Get Mystery Box with random crypto!

EthioipaNews

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioipanews — EthioipaNews
የሰርጥ አድራሻ: @ethioipanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.38K
የሰርጥ መግለጫ

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation.

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-26 21:13:00
#MoE

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር።


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444
@EthioipaNews
2.9K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 21:13:00
እስክንድር ነጋ ተፈቷል!!

እስክንድር ነጋ ከባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመታወቂያ ዋስ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶ መፈታቱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንዱሁም ከእስክንድር ነጋ ጋር አብረው የታሰሩ ወጣቶችም ተፈተዋል።


@EthioipaNews
2.7K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 14:29:39
ቦረና

እየሆነ ያለው እየሰማን የምንገኘው ነገር ሁሉ ልብ የሚሰብር ነው!!

የበረሀው መርከቡ ፅኑው፣ ጥምና ረሀብ ቻዩ እና ብርቱው ግመል በቦረና እንዲህ ከተጎሳቀለ የፍየሉ፣ የበጉ፣ የበሬውና ላሙን እጣፈንታ ወዳጄ አስተንትነው። ይህ የተለየ ዘመን ነው። ዘመኑ መንግስት ለህዝቡ ደንታ ቢስ የሆነበት ዘመን ነው። ህዝብ ግን ለህዝብ እንደጥንቱ ያዝናል፣ ይረዳል፣ ክፉ ዘመንን አብሮ ይሻገራል።

ቦረናን እንርዳ
@EthioipaNews
2.9K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 11:43:18
ሸገር ከተማ በዛሬው እለት በይፋ ወደ ስራ ገብቷል።

ሸገር ከተማ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ስራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

ቀድሞ የነበሩ 6 ከተሞችን አንድ በማድረግ በ12 ክፍለ ከተሞች እና በ36 ወረዳዎች የተዋቀረው ሸገር ከተማ በዛሬው እለት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት በይፋ ስራ መጀመሩን ኦቢ ኤን ዘግቧል።

@EthioipaNews
3.6K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 08:59:13 በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ "ሸገር ከተማ አስተዳደር" በርካታ ነዋሪዎች የክልሉ መንግሥት መኖሪያ ቤታችን "ያለ ማስጠንቀቂያ" እያፈረሰብን ነው ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

በለገጣፎ አካባቢ ቤታቸው እየፈረሰባቸው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ድርጊቱ "የብሄር ማንነትን የለየ" መሆኑን መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የአዲሱ ሸገር ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ አስተዳደሩ እያፈረሰ ያለው የግንባታ ፍቃድ የሌላቸውን ቤቶች" መሆኑን እንደገለጸና ድርጊቱ "ብሄርን የለየ ነው" መባሉን እንዳስተባበለ ዘገባው አመልክቷልል።

@EthioipaNews
4.0K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 22:38:15 ሰበር ዜና

ግልፅ አቋም! ጎንደር ወልቃይጥ ጠገዴ

ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስና ህልውናችንን ለማስከበር እንሠራለን"

የሕግ ማሕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሐቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን! "

"#የህወሓት ወራሪ ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴ አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውና በሕዝባችን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር፤ ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ሕዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን!"

*

እኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ፣ የካቲት 17 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ጎንደር  ከተማችን ተሰባስበን “በፈተና እንፀናለን፤ በሥራ እንገለጣለን፡- ዘላቂ የሕግ አሸናፊነት” በሚል  ርእስ ከመከርን በኋላ፤ የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡-

1) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መሆኑን በማመን፤ እስከመጨረሻው ከወገኖቻችን ጋር ፀንተን ለመቆም ተስማምተናል!

2) ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ፤ ከዚህ በኋላም ለሚደረገው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ትግል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ እና ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል ቃል እንገባለን!

3) የወልቃይት ጠገዴ ትግል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሰማዕት የሆኑበት መሆኑን በመረዳት፤ የትግሉን ሰማዕታት አደራ ለመጠበቅ እንተጋለን!

4) የማንነት ትግሉ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጥያቄው ተጋሪ እንዲሆኑ እና ከፍትሕ ጎን እንዲቆሙ እውነታውን ለማስገንዘብ እንሠራለን!

5) የማንነት ትግሉ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች አገር ዐቀፍና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እውነታውን ተገንዝበው ከፍትሕና ከእውነት ጎን እንዲቆሙ እንሠራለን!

6) ትግሉ ለጥቂት ግለሰቦች የሚሰጥ እና የውስን ጊዜ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም የማንነት ትግሉ የሁላችንም፣ የሁልጊዜም እና አሸናፊ እስከምንሆን የምንቀጥልበት መሆኑን በማመን፤ እያንዳንዳችን የትግሉ መሪ ተዋናዮች መሆናችንን በተግባር እናረጋግጣለን!

7) አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ፍትሕ ሲሰፍን ነው፡፡ ስለሆነም፤ የትግራይ ወራሪ ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴ አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውና በሕዝባችን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር፤ ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ሕዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን!

8) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን፤ የትግሉ አስኳልና የአገራዊ ለውጡ ቀንዲል በመሆኑ፤ ገዥው ብልጽግና ፓርቲና የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት በእጁ ያሉትን የሕግ ማሕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሐቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን!

9) ወራሪው ኃይል ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር፤ እንደተለመደው በዕብሪት ተነሳስቶ በሕዝባችን ላይ ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ መሆኑን በመገንዘብ፤ “ዋነኛው ሠራዊታችን ሕዝባችን ነውና” በሁሉም ማዕዘን የሚኖረውን ሕዝባችንን አንቀሳቅሰን ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስና ህልውናችንን ለማስከበር እንሠራለን!

10) የጎንደር ሕዝብ በየዘመናቱ የፀረ እኩልነትና ፀረ ፍትሕ ኃይሎች ሲለባ ሲሆን የቆየ ሕዝብ ነው፡፡ ስለሆነም፤ የግፈኞች የጭቆና ሰለባ በመሆናችን፤ በአገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላምና ሁለንተናዊ ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው ፍትሕ እና እኩልነት ሲረጋገጥ መሆኑን በማመን፤ ሁልጊዜም ከፍትሕና እኩልነት ጎን የምንቆም ሆናችንን እናረጋግጣለን!

ሁላችንም ሁልጊዜም አሸናፊዎች እስከምንሆን እንታገላለን!

@EthioipaNews
5.2K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 20:31:25 እግዱ ተነስቷል

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

የአባ ሳዊሮስ፣
የአባ ኤዎስጣቴዎስ
የአባ ዜና ማርቆስ #ዕግድ_መነሳቱን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

(ተሚማ)
@EthioipaNews
5.4K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 12:21:32
ተፈቷል

በዛሬው እለት በ33 ጠበቆች ፍርድ ቤት የቀረበው ፓስተር ቢኒየም በዋስ እንዲወጣ ተወሰነ።

ከ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጎን በመቆሙ አላግባብ የታሰረው ፓስተር ቢኒያም  በ33 ጠበቆች ቡድን ክርክር  በ5000 ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ፍርድቤቱ ወስኗል ሲል ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ አስታውቋል።

@EthioipaNews
6.1K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:53:53
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ዕቅድ መያዛቸው ተሰማ!

አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን አንቶኒ ብሊንከንን ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዕቅድ መያዟ ተሰምቷል፡፡የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አንቶኒ ብሊንከንን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዕቅድ መያዙ የተሰማ ቢሆንም፣ ሚኒስትሩ መቼ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ቁርጥ ያለ ቀን አልተገለጸም፡፡

በአገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው አፍሪካ ኢንተለጀንስ ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ የብሊንከን የኢትዮጵያ ጉዞ በሚቀጥለው መጋቢት ወር ላይ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ብሊንከን ከዚህ በፊት ባለፈው የፈረጀንጆቹ 2022 ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸው የሚታወሰ ነው፡፡

ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡበት ዋና አጀንዳ በውል ባይታወቅም፣ በተለይ አሜሪካ በታዛቢነት በተሳተፈችበት የሕወሓት እና የፌደራል መንግሥት የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በፕሪቶሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በሽግግር ፍትሕ ላይ የተመሰረተ ተጠያቂነት ከኹለቱም ወገን እንደሚኖር በሚጠበቀው ጉዳይ ላይ አሜሪካ ፍላጎት እንዳላት በተለያየ ጊዜ አንጸባርቃለች፡፡

[Addis Maleda]
@EthioipaNews
5.4K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:53:53
በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎጂ ሆነዋል!

ሁለት ሚሊዮን 200 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል
ከ604 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግሥት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

በድርቁ ከሁለት ሚሊዮን በላይ እንስሳት መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተጠቁሟል።

ሙሉ ዘገባው:- https://www.press.et/?p=92996
@EthioipaNews
4.9K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ