,000 እሽግ ውሃ ማምረት እንደሚችልም ሰምተናል።

ከ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል ስራ የጀመረው ሃይላንድ ውሃ ለ 600 ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን ኩባንያው ለሸገር በላከው መረጃ ላይ ጠቅሷል።

የውሃ ፋብሪካዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረትና በሌሎችም እየተፈተኑ ፣አንዳንዶቹም እየተዘጉ ነው።ሃይላንድ ውሃ ግን በደንበኞቼ አዕምሮ ውስጥ ባስቀመጥኩት ጥሩ ስሜ የተነሳ ችግሮች ቢኖሩም በዘርፉ የመወዳደር አቅም አለኝ ብሏል።ኩባንያው የ10 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ነድፎ ስራ መጀመሩን ተናግሯል፡፡

[Sheger FM]
@EthioipaNews
6.0K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 14:36:54
አዲስአበባ

የተቋረጠው የባጃጅ_ትራንስፖርት አገልግሎትን አስመልከቶ ዛሬ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት 9 ሰዓት የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋረጠውን የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ " አሻም ቴሌቪዥን " ዘግቧል። የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የዕለቱ ጉርሳቸውን ማጣታቸውን፣ ተጠቃሚዎችም ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ይታወቃል።

@EthioipaNews
5.4K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 14:00:47
አሜሪካ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ ተግባራዊነትን ተከትሎ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኗን አንቶኑ ብሊንከን ገለጹ

አንቶኒ ብሊንከን በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተለይም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቃለመጠይቁም ዩናይትድ ስቴትስ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራች መሆኑን ነው የገለፁት።

ይህም አሜሪካ፥ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያበረታታ ተናግረዋል።

የሰላም ስምምነቱ በሚመለከታቸው አካላት ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ ኢትዮጵያን ምርቶቿን ከኮታና ቀረጥ ነፃ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንድታስገባ ወደ ሚፈቅደው የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለስ ቁርጠኛ ናት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር የጀመረችውን ጥረት ያደነቁት አንቶኒ ብሊንከን፥ የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ሒደት በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

@EthioipaNews
3.1K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 13:59:54
በአዲስ አበባ አንድ ኪሎ ጤፍ ከ50 እስከ 56 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የኑሮ ጫና እንዲያቀሉ የተለያዩ የእህል ምርቶችን ወደ ገበያ እያስገባ እንደሚገኝ አስታውቋል።በዚህም መሠረት አንድ ኪሎ ጤፍ ከ50 እስከ 56 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ የሕብረት ሥራ ማሕበራት እና የተለያዩ 10 የመሸጫ አካባቢዎች ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ የእህል እና የግብርና ምርቶች ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ እየተደረገ እንደሚገኝ የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

ለገበያ ከቀረቡት የእህል ምርቶች መካከል ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና ገብስ በብዛት ወደ ገበያ የገቡ ሲሆን፤ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶችም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

የእህል አቅርቦቱ በኦሮሚያ ነጋዴዎች ዩኒየኖች በኩል የተከናወነ ሲሆን፤ በቀጣይ የገበያ ትስስር በመፍጠር እጥረቱና የዋጋ ውድነቱ እስኪቀረፍ ድረስ አቅርቦቱ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ምክትል ፕረዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ፤ በከተማዋ የተፈጠረው የጤፍ ዋጋ መወደድ በአንዳንድ ነጋዴዎች የተፈጠረ ነው ያሉ ሲሆን፤ ችግሩን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመነጋገር ምርት ማቅረቡን ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የዋጋ ንረቱን ለማባባስ ምርት በሚደብቁ እና ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@EthioipaNews
3.0K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 13:58:18 #ባጃጅ

" በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሰጥ እገዳ መጣሉና በተለያዩ ሰብአዊ መብቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ገደብ የሚጥል እርምጃ በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው ብሏል።

ኮሚሽኑ ይህንን በተመለከተ በላከልን መግለጫው እገዳውን ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአ/አ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

ኃላፊዎቹ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በከተማዋ ወደ 10 ሺህ የሚገመቱ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ናቸው።

- እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ በከተማዋ አሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋላቸው መሆኑን፣ ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች አሉ።

- ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ከዋና መንገዶች ውጪ ባሉ ውስጥ ለውስጥ መንገዶች እስከ ሁለት ኪሎ ሜትር ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ማስተካከያ እየተወሰደ ቢቆይም በአንዳንድ አካባቢዎች ባጃጆቹ ከተቀመጠላቸው የእንቅስቃሴ አካባቢ ውጪ በዋና መንገዶች ላይ ሲሠሩ በመታየታቸው እና የከተማው የትራንስፖርት ፍሰት ላይ ጫና ፈጥሯል።

- እገዳው በሁሉም ቦታ የተደረገው ልዩነት እና መድሎ ላለመፍጠር ነው፡ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የሚሠሩ በመሆኑ አሠራሩን ስለማሻሻል ከማኅበራቱ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ነበሩ።

ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል እገዳው በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ በመሆኑ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎቹንና ቤተሰባቸውን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎችንም ችግር ላይ እንደጣለ መረዳት እንደተቻለ ገልጿል።

መንግሥት ሰዎች ሥራቸውን እና የመረጡትን መተዳደሪያ ያለአግባብ እንዳያጡ ማድረግን ጨምሮ የመረጡትን እና የተቀበሉትን ሥራ እንዲሠሩ የማስቻል ኃላፊነት አለበት ያለው ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 41(1) መሠረት “ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት ” ያለው መሆኑን በንዑስ-አንቀጽ 2 እንደተመለከተው ደግሞ መተዳደሪያውን፣ ሥራውን እና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው ማለቱን ጠቅሷል።

ይህ መተዳደሪያን የመምረጥ/በመረጡት ሥራ የመሰማራት መብት (the right to choose one’s livelihood/work) ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችም የተረጋገጠ መብት ነው ሲል ኮሚሽኑ አስገንዝቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  በባጃጅ የትራንስፖርት ሥራ የተፈጠሩትን ችግሮች በተገቢው ሕጋዊ እርምጃዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስተዳደር እና ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ማድረግ ሲገባ በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ከላይ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶችን አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው ብለውታል።

በተለይ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

@EthioipaNews
2.7K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 19:20:18
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች

ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረጉ፡፡

አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡ ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑ ተገልጿል። ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

@EthioipaNews
4.2K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ