Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ግልፅ አቋም! ጎንደር ወልቃይጥ ጠገዴ ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እን | EthioipaNews

ሰበር ዜና

ግልፅ አቋም! ጎንደር ወልቃይጥ ጠገዴ

ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስና ህልውናችንን ለማስከበር እንሠራለን"

የሕግ ማሕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሐቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን! "

"#የህወሓት ወራሪ ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴ አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውና በሕዝባችን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር፤ ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ሕዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን!"

*

እኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ፣ የካቲት 17 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ጎንደር  ከተማችን ተሰባስበን “በፈተና እንፀናለን፤ በሥራ እንገለጣለን፡- ዘላቂ የሕግ አሸናፊነት” በሚል  ርእስ ከመከርን በኋላ፤ የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡-

1) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መሆኑን በማመን፤ እስከመጨረሻው ከወገኖቻችን ጋር ፀንተን ለመቆም ተስማምተናል!

2) ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ፤ ከዚህ በኋላም ለሚደረገው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ትግል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ እና ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል ቃል እንገባለን!

3) የወልቃይት ጠገዴ ትግል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሰማዕት የሆኑበት መሆኑን በመረዳት፤ የትግሉን ሰማዕታት አደራ ለመጠበቅ እንተጋለን!

4) የማንነት ትግሉ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጥያቄው ተጋሪ እንዲሆኑ እና ከፍትሕ ጎን እንዲቆሙ እውነታውን ለማስገንዘብ እንሠራለን!

5) የማንነት ትግሉ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች አገር ዐቀፍና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እውነታውን ተገንዝበው ከፍትሕና ከእውነት ጎን እንዲቆሙ እንሠራለን!

6) ትግሉ ለጥቂት ግለሰቦች የሚሰጥ እና የውስን ጊዜ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም የማንነት ትግሉ የሁላችንም፣ የሁልጊዜም እና አሸናፊ እስከምንሆን የምንቀጥልበት መሆኑን በማመን፤ እያንዳንዳችን የትግሉ መሪ ተዋናዮች መሆናችንን በተግባር እናረጋግጣለን!

7) አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ፍትሕ ሲሰፍን ነው፡፡ ስለሆነም፤ የትግራይ ወራሪ ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴ አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውና በሕዝባችን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር፤ ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ሕዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን!

8) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን፤ የትግሉ አስኳልና የአገራዊ ለውጡ ቀንዲል በመሆኑ፤ ገዥው ብልጽግና ፓርቲና የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት በእጁ ያሉትን የሕግ ማሕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሐቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን!

9) ወራሪው ኃይል ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር፤ እንደተለመደው በዕብሪት ተነሳስቶ በሕዝባችን ላይ ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ መሆኑን በመገንዘብ፤ “ዋነኛው ሠራዊታችን ሕዝባችን ነውና” በሁሉም ማዕዘን የሚኖረውን ሕዝባችንን አንቀሳቅሰን ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስና ህልውናችንን ለማስከበር እንሠራለን!

10) የጎንደር ሕዝብ በየዘመናቱ የፀረ እኩልነትና ፀረ ፍትሕ ኃይሎች ሲለባ ሲሆን የቆየ ሕዝብ ነው፡፡ ስለሆነም፤ የግፈኞች የጭቆና ሰለባ በመሆናችን፤ በአገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላምና ሁለንተናዊ ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው ፍትሕ እና እኩልነት ሲረጋገጥ መሆኑን በማመን፤ ሁልጊዜም ከፍትሕና እኩልነት ጎን የምንቆም ሆናችንን እናረጋግጣለን!

ሁላችንም ሁልጊዜም አሸናፊዎች እስከምንሆን እንታገላለን!

@EthioipaNews